Yā 'Ayyuhā Al-Muddaththiru  | 074-001 አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ! | يَاأَيُّهَا الْمُدَّثِّرُ |
Qum Fa'andhir  | 074-002 ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡ | قُمْ فَأَنذِرْ |
Wa Rabbaka Fakabbir  | 074-003 ጌታህንም አክብር፡፡ | وَرَبَّكَ فَكَبِّرْ |
Wa Thiyābaka Faţahhir  | 074-004 ልብስህንም አጥራ፡፡ | وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ |
Wa Ar-Rujza Fāhjur  | 074-005 ጣዖትንም ራቅ፡፡ | وَالرُّجْزَ فَاهْجُرْ |
Wa Lā Tamnun Tastakthiru  | 074-006 ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ | وَلاَ تَمْنُنْ تَسْتَكْثِرُ |
Wa Lirabbika Fāşbir  | 074-007 ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡ | وَلِرَبِّكَ فَاصْبِرْ |
Fa'idhā Nuqira Fī An-Nāqūri  | 074-008 በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡ | فَإِذَا نُقِرَ فِي النَّاقُورِ |
Fadhālika Yawma'idhin Yawmun `Asīrun  | 074-009 ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ | فَذَلِكَ يَوْمَئِذٍ يَوْمٌ عَسِيرٌ |
`Alá Al-Kāfirīna Ghayru Yasīrin  | 074-010 በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡ | عَلَى الْكَافِرِينَ غَيْرُ يَسِيرٍ |
Dharnī Wa Man Khalaqtu Waĥīdāan  | 074-011 አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ | ذَرْنِي وَمَنْ خَلَقْتُ وَحِيداً |
Wa Ja`altu Lahu Mālāan Mamdūdāan  | 074-012 ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡ | وَجَعَلْتُ لَهُ مَالاً مَمْدُوداً |
Wa Banīna Shuhūdāan  | 074-013 (በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡ | وَبَنِينَ شُهُوداً |
Wa Mahhadtu Lahu Tamhīdāan  | 074-014 ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡ | وَمَهَّدْتُ لَهُ تَمْهِيداً |
Thumma Yaţma`u 'An 'Azīda  | 074-015 ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡ | ثُمَّ يَطْمَعُ أَنْ أَزِيدَ |
Kallā 'Innahu Kāna Li'yātinā `Anīdāan  | 074-016 ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡ | كَلاَّ إِنَّهُ كَانَ لِأيَاتِنَا عَنِيداً |
Sa'urhiquhu Şa`ūdāan  | 074-017 በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡ | سَأُرْهِقُهُ صَعُوداً |
'Innahu Fakkara Wa Qaddara  | 074-018 እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡ | إِنَّهُ فَكَّرَ وَقَدَّرَ |
Faqutila Kayfa Qaddara  | 074-019 ተረገመም፤ እንዴት ገመተ! | فَقُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ |
Thumma Qutila Kayfa Qaddara  | 074-020 ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ! | ثُمَّ قُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ |
Thumma Nažara  | 074-021 ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡ | ثُمَّ نَظَرَ |
Thumma `Abasa Wa Basara  | 074-022 ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡ | ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ |
Thumma 'Adbara Wa Astakbara  | 074-023 ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡ | ثُمَّ أَدْبَرَ وَاسْتَكْبَرَ |
Faqāla 'In Hādhā 'Illā Siĥrun Yu'utharu  | 074-024 አለም آ«ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ | فَقَالَ إِنْ هَذَا إِلاَّ سِحْرٌ يُؤْثَرُ |
'In Hādhā 'Illā Qawlu Al-Bashari  | 074-025 آ«ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡آ» | إِنْ هَذَا إِلاَّ قَوْلُ الْبَشَرِ |
Sa'uşlīhi Saqara  | 074-026 በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡ | سَأُصْلِيهِ سَقَرَ |
Wa Mā 'Adrāka Mā Saqaru  | 074-027 ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? | وَمَا أَدْرَاكَ مَا سَقَرُ |
Lā Tubqī Wa Lā Tadharu  | 074-028 (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡ | لاَ تُبْقِي وَلاَ تَذَرُ |
Lawwāĥatun Lilbashari  | 074-029 ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡ | لَوَّاحَةٌ لِلْبَشَرِ |
`Alayhā Tis`ata `Ashara  | 074-030 በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡ | عَلَيْهَا تِسْعَةَ عَشَرَ |
Wa Mā Ja`alnā 'Aşĥāba An-Nāri 'Illā Malā'ikatan Wa Mā Ja`alnā `Iddatahum 'Illā Fitnatan Lilladhīna Kafarū Liyastayqina Al-Ladhīna 'Ūtū Al-Kitāba Wa Yazdāda Al-Ladhīna 'Āmanū 'Īmānāan Wa Lā Yartāba Al-Ladhīna 'Ūtū Al-Kitāba Wa Al-Mu'uminūna Wa Liyaqūla Al-Ladhīna Fī Qulūbihim Marađun Wa Al-Kāfirūna Mādhā 'Arāda Al-Lahu Bihadhā Mathalāan Kadhālika Yuđillu Al-Lahu Man Yashā'u Wa Yahdī Man Yashā'u Wa Mā Ya`lamu Junūda Rabbika 'Illā Huwa Wa Mā Hiya 'Illā Dhikrá Lilbashari  | 074-031 የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅ&
|
Kallā Wa Al-Qamari  | 074-032 (ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡ | كَلاَّ وَالْقَمَرِ |
Wa Al-Layli 'Idh 'Adbara  | 074-033 በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡ | وَاللَّيْلِ إِذْ أَدْبَرَ |
Wa Aş-Şubĥi 'Idhā 'Asfara  | 074-034 በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡ | وَالصُّبْحِ إِذَا أَسْفَرَ |
'Innahā La'iĥdá Al-Kubari  | 074-035 እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡ | إِنَّهَا لَإِحْدَى الْكُبَرِ |
Nadhīrāan Lilbashari  | 074-036 ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡ | نَذِيراً لِلْبَشَرِ |
Liman Shā'a Minkum 'An Yataqaddama 'Aw Yata'akhkhara  | 074-037 ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡ | لِمَنْ شَاءَ مِنْكُمْ أَنْ يَتَقَدَّمَ أَوْ يَتَأَخَّرَ |
Kullu Nafsin Bimā Kasabat Rahīnahun  | 074-038 ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡ | كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ |
'Illā 'Aşĥāba Al-Yamīni  | 074-039 የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ | إِلاَّ أَصْحَابَ الْيَمِينِ |
Fī Jannātin Yatasā'alūna  | 074-040 (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ | فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ |
`Ani Al-Mujrimīna  | 074-041 ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ | عَنِ الْمُجْرِمِينَ |
Mā Salakakum Fī Saqara  | 074-042 (ይሏቸዋልም) آ«በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?آ» | مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ |
Qālū Lam Naku Mina Al-Muşallīna  | 074-043 (እነርሱም) ይላሉ آ«ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ | قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ |
Wa Lam Naku Nuţ`imu Al-Miskīna  | 074-044 آ«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡ | وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ |
Wa Kunnā Nakhūđu Ma`a Al-Khā'iđīna  | 074-045 آ«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ | وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ الْخَائِضِينَ |
Wa Kunnā Nukadhdhibu Biyawmi Ad-Dīni  | 074-046 آ«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ | وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ الدِّينِ |
Ĥattá 'Atānā Al-Yaqīnu  | 074-047 آ«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡آ» | حَتَّى أَتَانَا الْيَقِينُ |
Famā Tanfa`uhum Shafā`atu Ash-Shāfi`īna  | 074-048 የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ | فَمَا تَنْفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ |
Famā Lahum `Ani At-Tadhkirati Mu`riđīna  | 074-049 ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው? | فَمَا لَهُمْ عَنِ التَّذْكِرَةِ مُعْرِضِينَ |
Ka'annahum Ĥumurun Mustanfirahun  | 074-050 እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡ | كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُسْتَنْفِرَةٌ |
Farrat Min Qaswarahin  | 074-051 ከዐንበሳ የሸሹ፡፡ | فَرَّتْ مِنْ قَسْوَرَةٍ |
Bal Yurīdu Kullu Amri'in Minhum 'An Yu'utá Şuĥufāan Munashsharahan  | 074-052 ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡ | بَلْ يُرِيدُ كُلُّ امْرِئٍ مِنْهُمْ أَنْ يُؤْتَى صُحُفاً مُنَشَّرَةً |
Kallā Bal Lā Yakhāfūna Al-'Ākhiraha  | 074-053 ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡ | كَلاَّ بَلْ لاَ يَخَافُونَ الآخِرَةَ |
Kallā 'Innahu Tadhkirahun  | 074-054 ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡ | كَلاَّ إِنَّهُ تَذْكِرَةٌ |
Faman Shā'a Dhakarahu  | 074-055 ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡ | فَمَنْ شَاءَ ذَكَرَهُ |
Wa Mā Yadhkurūna 'Illā 'An Yashā'a Al-Lahu Huwa 'Ahlu At-Taqwá Wa 'Ahlu Al-Maghfirahi  | 074-056 /p> | وَمَا يَذْكُرُونَ إِلاَّ أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ هُوَ أَهْلُ التَّقْوَى وَأَهْلُ الْمَغْفِرَةِ |