`Abasa Wa Tawallá  | 080-001 ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ | عَبَسَ وَتَوَلَّى |
'An Jā'ahu Al-'A`má  | 080-002 ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ | أَنْ جَاءَهُ الأَعْمَى |
Wa Mā Yudrīka La`allahu Yazzakká  | 080-003 ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ | وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّى |
'Aw Yadhdhakkaru Fatanfa`ahu Adh-Dhikrá  | 080-004 ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ | أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنْفَعَهُ الذِّكْرَى |
'Ammā Mani Astaghná  | 080-005 የተብቃቃው ሰውማ፤ | أَمَّا مَنِ اسْتَغْنَى |
Fa'anta Lahu Taşaddá  | 080-006 አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ | فَأَنْتَ لَهُ تَصَدَّى |
Wa Mā `Alayka 'Allā Yazzakká  | 080-007 ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ | وَمَا عَلَيْكَ أَلاَّ يَزَّكَّى |
Wa 'Ammā Man Jā'aka Yas`á  | 080-008 እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ | وَأَمَّا مَنْ جَاءَكَ يَسْعَى |
Wa Huwa Yakhshá  | 080-009 እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ | وَهُوَ يَخْشَى |
Fa'anta `Anhu Talahhá  | 080-010 አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ | فَأَنْتَ عَنْهُ تَلَهَّى |
Kallā 'Innahā Tadhkirahun  | 080-011 ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ | كَلاَّ إِنَّهَا تَذْكِرَةٌ |
Faman Shā'a Dhakarahu  | 080-012 የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ | فَمَنْ شَاءَ ذَكَرَهُ |
Fī Şuĥufin Mukarramahin  | 080-013 በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ | فِي صُحُفٍ مُكَرَّمَةٍ |
Marfū`atin Muţahharahin  | 080-014 ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ | مَرْفُوعَةٍ مُطَهَّرَةٍ |
Bi'aydī Safarahin  | 080-015 በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ | بِأَيْدِي سَفَرَةٍ |
Kirāmin Bararahin  | 080-016 የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ | كِرَامٍ بَرَرَةٍ |
Qutila Al-'Insānu Mā 'Akfarahu  | 080-017 ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው? | قُتِلَ الإِنْسَانُ مَا أَكْفَرَهُ |
Min 'Ayyi Shay'in Khalaqahu  | 080-018 (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) | مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ |
Min Nuţfatin Khalaqahu Faqaddarahu  | 080-019 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ | مِنْ نُطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ |
Thumma As-Sabīla Yassarahu  | 080-020 ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ | ثُمَّ السَّبِيلَ يَسَّرَهُ |
Thumma 'Amātahu Fa'aqbarahu  | 080-021 ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ | ثُمَّ أَمَاتَهُ فَأَقْبَرَهُ |
Thumma 'Idhā Shā'a 'Ansharahu  | 080-022 ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ | ثُمَّ إِذَا شَاءَ أَنْشَرَهُ |
Kallā Lammā Yaqđi Mā 'Amarahu  | 080-023 በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ | كَلاَّ لَمَّا يَقْضِ مَا أَمَرَهُ |
Falyanžuri Al-'Insānu 'Ilá Ţa`āmihi  | 080-024 ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ | فَلْيَنْظُرِ الإِنسَانُ إِلَى طَعَامِهِ |
'Annā Şababnā Al-Mā'a Şabbāan  | 080-025 እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ | أَنَّا صَبَبْنَا الْمَاءَ صَبّاً |
Thumma Shaqaqnā Al-'Arđa Shaqqāan  | 080-026 ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ | ثُمَّ شَقَقْنَا الأَرْضَ شَقّاً |
Fa'anbatnā Fīhā Ĥabbāan  | 080-027 በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ | فَأَنْبَتْنَا فِيهَا حَبّاً |
Wa `Inabāan Wa Qađbāan  | 080-028 ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ | وَعِنَباً وَقَضْباً |
Wa Zaytūnāan Wa Nakhlāan  | 080-029 የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ | وَزَيْتُوناً وَنَخْلاً |
Wa Ĥadā'iqa Ghulbāan  | 080-030 ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ | وَحَدَائِقَ غُلْباً |
Wa Fākihatan Wa 'Abbāan  | 080-031 ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ | وَفَاكِهَةً وَأَبّاً |
Matā`āan Lakum Wa Li'an`āmikum  | 080-032 ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ | مَتَاعاً لَكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ |
Fa'idhā Jā'ati Aş-Şākhkhahu  | 080-033 አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ | فَإِذَا جَاءَتِ الصَّاخَّةُ |
Yawma Yafirru Al-Mar'u Min 'Akhīhi  | 080-034 ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ | يَوْمَ يَفِرُّ الْمَرْءُ مِنْ أَخِيهِ |
Wa 'Ummihi Wa 'Abīhi  | 080-035 ከናቱም ካባቱም፤ | وَأُمِّهِ وَأَبِيهِ |
Wa Şāĥibatihi Wa Banīhi  | 080-036 ከሚስቱም ከልጁም፤ | وَصَاحِبَتِهِ وَبَنِيهِ |
Likulli Amri'in Minhum Yawma'idhin Sha'nun Yughnīhi  | 080-037 ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ | لِكُلِّ امْرِئٍ مِنْهُمْ يَوْمَئِذٍ شَأْنٌ يُغْنِيهِ |
Wujūhun Yawma'idhin Musfirahun  | 080-038 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ | وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُسْفِرَةٌ |
Đāĥikatun Mustabshirahun  | 080-039 ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ | ضَاحِكَةٌ مُسْتَبْشِرَةٌ |
Wa Wujūhun Yawma'idhin `Alayhā Ghabarahun  | 080-040 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ | وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ |
Tarhaquhā Qatarahun  | 080-041 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ | تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ |
'Ūlā'ika Humu Al-Kafaratu Al-Fajarahu  | 080-042 እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ | أُوْلَائِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ |