Al-Ĥāqqahu  | 069-001 እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡ | الْحَاقَّةُ |
Mā Al-Ĥāqqahu  | 069-002 አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት! | مَا الْحَاقَّةُ |
Wa Mā 'Adrāka Mā Al-Ĥāqqahu  | 069-003 አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? | وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْحَاقَّةُ |
Kadhdhabat Thamūdu Wa `Ādun Bil-Qāri`ahi  | 069-004 ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡ | كَذَّبَتْ ثَمُودُ وَعَادٌ بِالْقَارِعَةِ |
Fa'ammā Thamūdu Fa'uhlikū Biţ-Ţāghiyahi  | 069-005 ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡ | فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهْلِكُوا بِالطَّاغِيَةِ |
Wa 'Ammā `Ādun Fa'uhlikū Birīĥin Şarşarin `Ātiyahin  | 069-006 ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡ | وَأَمَّا عَادٌ فَأُهْلِكُوا بِرِيحٍ صَرْصَرٍ عَاتِيَةٍ |
Sakhkharahā `Alayhim Sab`a Layālin Wa Thamāniyata 'Ayyāmin Ĥusūmāan Fatará Al-Qawma Fīhā Şar`á Ka'annahum 'A`jāzu Nakhlin Khāwiyahin  | 069-007 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡ | سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍ وَثَمَانِيَةَ أَيَّامٍ حُسُوماً فَتَرَى الْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَى كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍ |
Fahal Tará Lahum Min Bāqiyahin  | 069-008 ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን? | فَهَلْ تَرَى لَهُمْ مِنْ بَاقِيَةٍ |
Wa Jā'a Fir`awnu Wa Man Qablahu Wa Al-Mu'utafikātu Bil-Khāţi'ahi  | 069-009 ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡ | وَجَاءَ فِرْعَوْنُ وَمَنْ قَبْلَهُ وَالْمُؤْتَفِكَاتُ بِالْخَاطِئَةِ |
Fa`aşaw Rasūla Rabbihim Fa'akhadhahum 'Akhdhatan Rābiyahan  | 069-010 የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡ | فَعَصَوْا رَسُولَ رَبِّهِمْ فَأَخَذَهُمْ أَخْذَةً رَابِيَةً |
'Innā Lammā Ţaghá Al-Mā'u Ĥamalnākum Fī Al-Jāriyahi  | 069-011 እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡ | إِنَّا لَمَّا طَغَى الْمَاءُ حَمَلْنَاكُمْ فِي الْجَارِيَةِ |
Linaj`alahā Lakum Tadhkiratan Wa Ta`iyahā 'Udhunun Wā`iyahun  | 069-012 ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡ | لِنَجْعَلَهَا لَكُمْ تَذْكِرَةً وَتَعِيَهَا أُذُنٌ وَاعِيَةٌ |
Fa'idhā Nufikha Fī Aş-Şūri Nafkhatun Wāĥidahun  | 069-013 በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡ | فَإِذَا نُفِخَ فِي الصُّورِ نَفْخَةٌ وَاحِدَةٌ |
Wa Ĥumilati Al-'Arđu Wa Al-Jibālu Fadukkatā Dakkatan Wāĥidahan  | 069-014 ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡ | وَحُمِلَتِ الأَرْضُ وَالْجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةً وَاحِدَةً |
Fayawma'idhin Waqa`ati Al-Wāqi`ahu  | 069-015 በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡ | فَيَوْمَئِذٍ وَقَعَتِ الْوَاقِعَةُ |
Wa Anshaqqati As-Samā'u Fahiya Yawma'idhin Wa Ahiyahun  | 069-016 ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡ | وَانشَقَّتِ السَّمَاءُ فَهِيَ يَوْمَئِذٍ وَاهِيَةٌ |
Wa Al-Malaku `Alá 'Arjā'ihā Wa Yaĥmilu `Arsha Rabbika Fawqahum Yawma'idhin Thamāniyahun  | 069-017 መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡ | وَالْمَلَكُ عَلَى أَرْجَائِهَا وَيَحْمِلُ عَرْشَ رَبِّكَ فَوْقَهُمْ يَوْمَئِذٍ ثَمَانِيَةٌ |
Yawma'idhin Tu`rađūna Lā Takhfá Minkum Khāfiyahun  | 069-018 በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡ | يَوْمَئِذٍ تُعْرَضُونَ لاَ تَخْفَى مِنْكُمْ خَافِيَةٌ |
Fa'ammā Man 'Ūtiya Kitābahu Biyamīnihi Fayaqūlu Hā'uum Aqra'ū Kitābī  | 069-019 መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) آ«እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡآ» ይላል፡፡ | فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمْ اقْرَءُوا كِتَابِي |
'Innī Žanantu 'Annī Mulāqin Ĥisābiyah  | 069-020 آ«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤آ» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡ | إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلاَقٍ حِسَابِيَه |
Fahuwa Fī `Īshatin Rāđiyahin  | 069-021 እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡ | فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَاضِيَةٍ |
Fī Jannatin `Āliyahin  | 069-022 በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡ | فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ |
Quţūfuhā Dāniyahun  | 069-023 ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡ | قُطُوفُهَا دَانِيَةٌ |
Kulū Wa Ashrabū Hanī'āan Bimā 'Aslaftum Fī Al-'Ayyāmi Al-Khāliyahi  | 069-024 በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡ | كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئاً بِمَا أَسْلَفْتُمْ فِي الأَيَّامِ الْخَالِيَةِ |
Wa 'Ammā Man 'Ūtiya Kitābahu Bishimālihi Fayaqūlu Yā Laytanī Lam 'Ūta Kitābīh  | 069-025 መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ آ«ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁآ» ይላል፡፡ | وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيهْ |
Wa Lam 'Adri Mā Ĥisābīh  | 069-026 آ«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡ | وَلَمْ أَدْرِ مَا حِسَابِيهْ |
Yā Laytahā Kānati Al-Qāđiyaha  | 069-027 آ«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡ | يَا لَيْتَهَا كَانَتِ الْقَاضِيَةَ |
Mā 'Aghná `Annī Mālīh  | 069-028 آ«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡ | مَا أَغْنَى عَنِّي مَالِيهْ |
Halaka `Annī Sulţānīh  | 069-029 آ«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋآ» (ይላል)፡፡ | هَلَكَ عَنِّي سُلْطَانِيهْ |
Khudhūhu Faghullūhu  | 069-030 آ«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡ | خُذُوهُ فَغُلُّوهُ |
Thumma Al-Jaĥīma Şallūhu  | 069-031 آ«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡ | ثُمَّ الْجَحِيمَ صَلُّوهُ |
Thumma Fī Silsilatin Dhar`uhā Sab`ūna Dhirā`āan Fāslukūhu  | 069-032 آ«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡آ» | ثُمَّ فِي سِلْسِلَةٍ ذَرْعُهَا سَبْعُونَ ذِرَاعاً فَاسْلُكُوهُ |
'Innahu Kāna Lā Yu'uminu Bil-Lahi Al-`Ažīmi  | 069-033 እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡ | إِنَّهُ كَانَ لاَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ الْعَظِيمِ |
Wa Lā Yaĥuđđu `Alá Ţa`āmi Al-Miskīni  | 069-034 ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡ | وَلاَ يَحُضُّ عَلَى طَعَامِ الْمِسْكِينِ |
Falaysa Lahu Al-Yawma Hāhunā Ĥamīmun  | 069-035 ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡ | فَلَيْسَ لَهُ الْيَوْمَ هَاهُنَا حَمِيمٌ |
Wa Lā Ţa`āmun 'Illā Min Ghislīnin  | 069-036 ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡ | وَلاَ طَعَامٌ إِلاَّ مِنْ غِسْلِينٍ |
Lā Ya'kuluhu 'Illā Al-Khāţi'ūna  | 069-037 ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡ | لاَ يَأْكُلُهُ إِلاَّ الْخَاطِئُونَ |
Falā 'Uqsimu Bimā Tubşirūna  | 069-038 በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡ | فَلاَ أُقْسِمُ بِمَا تُبْصِرُونَ |
Wa Mā Lā Tubşirūna  | 069-039 በማታዩትም ነገር፡፡ | وَمَا لاَ تُبْصِرُونَ |
'Innahu Laqawlu Rasūlin Karīmin  | 069-040 እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡ | إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ |
Wa Mā Huwa Biqawli Shā`irin Qalīlāan Mā Tu'uminūna  | 069-041 እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡ | وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَاعِرٍ قَلِيلاً مَا تُؤْمِنُونَ |
Wa Lā Biqawli Kāhinin Qalīlāan Mā Tadhakkarūna  | 069-042 የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡ | وَلاَ بِقَوْلِ كَاهِنٍ قَلِيلاً مَا تَذَكَّرُونَ |
Tanzīlun Min Rabbi Al-`Ālamīna  | 069-043 ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ | تَنزِيلٌ مِنْ رَبِّ الْعَالَمِينَ |
Wa Law Taqawwala `Alaynā Ba`đa Al-'Aqāwīli  | 069-044 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤ | وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ الأَقَاوِيلِ |
La'akhadhnā Minhu Bil-Yamīni  | 069-045 በኀይል በያዝነው ነበር፡፡ | لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِالْيَمِينِ |
Thumma Laqaţa`nā Minhu Al-Watīna  | 069-046 ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡ | ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ الْوَتِينَ |
Famā Minkum Min 'Aĥadin `Anhu Ĥājizīna  | 069-047 ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡ | فَمَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ عَنْهُ حَاجِزِينَ |
Wa 'Innahu Latadhkiratun Lilmuttaqīna  | 069-048 እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡ | وَإِنَّهُ لَتَذْكِرَةٌ لِلْمُتَّقِينَ |
Wa 'Innā Lana`lamu 'Anna Minkum Mukadhdhibīna  | 069-049 እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ | وَإِنَّا لَنَعْلَمُ أَنَّ مِنْكُمْ مُكَذِّبِينَ |
Wa 'Innahu Laĥasratun `Alá Al-Kāfirīna  | 069-050 እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡ | وَإِنَّهُ لَحَسْرَةٌ عَلَى الْكَافِرِينَ |
Wa 'Innahu Laĥaqqu Al-Yaqīni  | 069-051 እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ | وَإِنَّهُ لَحَقُّ الْيَقِينِ |
Fasabbiĥ Biāsmi Rabbika Al-`Ažīmi  | 069-052 የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡ | فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ |