Aqra' Biāsmi Rabbika Al-Ladhī Khalaqa  | 096-001 አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ | اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ |
Khalaqa Al-'Insāna Min `Alaqin  | 096-002 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ | خَلَقَ الإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ |
Aqra' Wa Rabbuka Al-'Akramu  | 096-003 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ | اقْرَأْ وَرَبُّكَ الأَكْرَمُ |
Al-Ladhī `Allama Bil-Qalami  | 096-004 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ | الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ |
`Allama Al-'Insāna Mā Lam Ya`lam  | 096-005 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ | عَلَّمَ الإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ |
Kallā 'Inna Al-'Insāna Layaţghá  | 096-006 በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ | كَلاَّ إِنَّ الإِنسَانَ لَيَطْغَى |
'An Ra'āhu Astaghná  | 096-007 ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ | أَنْ رَآهُ اسْتَغْنَى |
'Inna 'Ilá Rabbika Ar-Ruj`á  | 096-008 መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ | إِنَّ إِلَى رَبِّكَ الرُّجْعَى |
'Ara'ayta Al-Ladhī Yanhá  | 096-009 አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ | أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَى |
`Abdāan 'Idhā Şallá  | 096-010 ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ | عَبْداً إِذَا صَلَّى |
'Ara'ayta 'In Kāna `Alá Al-Hudá  | 096-011 አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ | أَرَأَيْتَ إِنْ كَانَ عَلَى الْهُدَى |
'Aw 'Amara Bit-Taqwá  | 096-012 ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ | أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَى |
'Ara'ayta 'In Kadhdhaba Wa Tawallá  | 096-013 አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ | أَرَأَيْتَ إِنْ كَذَّبَ وَتَوَلَّى |
'Alam Ya`lam Bi'anna Al-Laha Yará  | 096-014 አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? | أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَى |
Kallā La'in Lam Yantahi Lanasfa`ā Bin-Nāşiyahi  | 096-015 ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ | كَلاَّ لَئِنْ لَمْ يَنْتَهِ لَنَسْفَعَا بِالنَّاصِيَةِ |
Nāşiyatin Kādhibatin Khāţi'ahin  | 096-016 ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ | نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ |
Falyad`u Nādiyah  | 096-017 ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ | فَلْيَدْعُ نَادِيَه |
Sanad`u Az-Zabāniyaha  | 096-018 (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ | سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ |
Kallā Lā Tuţi`hu Wa Asjud Wāqtarib  | 096-019 ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ | كَلاَّ لاَ تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِبْ |