68) Sūrat Al-Qalam

Printed format

68) سُورَة القَلَم

n Wa Al-Qalami Wa Mā Yasţurūna 068-001 ነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡ نُون وَا‍لْقَلَمِ وَمَا يَسْطُر‍ُو‍نَ
Mā 'Anta Bini`mati Rabbika Bimajnūnin 068-002 አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡ مَ‍‍ا‍ أَ‍ن‍‍ْتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَ‍‍ج‍‍ْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٍ
Wa 'Inna Laka La'ajrāan Ghayra Mamnūnin 068-003 ላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡ وَإِ‍نّ‍‍َ لَكَ لَأَ‍ج‍‍ْراً غَيْرَ مَمْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٍ
Wa 'Innaka La`alá Khuluqin `Ažīmin 068-004 አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡ وَإِ‍نّ‍‍َكَ لَعَلى خُلُقٍ عَظ‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Fasatubşiru Wa Yubşirūna 068-005 ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡ فَسَتُ‍‍ب‍‍ْصِ‍‍ر‍ُ وَيُ‍‍ب‍‍ْصِر‍ُو‍نَ
Bi'ayyyikumu Al-Maftūnu 068-006 ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡ بِأَيّيِكُمُ ا‍لْمَفْت‍‍ُ‍و‍نُ
'Inna Rabbaka Huwa 'A`lamu Biman Đalla `An Sabīlihi Wa Huwa 'A`lamu Bil-Muhtadīna 068-007 ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَ‍‍ن‍ْ ضَلَّ عَ‍‍ن‍ْ سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِ‍‍ا‍لْمُهْتَد‍ِي‍نَ
Falā Tuţi`i Al-Mukadhdhibīna 068-008 ለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡ فَلاَ تُطِعِ ا‍لْمُكَذِّب‍‍ِ‍ي‍نَ
Wa Ddū Law Tud/hinu Fayud/hinūna 068-009 ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡ وَدُّوا‍ لَوْ تُ‍‍د‍‍ْهِنُ فَيُ‍‍د‍‍ْهِن‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Lā Tuţi` Kulla Ĥallāfin Mahīnin 068-010 ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡ وَلاَ تُطِعْ كُلَّ حَلاَّف‍‍‍ٍ مَه‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٍ
Hammāzin Mashshā'in Binamīmin 068-011 ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡ هَ‍‍م‍ّ‍‍َ‍ا‍ز‍ٍ مَشّ‍‍َ‍ا‍ء‍ٍ بِنَم‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
Mannā`in Lilkhayri Mu`tadin 'Athīmin 068-012 ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤ مَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ع‍‍‍ٍ لِلْخَيْ‍‍ر‍ِ مُعْتَدٍ أَث‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
`Utullin Ba`da Dhālika Zanīmin 068-013 ልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡ عُتُلّ‍‍‍ٍ بَعْدَ ذَلِكَ زَن‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٍ
'An Kāna Dhā Mālin Wa Banīna 068-014 የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡ أَ‍ن‍ْ ك‍‍َ‍ا‍نَ ذَا م‍‍َ‍ا‍ل‍‍‍ٍ وَبَن‍‍ِ‍ي‍نَ
'Idhā Tutlá `Alayhi 'Āyātunā Qāla 'Asāţīru Al-'Awwalīna 068-015 በእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ آ«የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸውآ» ይላል፡፡ إِذَا تُتْلَى عَلَيْهِ آيَاتُنَا ق‍‍َ‍ا‍لَ أَسَاط‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ ا‍لأَوَّل‍‍ِ‍ي‍نَ
Sanasimuhu `Alá Al-Khurţūmi 068-016 በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡ سَنَسِمُهُ عَلَى ا‍لْخُرْط‍‍ُ‍و‍مِ
'Innā Balawnāhum Kamā Balawnā 'Aşĥāba Al-Jannati 'Idh 'Aqsamū Layaşrimunnahā Muşbiĥīna 068-017 እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡ إِ‍نّ‍‍َا بَلَوْنَاهُمْ كَمَا بَلَوْنَ‍‍ا‍ أَصْح‍‍َ‍ا‍بَ ا‍لْجَ‍‍ن‍ّ‍‍َةِ إِذْ أَ‍ق‍‍ْسَمُو‍‍ا‍ لَيَصْ‍‍ر‍‍ِمُ‍‍ن‍ّ‍‍َهَا مُصْبِح‍‍ِ‍ي‍نَ
Wa Lā Yastathnūna 068-018 (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡ وَلاَ يَسْتَثْن‍‍ُ‍و‍نَ
Faţāfa `Alayhā Ţā'ifun Min Rabbika Wa Hum Nā'imūna 068-019 እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡ فَط‍‍َ‍ا‍فَ عَلَيْهَا ط‍‍َ‍ا‍ئِف‍‍‍ٌ مِ‍‍ن‍ْ رَبِّكَ وَهُمْ ن‍‍َ‍ا‍ئِم‍‍ُ‍و‍نَ
Fa'aşbaĥat Kālşşarīmi 068-020 እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡ فَأَصْبَحَتْ كَال‍صَّ‍‍ر‍‍ِي‍مِ
Fatanādaw Muşbiĥīna 068-021 ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡ فَتَنَادَوا مُصْبِح‍‍ِ‍ي‍نَ
'Ani Aghdū `Alá Ĥarthikum 'In Kuntum Şārimīna 068-022 آ«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱآ» በማለት፡፡ أَنِ ا‍غْدُوا‍ عَلَى حَرْثِكُمْ إِ‍ن‍ْ كُ‍‍ن‍تُمْ صَا‍ر‍‍ِم‍‍ِ‍ي‍نَ
nţalaqū Wa Hum Yatakhāfatūna 068-023 እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡ فَان‍طَلَقُو‍‍ا‍ وَهُمْ يَتَخَافَت‍‍ُ‍و‍نَ
'An Lā Yadkhulannahā Al-Yawma `Alaykum Miskīnun 068-024 ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡ أَ‍ن‍ْ لاَ يَ‍‍د‍‍ْخُلَ‍‍ن‍ّ‍‍َهَا ا‍لْيَوْمَ عَلَيْكُ‍‍م‍ْ مِسْك‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٌ
Waghadaw `Alá Ĥardin Qādirīna 068-025 (ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡ وَغَدَوْا عَلَى حَرْد‍ٍ قَادِ‍ر‍‍ِي‍نَ
Falammā Ra'awhā Qālū 'Innā Lađāllūna 068-026 (ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ آ«እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነንآ» አሉ፡፡ فَلَ‍‍م‍ّ‍‍َا رَأَوْهَا قَالُ‍‍و‍‍ا‍ إِ‍نّ‍‍َا لَض‍‍َ‍ا‍لّ‍‍ُ‍و‍نَ
Bal Naĥnu Maĥrūmūna 068-027 آ«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነንآ» አሉ፡፡ بَلْ نَحْنُ مَحْرُوم‍‍ُ‍و‍نَ
Qāla 'Awsaţuhum 'Alam 'Aqul Lakum Lawlā Tusabbiĥūna 068-028 ትክክለኛቸው آ«ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?آ» አላቸው፡፡ ق‍َا‍لَ أَوْسَطُهُمْ أَلَمْ أَقُ‍‍ل‍ْ لَكُمْ لَوْلاَ تُسَبِّح‍‍ُ‍و‍نَ
Qālū Subĥāna Rabbinā 'Innā Kunnā Žālimīna 068-029 آ«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤آ» አሉ፡፡ قَالُو‍‍ا‍ سُ‍‍ب‍‍ْح‍‍َ‍ا‍نَ رَبِّنَ‍‍ا إِ‍نّ‍‍َا كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا ظَالِم‍‍ِ‍ي‍نَ
Fa'aqbala Ba`đuhum `Alá Ba`đin Yatalāwamūna 068-030 የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡ فَأَ‍ق‍‍ْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْض‍‍‍ٍ يَتَلاَوَم‍‍ُ‍و‍نَ
Qālū Yā Waylanā 'Innā Kunnā Ţāghīna 068-031 آ«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤آ» አሉ፡፡ قَالُو‍‍ا‍ يَا وَيْلَنَ‍‍ا إِ‍نّ‍‍َا كُ‍‍ن‍ّ‍‍َا طَاغ‍‍ِ‍ي‍نَ
`Asá Rabbunā 'An Yubdilanā Khayrāan Minhā 'Innā 'Ilá Rabbinā Rāghibūna 068-032 آ«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤آ» (አሉ)፡፡ عَسَى رَبُّنَ‍‍ا‍ أَ‍ن‍ْ يُ‍‍ب‍‍ْدِلَنَا خَيْرا‍ً مِنْهَ‍‍ا إِ‍نّ‍‍َ‍‍ا إِلَى رَبِّنَا رَاغِب‍‍ُ‍و‍نَ
Kadhālika Al-`Adhābu Wa La`adhābu Al-'Ākhirati 'Akbaru Law Kānū Ya`lamūna 068-033 ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡ كَذَلِكَ ا‍لْعَذ‍َا‍بُ وَلَعَذ‍َا‍بُ ا‍لآخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُو‍‍ا‍ يَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
'Inna Lilmuttaqīna `Inda Rabbihim Jannāti An-Na`īmi 068-034 ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ لِلْمُتَّق‍‍ِ‍ي‍نَ عِ‍‍ن‍‍ْدَ رَبِّهِمْ جَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍تِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َع‍‍ِ‍ي‍مِ
'Afanaj`alu Al-Muslimīna Kālmujrimīna 068-035 ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን? أَفَنَ‍‍ج‍‍ْعَلُ ا‍لْمُسْلِم‍‍ِ‍ي‍نَ كَالْمُ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِم‍‍ِ‍ي‍نَ
Mā Lakum Kayfa Taĥkumūna 068-036 ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡ مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُم‍‍ُ‍و‍نَ
'Am Lakum Kitābun Fīhi Tadrusūna 068-037 በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን? أَمْ لَكُمْ كِت‍‍َ‍ا‍ب‍‍‍ٌ ف‍‍ِ‍ي‍هِ تَ‍‍د‍‍ْرُس‍‍ُ‍و‍نَ
'Inna Lakum Fīhi Lamā Takhayyarūna 068-038 በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል) إِ‍نّ‍‍َ لَكُمْ ف‍‍ِ‍ي‍هِ لَمَا تَخَيَّر‍ُو‍نَ
'Am Lakum 'Aymānun `Alaynā Bālighatun 'Ilá Yawmi Al-Qiyāmati 'Inna Lakum Lamā Taĥkumūna 068-039 ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን? أَمْ لَكُمْ أَيْم‍‍َ‍ا‍نٌ عَلَيْنَا بَالِغَة‍‍‍ٌ إِلَى يَوْمِ ا‍لْقِيَامَةِ إِ‍نّ‍‍َ لَكُمْ لَمَا تَحْكُم‍‍ُ‍و‍نَ
Salhum 'Ayyuhum Bidhālika Za`īmun 068-040 በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡ سَلْهُم أَيُّهُ‍‍م‍ْ بِذَلِكَ زَع‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ
'Am Lahum Shurakā'u Falya'tū Bishurakā'ihim 'In Kānū Şādiqīna 068-041 ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) آ«ተጋሪዎችآ» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ آ«ተጋሪዎቻቸውንآ» ያምጡ፡፡ أَمْ لَهُمْ شُرَك‍‍َ‍ا‍ءُ فَلْيَأْتُو‍‍ا‍ بِشُرَك‍‍َ‍ا‍ئِهِمْ إِ‍ن‍ْ كَانُو‍‍ا‍ صَادِق‍‍ِ‍ي‍نَ
Yawma Yukshafu `An Sāqin Wa Yud`awna 'Ilá As-Sujūdi Falā Yastaţī`ūna 068-042 ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡ يَوْمَ يُكْشَفُ عَ‍‍ن‍ْ س‍‍َ‍ا‍ق‍‍‍ٍ وَيُ‍‍د‍‍ْعَوْنَ إِلَى ا‍لسُّج‍‍ُ‍و‍دِ فَلاَ يَسْتَطِيع‍‍ُ‍و‍نَ
Khāshi`atan 'Abşāruhum Tarhaquhum Dhillatun Wa Qad Kānū Yud`awna 'Ilá As-Sujūdi Wa Hum Sālimūna 068-043 ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡ خَاشِعَةً أَ‍ب‍‍ْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّة‍‍‍ٌ وَقَ‍‍د‍ْ كَانُو‍‍ا‍ يُ‍‍د‍‍ْعَوْنَ إِلَى ا‍لسُّج‍‍ُ‍و‍دِ وَهُمْ سَالِم‍‍ُ‍و‍نَ
Fadharnī Wa Man Yukadhdhibu Bihadhā Al-Ĥadīthi Sanastadrijuhum Min Ĥaythu Lā Ya`lamūna 068-044 በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡ فَذَرْنِي وَمَ‍‍ن‍ْ يُكَذِّبُ بِهَذَا ا‍لْحَد‍ِي‍ثِ سَنَسْتَ‍‍د‍‍ْ‍ر‍‍ِجُهُ‍‍م‍ْ مِنْ حَيْثُ لاَ يَعْلَم‍‍ُ‍و‍نَ
Wa 'Umlī Lahum 'Inna Kaydī Matīnun 068-045 እነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡ وَأُمْلِي لَهُمْ إِ‍نّ‍‍َ كَيْدِي مَت‍‍ِ‍ي‍ن‍‍‍ٌ
'Am Tas'aluhum 'Ajrāan Fahum Min Maghramin Muthqalūna 068-046 በእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን? أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَ‍ج‍‍ْرا‍ً فَهُ‍‍م‍ْ مِ‍‍ن‍ْ مَغْرَم‍‍‍ٍ مُثْقَل‍‍ُ‍و‍نَ
'Am `Indahumu Al-Ghaybu Fahum Yaktubūna 068-047 ወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? أَمْ عِ‍‍ن‍‍ْدَهُمُ ا‍لْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُب‍‍ُ‍و‍نَ
Fāşbir Liĥukmi Rabbika Wa Lā Takun Kaşāĥibi Al-Ĥūti 'Idhdá Wa Huwa Makžūmun 068-048 ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلاَ تَكُ‍‍ن‍ْ كَصَاحِبِ ا‍لْح‍‍ُ‍و‍تِ إِذْ نَادَى وَهُوَ مَكْظ‍‍ُ‍و‍م‍‍‍ٌ
Lawlā 'An Tadārakahu Ni`matun Min Rabbihi Lanubidha Bil-`Arā'i Wa Huwa Madhmūmun 068-049 ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡ لَوْلاَ أَ‍ن‍ْ تَدَارَكَهُ نِعْمَة‍‍‍ٌ مِ‍‍ن‍ْ رَبِّهِ لَنُبِذَ بِ‍‍ا‍لْعَر‍َا‍ءِ وَهُوَ مَذْم‍‍ُ‍و‍م‍‍‍ٌ
jtabāhu Rabbuhu Faja`alahu Mina Aş-Şāliĥīna 068-050 ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡ فَا‍ج‍‍ْتَب‍‍َ‍ا‍هُ رَبُّهُ فَجَعَلَهُ مِنَ ا‍لصَّالِح‍‍ِ‍ي‍نَ
Wa 'In Yakādu Al-Ladhīna Kafarū Layuzliqūnaka Bi'abşārihim Lammā Sami`ū Adh-Dhikra Wa Yaqūlūna 'Innahu Lamajnūnun 068-051 እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ آ«እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነውآ» ይላሉ፡፡ وَإِ‍ن‍ْ يَك‍‍َ‍ا‍دُ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ لَيُزْلِقُونَكَ بِأَ‍ب‍‍ْصَا‍ر‍‍ِهِمْ لَ‍‍م‍ّ‍‍َا سَمِعُو‍‍ا‍ ا‍لذِّكْرَ وَيَقُول‍‍ُ‍و‍نَ إِ‍نّ‍‍َهُ لَمَ‍‍ج‍‍ْن‍‍ُ‍و‍ن‍‍‍ٌ
Wa Mā Huwa 'Illā Dhikrun Lil`ālamīna 068-052 ግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ إِلاَّ ذِكْر‍ٌ لِلْعَالَم‍‍ِ‍ي‍نَ
Next Sūrah