'Idhā As-Samā'u Anfaţarat  | 082-001 ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ | إِذَا السَّمَاءُ انفَطَرَتْ |
Wa 'Idhā Al-Kawākibu Antatharat  | 082-002 ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ | وَإِذَا الْكَوَاكِبُ انتَثَرَتْ |
Wa 'Idhā Al-Biĥāru Fujjirat  | 082-003 ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ | وَإِذَا الْبِحَارُ فُجِّرَتْ |
Wa 'Idhā Al-Qubūru Bu`thirat  | 082-004 መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ | وَإِذَا الْقُبُورُ بُعْثِرَتْ |
`Alimat Nafsun Mā Qaddamat Wa 'Akhkharat  | 082-005 ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ | عَلِمَتْ نَفْسٌ مَا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ |
Yā 'Ayyuhā Al-'Insānu Mā Gharraka Birabbika Al-Karīmi  | 082-006 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? | يَاأَيُّهَا الإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ |
Al-Ladhī Khalaqaka Fasawwāka Fa`adalaka  | 082-007 በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ | الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ |
Fī 'Ayyi Şūratin Mā Shā'a Rakkabaka  | 082-008 በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ | فِي أَيِّ صُورَةٍ مَا شَاءَ رَكَّبَكَ |
Kallā Bal Tukadhdhibūna Bid-Dīni  | 082-009 ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ | كَلاَّ بَلْ تُكَذِّبُونَ بِالدِّينِ |
Wa 'Inna `Alaykum Laĥāfižīna  | 082-010 በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ | وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ |
Kirāmāan Kātibīna  | 082-011 የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ | كِرَاماً كَاتِبِينَ |
Ya`lamūna Mā Taf`alūna  | 082-012 የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ | يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ |
'Inna Al-'Abrāra Lafī Na`īmin  | 082-013 እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ | إِنَّ الأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ |
Wa 'Inna Al-Fujjāra Lafī Jaĥīmin  | 082-014 ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ | وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ |
Yaşlawnahā Yawma Ad-Dīni  | 082-015 በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ | يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ الدِّينِ |
Wa Mā Hum `Anhā Bighā'ibīna  | 082-016 እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ | وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَائِبِينَ |
Wa Mā 'Adrāka Mā Yawmu Ad-Dīni  | 082-017 የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? | وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ |
Thumma Mā 'Adrāka Mā Yawmu Ad-Dīni  | 082-018 ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? | ثُمَّ مَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ |
Yawma Lā Tamliku Nafsun Linafsin Shay'āan Wa Al-'Amru Yawma'idhin Lillahi  | 082-019 (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡ | يَوْمَ لاَ تَمْلِكُ نَفْسٌ لِنَفْسٍ شَيْئاً وَالأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِلَّهِ |