Sa'ala Sā'ilun Bi`adhābin Wāqi`in  | 070-001 ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ | سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ |
Lilkāfiryna Laysa Lahu Dāfi`un  | 070-002 በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ | لِلْكَافِرينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ |
Mina Al-Lahi Dhī Al-Ma`āriji  | 070-003 የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ | مِنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ |
Ta`ruju Al-Malā'ikatu Wa Ar-Rūĥu 'Ilayhi Fī Yawmin Kāna Miqdāruhu Khamsīna 'Alfa Sanahin  | 070-004 መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ | تَعْرُجُ الْمَلاَئِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ |
Fāşbir Şabrāan Jamīlāan  | 070-005 መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ | فَاصْبِرْ صَبْراً جَمِيلاً |
'Innahum Yarawnahu Ba`īdāan  | 070-006 እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ | إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيداً |
Wa Narāhu Qarībāan  | 070-007 እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ | وَنَرَاهُ قَرِيباً |
Yawma Takūnu As-Samā'u Kālmuhli  | 070-008 ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ | يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ |
Wa Takūnu Al-Jibālu Kāl`ihni  | 070-009 ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ | وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ |
Wa Lā Yas'alu Ĥamīmun Ĥamīmāan  | 070-010 ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ | وَلاَ يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيماً |
Yubaşşarūnahum Yawaddu Al-Mujrimu Law Yaftadī Min `Adhābi Yawmi'idhin Bibanīhi  | 070-011 (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ | يُبَصَّرُونَهُمْ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ |
Wa Şāĥibatihi Wa 'Akhīhi  | 070-012 በሚስቱም በወንድሙም፡፡ | وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ |
Wa Faşīlatihi Allatī Tu'uwyhi  | 070-013 በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ | وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْويهِ |
Wa Man Fī Al-'Arđi Jamī`āan Thumma Yunjīhi  | 070-014 በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ | وَمَنْ فِي الأَرْضِ جَمِيعاً ثُمَّ يُنجِيهِ |
Kallā 'Innahā Lažá  | 070-015 ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ | كَلاَّ إِنَّهَا لَظَى |
Nazzā`atan Lilshshawá  | 070-016 የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ | نَزَّاعَةً لِلشَّوَى |
Tad`ū Man 'Adbara Wa Tawallá  | 070-017 (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ | تَدْعُوا مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّى |
Wa Jama`a Fa'aw`á  | 070-018 ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ | وَجَمَعَ فَأَوْعَى |
'Inna Al-'Insāna Khuliqa Halū`āan  | 070-019 ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ | إِنَّ الإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعاً |
'Idhā Massahu Ash-Sharru Jazū`āan  | 070-020 ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ | إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعاً |
Wa 'Idhā Massahu Al-Khayru Manū`āan  | 070-021 መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ | وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعاً |
'Illā Al-Muşallīna  | 070-022 ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ | إِلاَّ الْمُصَلِّينَ |
Al-Ladhīna Hum `Alá Şalātihim Dā'imūna  | 070-023 እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ | الَّذِينَ هُمْ عَلَى صَلاَتِهِمْ دَائِمُونَ |
Wa Al-Ladhīna Fī 'Amwālihim Ĥaqqun Ma`lūmun  | 070-024 እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ | وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَعْلُومٌ |
Lilssā'ili Wa Al-Maĥrūmi  | 070-025 ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ | لِلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ |
Wa Al-Ladhīna Yuşaddiqūna Biyawmi Ad-Dīni  | 070-026 እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ | وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ |
Wa Al-Ladhīna Hum Min `Adhābi Rabbihim Mushfiqūna  | 070-027 እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ | وَالَّذِينَ هُمْ مِنْ عَذَابِ رَبِّهِمْ مُشْفِقُونَ |
'Inna `Adhāba Rabbihim Ghayru Ma'mūnin  | 070-028 የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ | إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ |
Wa Al-Ladhīna Hum Lifurūjihim Ĥāfižūna  | 070-029 እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ | وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ |
'Illā `Alá 'Azwājihim 'Aw Mā Malakat 'Aymānuhum Fa'innahum Ghayru Malūmīna  | 070-030 በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ | إِلاَّ عَلَى أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ |
Famani Abtaghá Warā'a Dhālika Fa'ūlā'ika Humu Al-`Ādūna  | 070-031 ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ | فَمَنِ ابْتَغَى وَرَاءَ ذَلِكَ فَأُوْلَائِكَ هُمُ الْعَادُونَ |
Wa Al-Ladhīna Hum Li'mānātihim Wa `Ahdihim Rā`ūna  | 070-032 እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ | وَالَّذِينَ هُمْ لِأمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ |
Wa Al-Ladhīna Hum Bishahādātihim Qā'imūna  | 070-033 እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ | وَالَّذِينَ هُمْ بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ |
Wa Al-Ladhīna Hum `Alá Şalātihim Yuĥāfižūna  | 070-034 እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ | وَالَّذِينَ هُمْ عَلَى صَلاَتِهِمْ يُحَافِظُونَ |
'Ūlā'ika Fī Jannātin Mukramūna  | 070-035 እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ | أُوْلَائِكَ فِي جَنَّاتٍ مُكْرَمُونَ |
Famāli Al-Ladhīna Kafarū Qibalaka Muhţi`īna  | 070-036 ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? | فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ |
`Ani Al-Yamīni Wa `Ani Ash-Shimāli `Izīna  | 070-037 ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ | عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ |
'Ayaţma`u Kullu Amri'in Minhum 'An Yudkhala Jannata Na`īmin  | 070-038 ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? | أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِنْهُمْ أَنْ يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ |
Kallā 'Innā Khalaqnāhum Mimmā Ya`lamūna  | 070-039 ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ | كَلاَّ إِنَّا خَلَقْنَاهُمْ مِمَّا يَعْلَمُونَ |
Falā 'Uqsimu Birabbi Al-Mashāriqi Wa Al-Maghāribi 'Innā Laqādirūna  | 070-040 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ | فَلاَ أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ |
`Alá 'An Nubaddila Khayrāan Minhum Wa Mā Naĥnu Bimasbūqīna  | 070-041 ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ | عَلَى أَنْ نُبَدِّلَ خَيْراً مِنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ |
Fadharhum Yakhūđū Wa Yal`abū Ĥattá Yulāqū Yawmahumu Al-Ladhī Yū`adūna  | 070-042 ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ | فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّى يُلاَقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ |
Yawma Yakhrujūna Mina Al-'Ajdāthi Sirā`āan Ka'annahum 'Ilá Nuşubin Yūfiđūna  | 070-043 ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ | يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الأَجْدَاثِ سِرَاعاً كَأَنَّهُمْ إِلَى نُصُبٍ يُوفِضُونَ |
Khāshi`atan 'Abşāruhum Tarhaquhum Dhillatun Dhālika Al-Yawmu Al-Ladhī Kānū Yū`adūna  | 070-044 ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ | خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ذَلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ |