Hal 'Atá `Alá Al-'Insāni Ĥīnun Mina Ad-Dahri Lam Yakun Shay'āan Madhkūrāan  | 076-001 በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡ | هَلْ أَتَى عَلَى الإِنسَانِ حِينٌ مِنَ الدَّهْرِ لَمْ يَكُنْ شَيْئاً مَذْكُوراً |
'Innā Khalaqnā Al-'Insāna Min Nuţfatin 'Amshājin Nabtalīhi Faja`alnāhu Samī`āan Başīrāan  | 076-002 እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡ | إِنَّا خَلَقْنَا الإِنسَانَ مِنْ نُطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعاً بَصِيراً |
'Innā Hadaynāhu As-Sabīla 'Immā Shākirāan Wa 'Immā Kafūrāan  | 076-003 እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት)፡፡ | إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِراً وَإِمَّا كَفُوراً |
'Innā 'A`tadnā Lilkāfirīna Salāsilāan Wa 'Aghlālāan Wa Sa`īrāan  | 076-004 እኛ ለከሓዲዎች ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም አዘጋጅተናል፡፡ | إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ سَلاَسِلاً وَأَغْلاَلاً وَسَعِيراً |
'Inna Al-'Abrāra Yashrabūna Min Ka'sin Kāna Mizājuhā Kāfūrāan  | 076-005 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ | إِنَّ الأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِنْ كَأْسٍ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُوراً |
`Aynāan Yashrabu Bihā `Ibādu Al-Lahi Yufajjirūnahā Tafjīrāan  | 076-006 ከእርሷ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት (ወደፈለጉበት) ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከኾነች ምንጭ (ይጠጣሉ)፡፡ | عَيْناً يَشْرَبُ بِهَا عِبَادُ اللَّهِ يُفَجِّرُونَهَا تَفْجِيراً |
Yūfūna Bin-Nadhri Wa Yakhāfūna Yawmāan Kāna Sharruhu Mustaţīrāan  | 076-007 (ዛሬ) በስለታቸው ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጪ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡ | يُوفُونَ بِالنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْماً كَانَ شَرُّهُ مُسْتَطِيراً |
Wa Yuţ`imūna Aţ-Ţa`āma `Alá Ĥubbihi Miskīnāan Wa Yatīmāan Wa 'Asīrāan  | 076-008 ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡ | وَيُطْعِمُونَ الطَّعَامَ عَلَى حُبِّهِ مِسْكِيناً وَيَتِيماً وَأَسِيراً |
'Innamā Nuţ`imukum Liwajhi Al-Lahi Lā Nurīdu Minkum Jazā'an Wa Lā Shukūrāan  | 076-009 آ«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡ | إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لاَ نُرِيدُ مِنْكُمْ جَزَاءً وَلاَ شُكُوراً |
'Innā Nakhāfu Min Rabbinā Yawmāan `Abūsāan Qamţarīrāan  | 076-010 آ«እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤آ» (ይላሉ)፡፡ | إِنَّا نَخَافُ مِنْ رَبِّنَا يَوْماً عَبُوساً قَمْطَرِيراً |
Fawaqāhumu Al-Lahu Sharra Dhālika Al-Yawmi Wa Laqqāhum Nađratan Wa Surūrāan  | 076-011 አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው፡፡ (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው፡፡ | فَوَقَاهُمُ اللَّهُ شَرَّ ذَلِكَ الْيَوْمِ وَلَقَّاهُمْ نَضْرَةً وَسُرُوراً |
Wa Jazāhum Bimā Şabarū Jannatan Wa Ĥarīrāan  | 076-012 በመታገሣቸውም ገነትንና የሐር ልብስን መነዳቸው፡፡ | وَجَزَاهُمْ بِمَا صَبَرُوا جَنَّةً وَحَرِيراً |
Muttaki'īna Fīhā `Alá Al-'Arā'iki Lā Yarawna Fīhā Shamsāan Wa Lā Zamharīrāan  | 076-013 በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች በውስጧ ፀሐይንም ጨረቃንም የማያዩ ሲኾኑ፡፡ | مُتَّكِئِينَ فِيهَا عَلَى الأَرَائِكِ لاَ يَرَوْنَ فِيهَا شَمْساً وَلاَ زَمْهَرِيراً |
Wa Dāniyatan `Alayhim Žilāluhā Wa Dhullilat Quţūfuhā Tadhlīlāan  | 076-014 ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች፣ ፍሬዎችዋም (ለለቃሚዎች) መግገራትን የተገራች ስትኾን (ገነትን መነዳቸው)፡፡ | وَدَانِيَةً عَلَيْهِمْ ظِلاَلُهَا وَذُلِّلَتْ قُطُوفُهَا تَذْلِيلاً |
Wa Yuţāfu `Alayhim Bi'āniyatin Min Fiđđatin Wa 'Akwābin Kānat Qawārīra  | 076-015 በእነርሱም ላይ ከብር በኾኑ ዕቃዎች (ሰሐኖች) የብርጭቆዎች በኾኑ ኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል፡፡ | وَيُطَافُ عَلَيْهِمْ بِآنِيَةٍ مِنْ فِضَّةٍ وَأَكْوَابٍ كَانَتْ قَوَارِيرَ |
Qawārīra Min Fiđđatin Qaddarūhā Taqdīrāan  | 076-016 መለካትን የለኳቸው በኾኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)፡፡ | قَوَارِيرَ مِنْ فِضَّةٍ قَدَّرُوهَا تَقْدِيراً |
