Wa As-Samā'i Wa Aţ-Ţāriqi  | 086-001 በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ | وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ |
Wa Mā 'Adrāka Mā Aţ-Ţāriqu  | 086-002 የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? | وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ |
An-Najmu Ath-Thāqibu  | 086-003 ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ | النَّجْمُ الثَّاقِبُ |
'In Kullu Nafsin Lammā `Alayhā Ĥāfižun  | 086-004 ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ | إِنْ كُلُّ نَفْسٍ لَمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ |
Falyanžuri Al-'Insānu Mimma Khuliqa  | 086-005 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ | فَلْيَنظُرِ الإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ |
Khuliqa Min Mā'in Dāfiqin  | 086-006 ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ | خُلِقَ مِنْ مَاءٍ دَافِقٍ |
Yakhruju Min Bayni Aş-Şulbi Wa At-Tarā'ibi  | 086-007 ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ | يَخْرُجُ مِنْ بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ |
'Innahu `Alá Raj`ihi Laqādirun  | 086-008 እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ | إِنَّهُ عَلَى رَجْعِهِ لَقَادِرٌ |
Yawma Tublá As-Sarā'iru  | 086-009 ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ | يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ |
Famā Lahu Min Qūwatin Wa Lā Nāşirin  | 086-010 ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ | فَمَا لَهُ مِنْ قُوَّةٍ وَلاَ نَاصِرٍ |
Wa As-Samā'i Dhāti Ar-Raj`i  | 086-011 የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ | وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ |
Wa Al-'Arđi Dhāti Aş-Şad`i  | 086-012 (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ | وَالأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ |
'Innahu Laqawlun Faşlun  | 086-013 እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ | إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ |
Wa Mā Huwa Bil-Hazli  | 086-014 እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ | وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ |
'Innahum Yakīdūna Kaydāan  | 086-015 እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ | إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْداً |
Wa 'Akīdu Kaydāan  | 086-016 (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ | وَأَكِيدُ كَيْداً |
Famahhili Al-Kāfirīna 'Amhilhum Ruwaydāan  | 086-017 ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ | فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْداً |