'Idhā Zulzilati Al-'Arđu Zilzālahā  | 099-001 ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ | إِذَا زُلْزِلَتِ الأَرْضُ زِلْزَالَهَا |
Wa 'Akhrajati Al-'Arđu 'Athqālahā  | 099-002 ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤ | وَأَخْرَجَتِ الأَرْضُ أَثْقَالَهَا |
Wa Qāla Al-'Insānu Mā Lahā  | 099-003 ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤ | وَقَالَ الإِنسَانُ مَا لَهَا |
Yawma'idhin Tuĥaddithu 'Akhbārahā  | 099-004 በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡ | يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا |
Bi'anna Rabbaka 'Awĥá Lahā  | 099-005 ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡ | بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَى لَهَا |
Yawma'idhin Yaşduru An-Nāsu 'Ashtātāan Liyuraw 'A`mālahum  | 099-006 በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡ | يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتاً لِيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ |
Faman Ya`mal Mithqāla Dharratin Khayrāan Yarahu  | 099-007 የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ | فَمَنْ يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْراً يَرَهُ |
Wa Man Ya`mal Mithqāla Dharratin Sharrāan Yarahu  | 099-008 የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ | وَمَنْ يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرّاً يَرَهُ |