Wa Yusqawna Fīhā Ka'sāan Kāna Mizājuhā Zanjabīlāan  | 076-017 በእርሷም መበረዣዋ ዘንጀቢል የኾነችን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ | وَيُسْقَوْنَ فِيهَا كَأْساً كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلاً |
`Aynāan Fīhā Tusammá Salsabīlāan  | 076-018 በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ፡፡ | عَيْناً فِيهَا تُسَمَّى سَلْسَبِيلاً |
Wa Yaţūfu `Alayhim Wildānun Mukhalladūna 'Idhā Ra'aytahum Ĥasibtahum Lu'ulu'uāan Manthūrāan  | 076-019 በእነርሱም ላይ (ባሉበት ኹነታ) የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡ | وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَانٌ مُخَلَّدُونَ إِذَا رَأَيْتَهُمْ حَسِبْتَهُمْ لُؤْلُؤاً مَنثُوراً |
Wa 'Idhā Ra'ayta Thamma Ra'ayta Na`īmāan Wa Mulkāan Kabīrāan  | 076-020 እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ፡፡ | وَإِذَا رَأَيْتَ ثَمَّ رَأَيْتَ نَعِيماً وَمُلْكاً كَبِيراً |
`Āliyahum Thiyābu Sundusin Khuđrun Wa 'Istabraqun Wa Ĥullū 'Asāwira Min Fiđđatin Wa Saqāhum Rabbuhum Sharābāan Ţahūrāan  | 076-021 አረንጓዴዎች የኾኑ የቀጭን ሐር ልብሶችና ወፍራም ሐርም በላያቸው ላይ አልለ፡፡ ከብር የኾኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ፡፡ ጌታቸውም አጥሪ የኾነን መጠጥ ያጠጣቸዋል፡፡ | عَالِيَهُمْ ثِيَابُ سُندُسٍ خُضْرٌ وَإِسْتَبْرَقٌ وَحُلُّوا أَسَاوِرَ مِنْ فِضَّةٍ وَسَقَاهُمْ رَبُّهُمْ شَرَاباً طَهُوراً |
'Inna Hādhā Kāna Lakum Jazā'an Wa Kāna Sa`yukum Mashkūrāan  | 076-022 آ«ይህ በእርግጥ ለእናንተ ዋጋ ኾነ፡፡ ሥራችሁም ምስጉን ኾነ፤آ» (ይባላሉ)፡፡ | إِنَّ هَذَا كَانَ لَكُمْ جَزَاءً وَكَانَ سَعْيُكُمْ مَشْكُوراً |
'Innā Naĥnu Nazzalnā `Alayka Al-Qur'āna Tanzīlāan  | 076-023 እኛ ቁርኣንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው፡፡ | إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ تَنْزِيلاً |
Fāşbir Liĥukmi Rabbika Wa Lā Tuţi` Minhum 'Āthimāan 'Aw Kafūrāan  | 076-024 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ ከእነርሱም ኀጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ፡፡ | فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلاَ تُطِعْ مِنْهُمْ آثِماً أَوْ كَفُوراً |
Wa Adhkur Asma Rabbika Bukratan Wa 'Aşīlāan  | 076-025 የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ፡፡ | وَاذْكُرْ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلاً |
Wa Mina Al-Layli Fāsjud Lahu Wa Sabbiĥhu Laylāan Ţawīlāan  | 076-026 ከሌሊቱም ለእርሱ ስገድ፡፡ በረዢም ሌሊትም አወድሰው፡፡ | وَمِنَ اللَّيْلِ فَاسْجُدْ لَهُ وَسَبِّحْهُ لَيْلاً طَوِيلاً |
'Inna Hā'uulā' Yuĥibbūna Al-`Ājilata Wa Yadharūna Warā'ahum Yawmāan Thaqīlāan  | 076-027 እነዚያ ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ፡፡ ከባድን ቀንም በስተፊታቸው ኾኖ ይተዋሉ፡፡ | إِنَّ هَاؤُلاَء يُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ وَيَذَرُونَ وَرَاءَهُمْ يَوْماً ثَقِيلاً |
Naĥnu Khalaqnāhum Wa Shadadnā 'Asrahum Wa 'Idhā Shi'nā Baddalnā 'Amthālahum Tabdīlāan  | 076-028 እኛ ፈጠርናቸው፡፡ መለያልያቸውንም አጠነከርን፡፡ በሻንም ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን፡፡ | نَحْنُ خَلَقْنَاهُمْ وَشَدَدْنَا أَسْرَهُمْ وَإِذَا شِئْنَا بَدَّلْنَا أَمْثَالَهُمْ تَبْدِيلاً |
'Inna Hadhihi Tadhkiratun Faman Shā'a Attakhadha 'Ilá Rabbihi Sabīlāan  | 076-029 ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ | إِنَّ هَذِهِ تَذْكِرَةٌ فَمَنْ شَاءَ اتَّخَذَ إِلَى رَبِّهِ سَبِيلاً |
Wa Mā Tashā'ūna 'Illā 'An Yashā'a Al-Lahu 'Inna Al-Laha Kāna `Alīmāan Ĥakīmāan  | 076-030 አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡ | وَمَا تَشَاءُونَ إِلاَّ أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيماً حَكِيماً |
Yudkhilu Man Yashā'u Fī Raĥmatihi Wa Až-Žālimīna 'A`adda Lahum `Adhābāan 'Alīmāan  | 076-031 የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባዋል፡፡ በዳዮቹንም (ዝቶባቸዋል)፡፡ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ | يُدْخِلُ مَنْ يَشَاءُ فِي رَحْمَتِهِ وَالظَّالِمِينَ أَعَدَّ لَهُمْ عَذَاباً أَلِيماً |