Wa As-Samā'i Dhāti Al-Burūji  | 085-001 የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ | وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ |
Wa Al-Yawmi Al-Maw`ūdi  | 085-002 በተቀጠረው ቀንም፤ | وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ |
Wa Shāhidin Wa Mash/hūdin  | 085-003 በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ | وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ |
Qutila 'Aşĥābu Al-'Ukhdūdi  | 085-004 የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ | قُتِلَ أَصْحَابُ الأُخْدُودِ |
An-Nāri Dhāti Al-Waqūdi  | 085-005 የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ | النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ |
'Idh Hum `Alayhā Qu`ūdun  | 085-006 እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ | إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ |
Wa Hum `Alá Mā Yaf`alūna Bil-Mu'uminīna Shuhūdun  | 085-007 እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ | وَهُمْ عَلَى مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ |
Wa Mā Naqamū Minhum 'Illā 'An Yu'uminū Bil-Lahi Al-`Azīzi Al-Ĥamīdi  | 085-008 ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ | وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلاَّ أَنْ يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ |
Al-Ladhī Lahu Mulku As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Allāhu `Alá Kulli Shay'in Shahīdun  | 085-009 በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ | الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَاللَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ |
'Inna Al-Ladhīna Fatanū Al-Mu'uminīna Wa Al-Mu'umināti Thumma Lam Yatūbū Falahum `Adhābu Jahannama Wa Lahum `Adhābu Al-Ĥarīqi  | 085-010 እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ | إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ |
'Inna Al-Ladhīna 'Āmanū Wa `Amilū Aş-Şāliĥāti Lahum Jannātun Tajrī Min Taĥtihā Al-'Anhāru Dhālika Al-Fawzu Al-Kabīru  | 085-011 እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ | إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الأَنْهَارُ ذَلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ |
'Inna Baţsha Rabbika Lashadīdun  | 085-012 የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ | إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ |
'Innahu Huwa Yubdi'u Wa Yu`īdu  | 085-013 እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ | إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ |
Wa Huwa Al-Ghafūru Al-Wadūdu  | 085-014 እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ | وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ |
Dhū Al-`Arshi Al-Majīdu  | 085-015 የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ | ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ |
Fa``ālun Limā Yurīdu  | 085-016 የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ | فَعَّالٌ لِمَا يُرِيدُ |
Hal 'Atāka Ĥadīthu Al-Junūdi  | 085-017 የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን? | هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ |
Fir`awna Wa Thamūda  | 085-018 የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ | فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ |
Bali Al-Ladhīna Kafarū Fī Takdhībin  | 085-019 በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ | بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ |
Wa Allāhu Min Warā'ihim Muĥīţun  | 085-020 አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ | وَاللَّهُ مِنْ وَرَائِهِمْ مُحِيطٌ |
Bal Huwa Qur'ānun Majīdun  | 085-021 ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ | بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَجِيدٌ |
Fī Lawĥin Maĥfūžin  | 085-022 የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ | فِي لَوْحٍ مَحْفُوظٍ |