Wa Al-`Ādiyāti Đabĥāan  | 100-001 እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡ | وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحاً |
Fālmūriyāti Qadĥāan  | 100-002 (በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤ | فَالْمُورِيَاتِ قَدْحاً |
Fālmughīrāti Şubĥāan  | 100-003 በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤ | فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحاً |
Fa'atharna Bihi Naq`āan  | 100-004 በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤ | فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعاً |
Fawasaţna Bihi Jam`āan  | 100-005 በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡ | فَوَسَطْنَ بِهِ جَمْعاً |
'Inna Al-'Insāna Lirabbihi Lakanūdun  | 100-006 ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡ | إِنَّ الإِنسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ |
Wa 'Innahu `Alá Dhālika Lashahīdun  | 100-007 እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡ | وَإِنَّهُ عَلَى ذَلِكَ لَشَهِيدٌ |
Wa 'Innahu Liĥubbi Al-Khayri Lashadīdun  | 100-008 እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡ | وَإِنَّهُ لِحُبِّ الْخَيْرِ لَشَدِيدٌ |
'Afalā Ya`lamu 'Idhā Bu`thira Mā Fī Al-Qubūri  | 100-009 (ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤ | أَفَلاَ يَعْلَمُ إِذَا بُعْثِرَ مَا فِي الْقُبُورِ |
Wa Ĥuşşila Mā Fī Aş-Şudūri  | 100-010 በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡ | وَحُصِّلَ مَا فِي الصُّدُورِ |
'Inna Rabbahum Bihim Yawma'idhin Lakhabīrun  | 100-011 ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡ | إِنَّ رَبَّهُمْ بِهِمْ يَوْمَئِذٍ لَخَبِيرٌ |