78) Sūrat An-Naba'

Printed format

78) سُورَة النَّبَأ

`Amma Yatasā'alūna 078-001 ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? عَ‍‍م‍ّ‍‍َ يَتَس‍‍َ‍ا‍ءَل‍‍ُ‍و‍نَ
`Ani An-Naba'i Al-`Ažīmi 078-002 ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ عَنِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َبَإِ ا‍لْعَظ‍‍ِ‍ي‍مِ
Al-Ladhī Hum Fīhi Mukhtalifūna 078-003 ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ ا‍لَّذِي هُمْ ف‍‍ِ‍ي‍هِ مُخْتَلِف‍‍ُ‍و‍نَ
Kallā Saya`lamūna 078-004 ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ كَلاَّ سَيَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
Thumma Kallā Saya`lamūna 078-005 ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ كَلاَّ سَيَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
'Alam Naj`ali Al-'Arđa Mihādāan 078-006 ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን? أَلَمْ نَ‍‍ج‍‍ْعَلِ ا‍لأَرْضَ مِهَادا‍ً
Wa Al-Jibāla 'Awtādāan 078-007 ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን? وَالْجِب‍‍َ‍ا‍لَ أَوْتَادا‍ً
Wa Khalaqnākum 'Azwājāan 078-008 ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَ‍‍ق‍‍ْنَاكُمْ أَزْوَاجا‍ً
Wa Ja`alnā Nawmakum Subātāan 078-009 እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتا‍ً
Wa Ja`alnā Al-Layla Libāsāan 078-010 ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا ا‍للَّيْلَ لِبَاسا‍ً
Wa Ja`alnā An-Nahāra Ma`āshāan 078-011 ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َه‍‍َ‍ا‍رَ مَعَاشا‍ً
Wa Banaynā Fawqakum Sab`āan Shidādāan 078-012 ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ وَبَنَيْنَا فَوْقَكُمْ سَ‍‍ب‍‍ْعا‍ً شِدَادا‍ً
Wa Ja`alnā Sirājāan Wa Hhājāan 078-013 አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا سِرَاجا‍ً وَهَّاجا‍ً
Wa 'Anzalnā Mina Al-Mu`şirāti Mā'an Thajjājāan 078-014 ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ وَأَن‍زَلْنَا مِنَ ا‍لْمُعْصِر‍َا‍تِ م‍‍َ‍ا‍ء‍ً ثَجَّاجا‍ً
Linukhrija Bihi Ĥabbāan Wa Nabātāan 078-015 በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ لِنُخْ‍‍ر‍‍ِجَ بِهِ حَبّا‍ً وَنَبَاتا‍ً
Wa Jannātin 'Alfāfāan 078-016 የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ وَجَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍تٍ أَلْفَافا‍ً
'Inna Yawma Al-Faşli Kāna Mīqātāan 078-017 የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ يَوْمَ ا‍لْفَصْلِ ك‍‍َ‍ا‍نَ مِيقَاتا‍ً
Yawma Yunfakhu Fī Aş-Şūri Fata'tūna 'Afwājāan 078-018 በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ يَوْمَ يُ‍‍ن‍فَخُ فِي ا‍لصّ‍‍ُ‍و‍ر‍ِ فَتَأْت‍‍ُ‍و‍نَ أَفْوَاجا‍ً
Wa Futiĥati As-Samā'u Fakānat 'Abwābāan 078-019 ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ وَفُتِحَتِ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءُ فَكَانَتْ أَ‍ب‍‍ْوَابا‍ً
Wa Suyyirati Al-Jibālu Fakānat Sarābāan 078-020 ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ وَسُيِّرَتِ ا‍لْجِب‍‍َ‍ا‍لُ فَكَانَتْ سَرَابا‍ً
'Inna Jahannama Kānat Mirşādāan 078-021 ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ إِ‍نّ‍‍َ جَهَ‍‍ن‍ّ‍‍َمَ كَانَتْ مِرْصَادا‍ً
Lilţţāghīna Ma'āan 078-022 ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ لِلْطَّاغ‍‍ِ‍ي‍نَ مَآبا‍ً
