Hal 'Atāka Ĥadīthu Al-Ghāshiyahi  | 088-001 የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? | هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ |
Wujūhun Yawma'idhin Khāshi`ahun  | 088-002 ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ | وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ |
`Āmilatun Nāşibahun  | 088-003 ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ | عَامِلَةٌ نَاصِبَةٌ |
Taşlá Nārāan Ĥāmiyahan  | 088-004 ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ | تَصْلَى نَاراً حَامِيَةً |
Tusqá Min `Aynin 'Āniyahin  | 088-005 በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ | تُسْقَى مِنْ عَيْنٍ آنِيَةٍ |
Laysa Lahum Ţa`āmun 'Illā Min Đarī`in  | 088-006 ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ | لَيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلاَّ مِنْ ضَرِيعٍ |
Lā Yusminu Wa Lā Yughnī Min Jū`in  | 088-007 የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ | لاَ يُسْمِنُ وَلاَ يُغْنِي مِنْ جُوعٍ |
Wujūhun Yawma'idhin Nā`imahun  | 088-008 ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ | وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَاعِمَةٌ |
Lisa`yihā Rāđiyahun  | 088-009 ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ | لِسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ |
Fī Jannatin `Āliyahin  | 088-010 በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ | فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ |
Lā Tasma`u Fīhā Lāghiyahan  | 088-011 በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ | لاَ تَسْمَعُ فِيهَا لاَغِيَةً |
Fīhā `Aynun Jāriyahun  | 088-012 በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ | فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ |
Fīhā Sururun Marfū`ahun  | 088-013 በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ | فِيهَا سُرُرٌ مَرْفُوعَةٌ |
Wa 'Akwābun Mawđū`ahun  | 088-014 በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ | وَأَكْوَابٌ مَوْضُوعَةٌ |
Wa Namāriqu Maşfūfahun  | 088-015 የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ | وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ |
Wa Zarābīyu Mabthūthahun  | 088-016 የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ | وَزَرَابِيُّ مَبْثُوثَةٌ |
'Afalā Yanžurūna 'Ilá Al-'Ibili Kayfa Khuliqat  | 088-017 (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች! | أَفَلاَ يَنْظُرُونَ إِلَى الإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ |
Wa 'Ilá As-Samā'i Kayfa Rufi`at  | 088-018 ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች! | وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ |
Wa 'Ilá Al-Jibāli Kayfa Nuşibat  | 088-019 ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ! | وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ |
Wa 'Ilá Al-'Arđi Kayfa Suţiĥat  | 088-020 ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?) | وَإِلَى الأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ |
Fadhakkir 'Innamā 'Anta Mudhakkirun  | 088-021 አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ | فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنْتَ مُذَكِّرٌ |
Lasta `Alayhim Bimusayţirin  | 088-022 በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ | لَسْتَ عَلَيْهِمْ بِمُسَيْطِرٍ |
'Illā Man Tawallá Wa Kafara  | 088-023 ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ | إِلاَّ مَنْ تَوَلَّى وَكَفَرَ |
Fayu`adhdhibuhu Al-Lahu Al-`Adhāba Al-'Akbara  | 088-024 አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ | فَيُعَذِّبُهُ اللَّهُ الْعَذَابَ الأَكْبَرَ |
'Inna 'Ilaynā 'Īābahum  | 088-025 መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ | إِنَّ إِلَيْنَا إِيَابَهُمْ |
Thumma 'Inna `Alaynā Ĥisābahum  | 088-026 ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ | ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُمْ |