'Innā 'Arsalnā Nūĥāan 'Ilá Qawmihi 'An 'Andhir Qawmaka Min Qabli 'An Ya'tiyahum `Adhābun 'Alīmun  | 071-001 እኛ ኑሕን آ«ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡آ» | إِنَّا أَرْسَلْنَا نُوحاً إِلَى قَوْمِهِ أَنْ أَنذِرْ قَوْمَكَ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ |
Qāla Yā Qawmi 'Innī Lakum Nadhīrun Mubīnun  | 071-002 (እርሱም) አለ آ«ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡ | قَالَ يَاقَوْمِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ مُبِينٌ |
'Ani A`budū Al-Laha Wa Attaqūhu Wa 'Aţī`ūni  | 071-003 آ«አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡ | أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ |
Yaghfir Lakum Min Dhunūbikum Wa Yu'uakhkhirkum 'Ilá 'Ajalin Musammáan 'Inna 'Ajala Al-Lahi 'Idhā Jā'a Lā Yu'uakhkharu Law Kuntum Ta`lamūna  | 071-004 آ«ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡آ» | يَغْفِرْ لَكُمْ مِنْ ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرْكُمْ إِلَى أَجَلٍ مُسَمّىًاإِنَّ أَجَلَ اللَّهِ إِذَا جَاءَ لاَ يُؤَخَّرُ لَوْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ |
Qāla Rabbi 'Innī Da`awtu Qawmī Laylāan Wa Nahārāan  | 071-005 (ስለ ተቃወሙትም) آ«አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡ | قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوْتُ قَوْمِي لَيْلاً وَنَهَاراً |
Falam Yazid/hum Du`ā'ī 'Illā Firārāan  | 071-006 آ«ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡ | فَلَمْ يَزِدْهُمْ دُعَائِي إِلاَّ فِرَاراً |
Wa 'Innī Kullamā Da`awtuhum Litaghfira Lahum Ja`alū 'Aşābi`ahum Fī 'Ādhānihim Wa Astaghshaw Thiyābahum Wa 'Aşarrū Wa Astakbarū Astikbārāan  | 071-007 آ«እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡ | وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوْتُهُمْ لِتَغْفِرَ لَهُمْ جَعَلُوا أَصَابِعَهُمْ فِي آذَانِهِمْ وَاسْتَغْشَوْا ثِيَابَهُمْ وَأَصَرُّوا وَاسْتَكْبَرُوا اسْتِكْبَاراً |
Thumma 'Innī Da`awtuhum Jihārāan  | 071-008 آ«ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡ | ثُمَّ إِنِّي دَعَوْتُهُمْ جِهَاراً |
Thumma 'Innī 'A`lantu Lahum Wa 'Asrartu Lahum 'Isrārāan  | 071-009 آ«ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ | ثُمَّ إِنِّي أَعْلَنتُ لَهُمْ وَأَسْرَرْتُ لَهُمْ إِسْرَاراً |
Faqultu Astaghfirū Rabbakum 'Innahu Kāna Ghaffārāan  | 071-010 آ«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡ | فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّاراً |
Yursili As-Samā'a `Alaykum Midrārāan  | 071-011 آ«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡ | يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُمْ مِدْرَاراً |
Wa Yumdidkum Bi'amwālin Wa Banīna Wa Yaj`al Lakum Jannātin Wa Yaj`al Lakum 'Anhārāan  | 071-012 آ«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡آ» | وَيُمْدِدْكُمْ بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَلْ لَكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَلْ لَكُمْ أَنْهَاراً |
Mā Lakum Lā Tarjūna Lillahi Waqārāan  | 071-013 ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ? | مَا لَكُمْ لاَ تَرْجُونَ لِلَّهِ وَقَاراً |
Wa Qad Khalaqakum 'Aţwārāan  | 071-014 በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡ | وَقَدْ خَلَقَكُمْ أَطْوَاراً |
'Alam Taraw Kayfa Khalaqa Al-Lahu Sab`a Samāwātin Ţibāqāan  | 071-015 አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን? | أَلَمْ تَرَوْا كَيْفَ خَلَقَ اللَّهُ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقاً |
Wa Ja`ala Al-Qamara Fīhinna Nūrāan Wa Ja`ala Ash-Shamsa Sirājāan  | 071-016 በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡ | وَجَعَلَ الْقَمَرَ فِيهِنَّ نُوراً وَجَعَلَ الشَّمْسَ سِرَاجاً |
Wa Allāhu 'Anbatakum Mina Al-'Arđi Nabātāan  | 071-017 አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡ | وَاللَّهُ أَنْبَتَكُمْ مِنَ الأَرْضِ نَبَاتاً |
Thumma Yu`īdukum Fīhā Wa Yukhrijukum 'Ikhrājāan  | 071-018 ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡ | ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجاً |
Wa Allāhu Ja`ala Lakumu Al-'Arđa Bisāţāan  | 071-019 አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡ | وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الأَرْضَ بِسَاطاً |
Litaslukū Minhā Subulāan Fijājāan  | 071-020 ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡ | لِتَسْلُكُوا مِنْهَا سُبُلاً فِجَاجاً |
Qāla Nūĥun Rabbi 'Innahum `Aşawnī Wa Attaba`ū Man Lam Yazid/hu Māluhu Wa Waladuhu 'Illā Khasārāan  | 071-021 ኑሕ አለ፡- آ«ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡ | قَالَ نُوحٌ رَبِّ إِنَّهُمْ عَصَوْنِي وَاتَّبَعُوا مَنْ لَمْ يَزِدْهُ مَالُهُ وَوَلَدُهُ إِلاَّ خَسَاراً |
Wa Makarū Makrāan Kubbārāan  | 071-022 آ«ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎችآ» (ተከተሉ)፡፡ | وَمَكَرُوا مَكْراً كُبَّاراً |
Wa Qālū Lā Tadharunna 'Ālihatakum Wa Lā Tadharunna Waddāan Wa Lā Suwā`āan Wa Lā Yaghūtha Wa Ya`ūqa Wa Nasrāan  | 071-023 አሉም آ«አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡ | وَقَالُوا لاَ تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلاَ تَذَرُنَّ وَدّاً وَلاَ سُوَاعاً وَلاَ يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْراً |
Wa Qad 'Ađallū Kathīrāan Wa Lā Tazidi Až-Žālimīna 'Illā Đalālāan  | 071-024 آ«በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸውآ» (አለ)፡፡ | وَقَدْ أَضَلُّوا كَثِيراً وَلاَ تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلاَّ ضَلاَلاً |
Mimmā Khaţī'ātihim 'Ughriqū Fa'udkhilū Nārāan Falam Yajidū Lahum Min Dūni Al-Lahi 'Anşārāan  | 071-025 በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡ | مِمَّا خَطِيئَاتِهِمْ أُغْرِقُوا فَأُدْخِلُوا نَاراً فَلَمْ يَجِدُوا لَهُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَنْصَاراً |
Wa Qāla Nūĥun Rabbi Lā Tadhar `Alá Al-'Arđi Mina Al-Kāfirīna Dayyārāan  | 071-026 ኑሕም አለ آ«ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡ | وَقَالَ نُوحٌ رَبِّ لاَ تَذَرْ عَلَى الأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّاراً |
'Innaka 'In Tadharhum Yuđillū `Ibādaka Wa Lā Yalidū 'Illā Fājirāan Kaffārāan  | 071-027 آ«አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡ | إِنَّكَ إِنْ تَذَرْهُمْ يُضِلُّوا عِبَادَكَ وَلاَ يَلِدُوا إِلاَّ فَاجِراً كَفَّاراً |
Rabbi Aghfir Lī Wa Liwālidayya Wa Liman Dakhala Baytiya Mu'umināan Wa Lilmu'uminīna Wa Al-Mu'umināti Wa Lā Tazidi Až-Žālimīna 'Illā Tabārāan  | 071-028 آ«ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤آ» (አለ)፡፡ | رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ وَلِمَنْ دَخَلَ بَيْتِيَ مُؤْمِناً وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَلاَ تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلاَّ تَبَاراً |