Lā 'Uqsimu Bihadhā Al-Baladi  | 090-001 በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ | لاَ أُقْسِمُ بِهَذَا الْبَلَدِ |
Wa 'Anta Ĥillun Bihadhā Al-Baladi  | 090-002 አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ | وَأَنْتَ حِلٌّ بِهَذَا الْبَلَدِ |
Wa Wālidin Wa Mā Walada  | 090-003 በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ | وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ |
Laqad Khalaqnā Al-'Insāna Fī Kabadin  | 090-004 ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ | لَقَدْ خَلَقْنَا الإِنسَانَ فِي كَبَدٍ |
'Ayaĥsabu 'An Lan Yaqdira `Alayhi 'Aĥadun  | 090-005 በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? | أَيَحْسَبُ أَنْ لَنْ يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ |
Yaqūlu 'Ahlaktu Mālāan Lubadāan  | 090-006 آ«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁآ» ይላል፡፡ | يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالاً لُبَداً |
'Ayaĥsabu 'An Lam Yarahu 'Aĥadun  | 090-007 አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? | أَيَحْسَبُ أَنْ لَمْ يَرَهُ أَحَدٌ |
'Alam Naj`al Lahu `Aynayni  | 090-008 ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? | أَلَمْ نَجْعَلْ لَهُ عَيْنَيْنِ |
Wa Lisānāan Wa Shafatayni  | 090-009 ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ | وَلِسَاناً وَشَفَتَيْنِ |
Wa Hadaynāhu An-Najdayni  | 090-010 ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? | وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ |
Falā Aqtaĥama Al-`Aqabaha  | 090-011 ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ | فَلاَ اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ |
Wa Mā 'Adrāka Mā Al-`Aqabahu  | 090-012 ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? | وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ |
Fakku Raqabahin  | 090-013 (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ | فَكُّ رَقَبَةٍ |
'Aw 'Iţ`āmun Fī Yawmin Dhī Masghabahin  | 090-014 ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ | أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ |
Yatīmāan Dhā Maqrabahin  | 090-015 የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ | يَتِيماً ذَا مَقْرَبَةٍ |
'Aw Miskīnāan Dhā Matrabahin  | 090-016 ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ | أَوْ مِسْكِيناً ذَا مَتْرَبَةٍ |
Thumma Kāna Mina Al-Ladhīna 'Āmanū Wa Tawāşaw Biş-Şabri Wa Tawāşaw Bil-Marĥamahi  | 090-017 (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ | ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ |
'Ūlā'ika 'Aşĥābu Al-Maymanahi  | 090-018 እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ | أُوْلَائِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ |
Wa Al-Ladhīna Kafarū Bi'āyātinā Hum 'Aşĥābu Al-Mash'amahi  | 090-019 እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ | وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ |
`Alayhim Nārun Mu'uşadahun  | 090-020 በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ | عَلَيْهِمْ نَارٌ مُؤصَدَةٌ |