Lam Yakuni Al-Ladhīna Kafarū Min 'Ahli Al-Kitābi Wa Al-Mushrikīna Munfakkīna Ĥattá Ta'tiyahumu Al-Bayyinahu  | 098-001 እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ | لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّى تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ |
Rasūlun Mina Al-Lahi Yatlū Şuĥufāan Muţahharahan  | 098-002 (አስረጁም) ከአላህ የኾነ መልክተኛ የተጥራሩን መጽሐፎች የሚያነብ ነው፡፡ | رَسُولٌ مِنَ اللَّهِ يَتْلُوا صُحُفاً مُطَهَّرَةً |
Fīhā Kutubun Qayyimahun  | 098-003 በውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ ጽሑፎች ያሉባት የኾነችን፡፡ | فِيهَا كُتُبٌ قَيِّمَةٌ |
Wa Mā Tafarraqa Al-Ladhīna 'Ūtū Al-Kitāba 'Illā Min Ba`di Mā Jā'at/humu Al-Bayyinahu  | 098-004 እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ግልጽ አስረጅ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ | وَمَا تَفَرَّقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ إِلاَّ مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَةُ |
Wa Mā 'Umirū 'Illā Liya`budū Al-Laha Mukhlişīna Lahu Ad-Dīna Ĥunafā'a Wa Yuqīmū Aş-Şalāata Wa Yu'utū Az-Zakāata Wa Dhalika Dīnu Al-Qayyimahi  | 098-005 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡ | وَمَا أُمِرُوا إِلاَّ لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلاَةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ وَذَلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ |
'Inna Al-Ladhīna Kafarū Min 'Ahli Al-Kitābi Wa Al-Mushrikīna Fī Nāri Jahannama Khālidīna Fīhā 'Ūlā'ika Hum Sharru Al-Barīyahi  | 098-006 እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ | إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أُوْلَائِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ |
'Inna Al-Ladhīna 'Āmanū Wa `Amilū Aş-Şāliĥāti 'Ūlā'ika Hum Khayru Al-Barīyahi  | 098-007 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ | إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُوْلَائِكَ هُمْ خَيْرُ الْبَرِيَّةِ |
Jazā'uuhum `Inda Rabbihim Jannātu `Adnin Tajrī Min Taĥtihā Al-'Anhāru Khālidīna Fīhā 'Abadāan Rađiya Al-Lahu `Anhum Wa Rađū `Anhu Dhālika Liman Khashiya Rabbahu  | 098-008 በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡ | جَزَاؤُهُمْ عِنْدَ رَبِّهِمْ جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَداً رَضِيَ اللَّهُ عَ
|