Wa Al-Layli 'Idhā Yaghshá | 092-001 በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ | وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَى |
Wa An-Nahāri 'Idhā Tajallá | 092-002 በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡ | وَالنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّى |
Wa Mā Khalaqa Adh-Dhakara Wa Al-'Unthá | 092-003 ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡ | وَمَا خَلَقَ الذَّكَرَ وَالأُنْثَى |
'Inna Sa`yakum Lashattá | 092-004 ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡ | إِنَّ سَعْيَكُمْ لَشَتَّى |
Fa'ammā Man 'A`ţá Wa Attaqá | 092-005 የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡ | فَأَمَّا مَنْ أَعْطَى وَاتَّقَى |
Wa Şaddaqa Bil-Ĥusná | 092-006 በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ | وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَى |
Fasanuyassiruhu Lilyusrá | 092-007 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ | فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَى |
Wa 'Ammā Man Bakhila Wa Astaghná | 092-008 የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤ | وَأَمَّا مَنْ بَخِلَ وَاسْتَغْنَى |
Wa Kadhdhaba Bil-Ĥusná | 092-009 በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤ | وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَى |
Fasanuyassiruhu Lil`usrá | 092-010 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ | فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَى |
Wa Mā Yughnī `Anhu Māluhu 'Idhā Taraddá | 092-011 በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ | وَمَا يُغْنِي عَنْهُ مَالُهُ إِذَا تَرَدَّى |
'Inna `Alaynā Lalhudá | 092-012 ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡ | إِنَّ عَلَيْنَا لَلْهُدَى |
Wa 'Inna Lanā Lal'ākhirata Wa Al-'Ūlá | 092-013 መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡ | وَإِنَّ لَنَا لَلآخِرَةَ وَالأُولَى |
Fa'andhartukum Nārāan Talažžá | 092-014 የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡ | فَأَنْذَرْتُكُمْ نَاراً تَلَظَّى |
Lā Yaşlāhā 'Illā Al-'Ashqá | 092-015 ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡ | لاَ يَصْلاَهَا إِلاَّ الأَشْقَى |
Al-Ladhī Kadhdhaba Wa Tawallá | 092-016 ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡ | الَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّى |
Wa Sayujannabuhā Al-'Atqá | 092-017 አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡ | وَسَيُجَنَّبُهَا الأَتْقَى |
Al-Ladhī Yu'utī Mālahu Yatazakká | 092-018 ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡ | الَّذِي يُؤْتِي مَالَهُ يَتَزَكَّى |
Wa Mā Li'ĥadin `Indahu Min Ni`matin Tujzá | 092-019 ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ | وَمَا لِأحَدٍ عِنْدَهُ مِنْ نِعْمَةٍ تُجْزَى |
'Illā Abtighā'a Wajhi Rabbihi Al-'A`lá | 092-020 ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ | إِلاَّ ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِ الأَعْلَى |
Wa Lasawfa Yarđá | 092-021 ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡ | وَلَسَوْفَ يَرْضَى |