Wa Al-Fajri  | 089-001 በጎህ እምላለሁ፡፡ | وَالْفَجْرِ |
Wa Layālin `Ashrin  | 089-002 በዐሥር ሌሊቶችም፡፡ | وَلَيَالٍ عَشْرٍ |
Wa Ash-Shaf`i Wa Al-Watri  | 089-003 በጥንዱም በነጠላውም፡፡ | وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ |
Wa Al-Layli 'Idhā Yasri  | 089-004 በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡ | وَاللَّيْلِ إِذَا يَسْرِ |
Hal Fī Dhālika Qasamun Lidhī Ĥijrin  | 089-005 በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን? | هَلْ فِي ذَلِكَ قَسَمٌ لِذِي حِجْرٍ |
'Alam Tara Kayfa Fa`ala Rabbuka Bi`ādin  | 089-006 ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን? | أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ |
'Irama Dhāti Al-`Imādi  | 089-007 በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡ | إِرَمَ ذَاتِ الْعِمَادِ |
Allatī Lam Yukhlaq Mithluhā Fī Al-Bilādi  | 089-008 በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡ | الَّتِي لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِي الْبِلاَدِ |
Wa Thamūda Al-Ladhīna Jābū Aş-Şakhra Bil-Wādi  | 089-009 በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡ | وَثَمُودَ الَّذِينَ جَابُوا الصَّخْرَ بِالْوَادِ |
Wa Fir`awna Dhī Al-'Awtādi  | 089-010 በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡ | وَفِرْعَوْنَ ذِي الأَوْتَادِ |
Al-Ladhīna Ţaghaw Fī Al-Bilādi  | 089-011 በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡ | الَّذِينَ طَغَوْا فِي الْبِلاَدِ |
Fa'aktharū Fīhā Al-Fasāda  | 089-012 በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?) | فَأَكْثَرُوا فِيهَا الْفَسَادَ |
Faşabba `Alayhim Rabbuka Sawţa `Adhābin  | 089-013 በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡ | فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ |
'Inna Rabbaka Labiālmirşādi  | 089-014 ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡ | إِنَّ رَبَّكَ لَبِالْمِرْصَادِ |
Fa'ammā Al-'Insānu 'Idhā Mā Abtalāhu Rabbuhu Fa'akramahu Wa Na``amahu Fayaqūlu Rabbī 'Akramani  | 089-015 ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) آ«ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)آ» ይላል፡፡ | فَأَمَّا الإِنسَانُ إِذَا مَا ابْتَلاَهُ رَبُّهُ فَأَكْرَمَهُ وَنَعَّمَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَكْرَمَنِ |
Wa 'Ammā 'Idhā Mā Abtalāhu Faqadara `Alayhi Rizqahu Fayaqūlu Rabbī 'Ahānani  | 089-016 በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ آ«ጌታዬ አሳነሰኝآ» ይላል፡፡ | وَأَمَّا إِذَا مَا ابْتَلاَهُ فَقَدَرَ عَلَيْهِ رِزْقَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَهَانَنِ |
Kallā Bal Lā Tukrimūna Al-Yatīma  | 089-017 ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡ | كَلاَّ بَل لاَ تُكْرِمُونَ الْيَتِيمَ |
Wa Lā Taĥāđđūna `Alá Ţa`āmi Al-Miskīni  | 089-018 ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡ | وَلاَ تَحَاضُّونَ عَلَى طَعَامِ الْمِسْكِينِ |
Wa Ta'kulūna At-Turātha 'Aklāan Lammāan  | 089-019 የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡ | وَتَأْكُلُونَ التُّرَاثَ أَكْلاً لَمّاً |
Wa Tuĥibbūna Al-Māla Ĥubbāan Jammāan  | 089-020 ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ | وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبّاً جَمّاً |
Kallā 'Idhā Dukkati Al-'Arđu Dakkāan Dakkāan  | 089-021 ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ | كَلاَّ إِذَا دُكَّتِ الأَرْضُ دَكّاً دَكّاً |
Wa Jā'a Rabbuka Wa Al-Malaku Şaffāan Şaffāan  | 089-022 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤ | وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفّاً صَفّاً |
Wa Jī'a Yawma'idhin Bijahannama Yawma'idhin Yatadhakkaru Al-'Insānu Wa 'Anná Lahu Adh-Dhikrá  | 089-023 ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ? | وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الإِنْسَانُ وَأَنَّى لَهُ الذِّكْرَى |
Yaqūlu Yā Laytanī Qaddamtu Liĥayātī  | 089-024 آ«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮآ» ይላል፡፡ | يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي |
Fayawma'idhin Lā Yu`adhdhibu `Adhābahu 'Aĥadun  | 089-025 በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡ | فَيَوْمَئِذٍ لاَ يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ |
Wa Lā Yūthiqu Wathāqahu 'Aĥadun  | 089-026 የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡ | وَلاَ يُوثِقُ وَثَاقَهُ أَحَدٌ |
Yā 'Ayyatuhā An-Nafsu Al-Muţma'innahu  | 089-027 (ለአመነች ነፍስም) آ«አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! | يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ |
Arji`ī 'Ilá Rabbiki Rāđiyatan Marđīyahan  | 089-028 آ«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ | ارْجِعِي إِلَى رَبِّكِ رَاضِيَةً مَرْضِيَّةً |
Fādkhulī Fī `Ibādī  | 089-029 آ«በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ | فَادْخُلِي فِي عِبَادِي |
Wa Adkhulī Jannatī  | 089-030 ገነቴንም ግቢ፤آ» (ትባላለች)፡፡ | وَادْخُلِي جَنَّتِي |