Lābithīna Fīhā 'Aĥqābāan 078-023 በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ لاَبِث‍‍ِ‍ي‍نَ فِيهَ‍‍ا‍ أَحْقَابا‍ً
Lā Yadhūqūna Fīhā Bardāan Wa Lā Sharābāan 078-024 በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ لاَ يَذُوق‍‍ُ‍و‍نَ فِيهَا بَرْدا‍ً وَلاَ شَرَابا‍ً
'Illā Ĥamīmāan Wa Ghassāqāan 078-025 ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ إِلاَّ حَمِيما‍ً وَغَسَّاقا‍ً
Jazā'an Wifāqāan 078-026 ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ جَز‍َا‍ء‍ً وِفَاقا‍ً
'Innahum Kānū Lā Yarjūna Ĥisābāan 078-027 እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ إِ‍نّ‍‍َهُمْ كَانُو‍‍ا‍ لاَ يَرْج‍‍ُ‍و‍نَ حِسَابا‍ً
Wa Kadhdhabū Bi'āyātinā Kidhdhābāan 078-028 በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ وَكَذَّبُو‍‍ا‍ بِآيَاتِنَا كِذَّابا‍ً
Wa Kulla Shay'in 'Aĥşaynāhu Kitābāan 078-029 ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْن‍‍َ‍ا‍هُ كِتَابا‍ً
Fadhūqū Falan Nazīdakum 'Illā `Adhābāan 078-030 ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ فَذُوقُو‍‍ا‍ فَلَ‍‍ن‍ْ نَزِيدَكُمْ إِلاَّ عَذَابا‍ً
'Inna Lilmuttaqīna Mafāzāan 078-031 ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ لِلْمُتَّق‍‍ِ‍ي‍نَ مَفَازا‍ً
Ĥadā'iqa Wa 'A`nābāan 078-032 አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ حَد‍َا‍ئِقَ وَأَعْنَابا‍ً
Wa Kawā`iba 'Atrābāan 078-033 እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ وَكَوَاعِبَ أَتْرَابا‍ً
Wa Ka'sāan Dihāqāan 078-034 የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ وَكَأْسا‍ً دِهَاقا‍ً
Lā Yasma`ūna Fīhā Laghwan Wa Lā Kidhdhābāan 078-035 በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ لاَ يَسْمَع‍‍ُ‍و‍نَ فِيهَا لَغْوا‍ً وَلاَ كِذَّابا‍ً
Jazā'an Min Rabbika `Aţā'an Ĥisābāan 078-036 ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ جَز‍َا‍ء‍ً مِ‍‍ن‍ْ رَبِّكَ عَط‍‍َ‍ا‍ءً حِسَابا‍ً
Rabbi As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Mā Baynahumā Ar-Raĥmāni Lā Yamlikūna Minhu Khiţābāan 078-037 የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ رَبِّ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ا‍لرَّحْمَنِ لاَ يَمْلِك‍‍ُ‍و‍نَ مِنْهُ خِطَابا‍ً
Yawma Yaqūmu Ar-Rūĥu Wa Al-Malā'ikatu Şaffāan Lā Yatakallamūna 'Illā Man 'Adhina Lahu Ar-Raĥmānu Wa Qāla Şawābāan 078-038 መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ يَوْمَ يَق‍‍ُ‍و‍مُ ا‍لرّ‍ُو‍حُ وَا‍لْمَلاَئِكَةُ صَفّا‍ً لاَ يَتَكَلَّم‍‍ُ‍و‍نَ إِلاَّ مَنْ أَذِنَ لَهُ ا‍لرَّحْمَنُ وَق‍‍َ‍ا‍لَ صَوَابا‍ً
Dhālika Al-Yawmu Al-Ĥaqqu Faman Shā'a Attakhadha 'Ilá Rabbihi Ma'āan 078-039 ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ ذَلِكَ ا‍لْيَوْمُ ا‍لْحَقُّ فَمَ‍‍ن‍ْ ش‍‍َ‍ا‍ءَ ا‍تَّخَذَ إِلَى رَبِّهِ مَآبا‍ً
'Innā 'Andharnākum `Adhābāan Qarībāan Yawma Yanžuru Al-Mar'u Mā Qaddamat Yadāhu Wa Yaqūlu Al-Kāfiru Yā Laytanī Kuntu Turābāan 078-040 እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا‍ أَن‍ذَرْنَاكُمْ عَذَابا‍ً قَ‍‍ر‍‍ِيبا‍ً يَوْمَ يَ‍‍ن‍ظُرُ ا‍لْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَد‍َا‍هُ وَيَق‍‍ُ‍و‍لُ ا‍لْكَافِ‍‍ر‍ُ يَالَيْتَنِي كُ‍‍ن‍تُ تُرَابا‍ً
Next Sūrah