Wa Ash-Shamsi Wa Đuĥāhā  | 091-001 በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ | وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا |
Wa Al-Qamari 'Idhā Talāhā  | 091-002 በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ | وَالْقَمَرِ إِذَا تَلاَهَا |
Wa An-Nahāri 'Idhā Jallāhā  | 091-003 በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ | وَالنَّهَارِ إِذَا جَلاَّهَا |
Wa Al-Layli 'Idhā Yaghshāhā  | 091-004 በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ | وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا |
Wa As-Samā'i Wa Mā Banāhā  | 091-005 በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ | وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا |
Wa Al-'Arđi Wa Mā Ţaĥāhā  | 091-006 በምድሪቱም በዘረጋትም፤ | وَالأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا |
Wa Nafsin Wa Mā Sawwāhā  | 091-007 በነፍስም ባስተካከላትም፤ | وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا |
Fa'alhamahā Fujūrahā Wa Taqwāhā  | 091-008 አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ | فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا |
Qad 'Aflaĥa Man Zakkāhā  | 091-009 (ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ | قَدْ أَفْلَحَ مَنْ زَكَّاهَا |
Wa Qad Khāba Man Dassāhā  | 091-010 (በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ | وَقَدْ خَابَ مَنْ دَسَّاهَا |
Kadhdhabat Thamūdu Biţaghwāhā  | 091-011 ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ | كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا |
'Idhi Anba`atha 'Ashqāhā  | 091-012 ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ | إِذِ انْبَعَثَ أَشْقَاهَا |
Faqāla Lahum Rasūlu Al-Lahi Nāqata Al-Lahi Wa Suqyāhā  | 091-013 ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) آ«የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)آ» አላቸው፡፡ | فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا |
Fakadhdhabūhu Fa`aqarūhā Fadamdama `Alayhim Rabbuhum Bidhanbihim Fasawwāhā  | 091-014 አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ | فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُمْ بِذَنْبِهِمْ فَسَوَّاهَا |
Wa Lā Yakhāfu `Uqbāhā  | 091-015 ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡ | وَلاَ يَخَافُ عُقْبَاهَا |