81) Sūrat At-Takwīr

Printed format

81) سُورَة التَّكوِير

'Idhā Ash-Shamsu Kūwirat 081-001 ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤ إِذَا ا‍لشَّمْسُ كُوِّرَتْ
Wa 'Idhā An-Nujūmu Ankadarat 081-002 ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُج‍‍ُ‍و‍مُ ا‍ن‍كَدَرَتْ
Wa 'Idhā Al-Jibālu Suyyirat 081-003 ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْجِب‍‍َ‍ا‍لُ سُيِّرَتْ
Wa 'Idhā Al-`Ishāru `Uţţilat 081-004 የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْعِش‍‍َ‍ا‍رُ عُطِّلَتْ
Wa 'Idhā Al-Wuĥūshu Ĥushirat 081-005 እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْوُح‍‍ُ‍و‍شُ حُشِرَتْ
Wa 'Idhā Al-Biĥāru Sujjirat 081-006 ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْبِح‍‍َ‍ا‍رُ سُجِّرَتْ
Wa 'Idhā An-Nufūsu Zūwijat 081-007 ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُف‍‍ُ‍و‍سُ زُوِّجَتْ
Wa 'Idhā Al-Maw'ūdatu Su'ilat 081-008 በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْمَوْء‍ُ‍ودَةُ سُئِلَتْ
Bi'ayyi Dhanbin Qutilat 081-009 በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤ بِأَيِّ ذَ‍ن‍‍ْب‍‍‍ٍ قُتِلَتْ
Wa 'Idhā Aş-Şuĥufu Nushirat 081-010 ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لصُّحُفُ نُشِرَتْ
Wa 'Idhā As-Samā'u Kushiţat 081-011 ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءُ كُشِطَتْ
Wa 'Idhā Al-Jaĥīmu Su``irat 081-012 ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْجَح‍‍ِ‍ي‍مُ سُعِّرَتْ
Wa 'Idhā Al-Jannatu 'Uzlifat 081-013 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤ وَإِذَا ا‍لْجَ‍‍ن‍ّ‍‍َةُ أُزْلِفَتْ
`Alimat Nafsun Mā 'Aĥđarat 081-014 ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤ عَلِمَتْ نَفْس‍‍‍ٌ مَ‍‍ا‍ أَحْضَرَتْ
Falā 'Uqsimu Bil-Khunnasi 081-015 ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡ فَلاَ أُ‍ق‍‍ْسِمُ بِ‍‍ا‍لْخُ‍‍ن‍ّ‍‍َسِ
Al-Jawāri Al-Kunnasi 081-016 ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡ ا‍لْجَو‍َا‍ر‍ِ ا‍لْكُ‍‍ن‍ّ‍‍َسِ
Wa Al-Layli 'Idhā `As`asa 081-017 በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤ وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ
Wa Aş-Şubĥi 'Idhā Tanaffasa 081-018 በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡ وَالصُّ‍‍ب‍‍ْحِ إِذَا تَنَفَّسَ
'Innahu Laqawlu Rasūlin Karīmin 081-019 እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َهُ لَقَوْلُ رَس‍‍ُ‍و‍ل‍‍‍ٍ كَ‍‍ر‍‍ِي‍م‍‍‍ٍ
Dhī Qūwatin `Inda Dhī Al-`Arshi Makīnin 081-020 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ ذِي قُوَّةٍ عِ‍‍ن‍‍ْدَ ذِي ا‍لْعَرْشِ مَك‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Muţā`in Thamma 'Amīnin 081-021 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡ مُط‍‍َ‍ا‍ع‍‍‍ٍ ثَ‍‍م‍ّ‍‍َ أَم‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Wa Mā Şāĥibukum Bimajnūnin 081-022 ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَمَا صَاحِبُكُ‍‍م‍ْ بِمَ‍‍ج‍‍ْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٍ
Wa Laqad Ra'āhu Bil-'Ufuqi Al-Mubīni 081-023 በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ رَآهُ بِ‍‍ا‍لأُفُقِ ا‍لْمُب‍‍ِ‍ي‍نِ
Wa Mā Huwa `Alá Al-Ghaybi Biđanīnin 081-024 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ عَلَى ا‍لْغَيْبِ بِضَن‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Wa Mā Huwa Biqawli Shayţānin Rajīmin 081-025 እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْط‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ رَج‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Fa'ayna Tadh/habūna 081-026 ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ? فَأَيْنَ تَذْهَب‍‍ُ‍و‍نَ
'In Huwa 'Illā Dhikrun Lil`ālamīna 081-027 እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلاَّ ذِكْر‍ٌ لِلْعَالَم‍‍ِ‍ي‍نَ
Liman Shā'a Minkum 'An Yastaqīma 081-028 ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡ لِمَ‍‍ن‍ْ ش‍‍َ‍ا‍ءَ مِ‍‍ن‍‍ْكُمْ أَ‍ن‍ْ يَسْتَق‍‍ِ‍ي‍مَ
Wa Mā Tashā'ūna 'Illā 'An Yashā'a Al-Lahu Rabbu Al-`Ālamīna 081-029 የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡ وَمَا تَش‍‍َ‍ا‍ء‍ُو‍نَ إِلاَّ أَ‍ن‍ْ يَش‍‍َ‍ا‍ءَ ا‍للَّهُ رَبُّ ا‍لْعَالَم‍‍ِ‍ي‍نَ
Next Sūrah