'Idhā As-Samā'u Anshaqqat  | 084-001 ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤ | إِذَا السَّمَاءُ انشَقَّتْ |
Wa 'Adhinat Lirabbihā Wa Ĥuqqat  | 084-002 ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ | وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ |
Wa 'Idhā Al-'Arđu Muddat  | 084-003 ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ | وَإِذَا الأَرْضُ مُدَّتْ |
Wa 'Alqat Mā Fīhā Wa Takhallat  | 084-004 በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤ | وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ |
Wa 'Adhinat Lirabbihā Wa Ĥuqqat  | 084-005 ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡ | وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ |
Yā 'Ayyuhā Al-'Insānu 'Innaka Kādiĥun 'Ilá Rabbika Kadĥāan Famulāqīhi  | 084-006 አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡ | يَاأَيُّهَا الإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَى رَبِّكَ كَدْحاً فَمُلاَقِيهِ |
Fa'ammā Man 'Ūtiya Kitābahu Biyamīnihi  | 084-007 መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤ | فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ |
Fasawfa Yuĥāsabu Ĥisābāan Yasīrāan  | 084-008 በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡ | فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَاباً يَسِيراً |
Wa Yanqalibu 'Ilá 'Ahlihi Masrūrāan  | 084-009 ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡ | وَيَنقَلِبُ إِلَى أَهْلِهِ مَسْرُوراً |
Wa 'Ammā Man 'Ūtiya Kitābahu Warā'a Žahrihi  | 084-010 መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤ | وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاءَ ظَهْرِهِ |
Fasawfa Yad`ū Thubūrāan  | 084-011 (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡ | فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُوراً |
Wa Yaşlá Sa`īrāan  | 084-012 የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡ | وَيَصْلَى سَعِيراً |
'Innahu Kāna Fī 'Ahlihi Masrūrāan  | 084-013 እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡ | إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُوراً |
'Innahu Žanna 'An Lan Yaĥūra  | 084-014 እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡ | إِنَّهُ ظَنَّ أَنْ لَنْ يَحُورَ |
Balá 'Inna Rabbahu Kāna Bihi Başīrāan  | 084-015 አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡ | بَلَى إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيراً |
Falā 'Uqsimu Bish-Shafaqi  | 084-016 አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡ | فَلاَ أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ |
Wa Al-Layli Wa Mā Wasaqa  | 084-017 በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤ | وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ |
Wa Al-Qamari 'Idhā Attasaqa  | 084-018 በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡ | وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ |
Latarkabunna Ţabaqāan `An Ţabaqin  | 084-019 ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ | لَتَرْكَبُنَّ طَبَقاً عَنْ طَبَقٍ |
Famā Lahum Lā Yu'uminūna  | 084-020 የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? | فَمَا لَهُمْ لاَ يُؤْمِنُونَ |
Wa 'Idhā Quri'a `Alayhimu Al-Qur'ānu Lā Yasjudūna  | 084-021 በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?) | وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لاَ يَسْجُدُونَ |
Bali Al-Ladhīna Kafarū Yukadhdhibūna  | 084-022 በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡ | بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ |
Wa Allāhu 'A`lamu Bimā Yū`ūna  | 084-023 አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ | وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ |
Fabashshirhum Bi`adhābin 'Alīmin  | 084-024 በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡ | فَبَشِّرْهُمْ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ |
'Illā Al-Ladhīna 'Āmanū Wa `Amilū Aş-Şāliĥāti Lahum 'Ajrun Ghayru Mamnūnin  | 084-025 ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡ | إِلاَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ |