Tabāraka Al-Ladhī Biyadihi Al-Mulku Wa Huwa `Alá Kulli Shay'in Qadīrun  | 067-001 ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ | تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ |
Al-Ladhī Khalaqa Al-Mawta Wa Al-Ĥayāata Liyabluwakum 'Ayyukum 'Aĥsanu `Amalāan Wa Huwa Al-`Azīzu Al-Ghafūru  | 067-002 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ | الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلاً وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ |
Al-Ladhī Khalaqa Sab`a Samāwātin Ţibāqāan Mā Tará Fī Khalqi Ar-Raĥmāni Min Tafāwutin Fārji`i Al-Başara Hal Tará Min Fuţūrin  | 067-003 ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ آ«ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?آ» | الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقاً مَا تَرَى فِي خَلْقِ الرَّحْمَنِ مِنْ تَفَاوُتٍ فَارْجِعِ الْبَصَرَ هَلْ تَرَى مِنْ فُطُورٍ |
Thumma Arji`i Al-Başara Karratayni Yanqalib 'Ilayka Al-Başaru Khāsi'āan Wa Huwa Ĥasīrun  | 067-004 ከዚያም ብዙ ጊዜ ዓይንህን መላልስ፡፡ ዓይንህ ተዋርዶ እርሱም የደከመ ኾኖ ወዳንተ ይመለሳል፡፡ | ثُمَّ ارْجِعِ الْبَصَرَ كَرَّتَيْنِ يَنقَلِبْ إِلَيْكَ الْبَصَرُ خَاسِئاً وَهُوَ حَسِيرٌ |
Wa Laqad Zayyannā As-Samā'a Ad-Dunyā Bimaşābīĥa Wa Ja`alnāhā Rujūmāan Lilshshayāţīni Wa 'A`tadnā Lahum `Adhāba As-Sa`īri  | 067-005 ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት፡፡ ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፡፡ ለእነርሱም (ለሰይጣኖች) የእሳትን ቅጣት አዘጋጀን፡፡ | وَلَقَدْ زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِمَصَابِيحَ وَجَعَلْنَاهَا رُجُوماً لِلشَّيَاطِينِ وَأَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابَ السَّعِيرِ |
Wa Lilladhīna Kafarū Birabbihim `Adhābu Jahannama Wa Bi'sa Al-Maşīru  | 067-006 ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! | وَلِلَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ |
'Idhā 'Ulqū Fīhā Sami`ū Lahā Shahīqāan Wa Hiya Tafūru  | 067-007 በውስጧ በተጣሉ ጊዜ፤ እርሷ የምትፈላ ስትኾን ለእርሷ (እንደ አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ፡፡ | إِذَا أُلْقُوا فِيهَا سَمِعُوا لَهَا شَهِيقاً وَهِيَ تَفُورُ |
Takādu Tamayyazu Mina Al-Ghayži Kullamā 'Ulqiya Fīhā Fawjun Sa'alahum Khazanatuhā 'Alam Ya'tikum Nadhīrun  | 067-008 ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፡፡ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር ዘበኞችዋ آ«አስፈራሪ (ነቢይ) አልመጣችሁምን?آ» በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡ | تَكَادُ تَمَيَّزُ مِنَ الْغَيْظِ كُلَّمَا أُلْقِيَ فِيهَا فَوْجٌ سَأَلَهُمْ خَزَنَتُهَا أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَذِيرٌ |
Qālū Balá Qad Jā'anā Nadhīrun Fakadhdhabnā Wa Qulnā Mā Nazzala Al-Lahu Min Shay'in 'In 'Antum 'Illā Fī Đalālin Kabīrin  | 067-009 آ«አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶናል፡፡ አስተባበልንም፡፡ አላህም ምንንም አላወረደ እናንተ (አውርዷል ስትሉ) በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጅ አይደላችሁም አልንآ» ይላሉ፡፡ | قَالُوا بَلَى قَدْ جَاءَنَا نَذِيرٌ فَكَذَّبْنَا وَقُلْنَا مَا نَزَّلَ اللَّهُ مِنْ شَيْءٍ إِنْ أَنْتُمْ إِلاَّ فِي ضَلاَلٍ كَبِيرٍ |
Wa Qālū Law Kunnā Nasma`u 'Aw Na`qilu Mā Kunnā Fī 'Aşĥābi As-Sa`īri  | 067-010 آ«የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበርآ» ይላሉ፡፡ | وَقَالُوا لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِي أَصْحَابِ السَّعِيرِ |
Fā`tarafū Bidhanbihim Fasuĥqāan Li'şĥābi As-Sa`īri  | 067-011 በኀጢኣታቸውም ያምናሉ ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡ | فَاعْتَرَفُوا بِذَنْبِهِمْ فَسُحْقاً لِأصْحَابِ السَّعِيرِ |
'Inna Al-Ladhīna Yakhshawna Rabbahum Bil-Ghaybi Lahum Maghfiratun Wa 'Ajrun Kabīrun  | 067-012 እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡ | إِنَّ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ بِالْغَيْبِ لَهُمْ مَغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ |
Wa 'Asirrū Qawlakum 'Aw Ajharū Bihi 'Innahu `Alīmun Bidhāti Aş-Şudūri  | 067-013 (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ፡፡ ወይም በእርሱ ጩሁ፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ | وَأَسِرُّوا قَوْلَكُمْ أَوْ اجْهَرُوا بِهِ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ |
'Alā Ya`lamu Man Khalaqa Wa Huwa Al-Laţīfu Al-Khabīru  | 067-014 የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀት ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን? | أَلاَ يَعْلَمُ مَنْ خَلَقَ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ |
Huwa Al-Ladhī Ja`ala Lakumu Al-'Arđa Dhalūlāan Fāmshū Fī Manākibihā Wa Kulū Min Rizqihi Wa 'Ilayhi An-Nushūru  | 067-015 እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡ | هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الأَرْضَ ذَلُولاً فَامْشُوا فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُوا مِنْ رِزْقِهِ وَإِلَيْهِ النُّشُورُ |
'A'amintum Man Fī As-Samā'i 'An Yakhsifa Bikumu Al-'Arđa Fa'idhā Hiya Tamūru  | 067-016 በሰማይ ውስጥ ያለን (ሰራዊት) በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) | أَأَمِنتُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ أَنْ يَخْسِفَ بِكُمُ الأَرْضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُ |
'Am 'Amintum Man Fī As-Samā'i 'An Yursila `Alaykum Ĥāşibāan Fasata`lamūna Kayfa Nadhīri  | 067-017 ወይም በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡ | أَمْ أَمِنتُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ أَنْ يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِباً فَسَتَعْلَمُونَ كَيْفَ نَذِيرِ |
Wa Laqad Kadhdhaba Al-Ladhīna Min Qablihim Fakayfa Kāna Nakīri  | 067-018 እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ ጥላቻዬም እንዴት ነበር! | وَلَقَدْ كَذَّبَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ |
'Awalam Yaraw 'Ilá Aţ-Ţayri Fawqahum Şāffātin Wa Yaqbiđna Mā Yumsikuhunna 'Illā Ar-Raĥmānu 'Innahu Bikulli Shay'in Başīrun  | 067-019 ወደ አእዋፍ ከበላያቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች የሚሰበሰቡም ሲኾኑ አላዩምን? ከአልረሕማን በቀር (ባየር ላይ) የሚይዛቸው የለም፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ | أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الطَّيْرِ فَوْقَهُمْ صَافَّاتٍ وَيَقْبِضْنَ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلاَّ الرَّحْمَنُ إِنَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ بَصِيرٌ |
'Amman Hādhā Al-Ladhī Huwa Jundun Lakum Yanşurukum Min Dūni Ar-Raĥmāni 'Ini Al-Kāfirūna 'Illā Fī Ghurūrin  | 067-020 በእውነቱ ያ እርሱ ከአልረሕማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የኾነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲዎች በመታለል ውስጥ እንጅ በሌላ ላይ አይደሉም፡፡ | أَمَّنْ هَذَا الَّذِي هُوَ جُندٌ لَكُمْ يَنصُرُكُمْ مِنْ دُونِ الرَّحْمَنِ إِنِ الْكَافِرُونَ إِلاَّ فِي غُرُورٍ |
'Amman Hādhā Al-Ladhī Yarzuqukum 'In 'Amsaka Rizqahu Bal Lajjū Fī `Utūwin Wa Nufūrin  | 067-021 ወይም ሲሳዩን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነቱ እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ችክ አሉ፡፡ | أَمَّنْ هَذَا الَّذِي يَرْزُقُكُمْ إِنْ أَمْسَكَ رِزْقَهُ بَلْ لَجُّوا فِي عُتُوٍّ وَنُفُورٍ |
'Afaman Yamshī Mukibbāan `Alá Wajhihi 'Ahdá 'Amman Yamshī Sawīyāan `Alá Şirāţin Mustaqīmin  | 067-022 በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚኼድ ሰው ይበልጥ የቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛ መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚኼድ? | أَفَمَنْ يَمْشِي مُكِبّاً عَلَى وَجْهِهِ أَهْدَى أَمَّنْ يَمْشِي سَوِيّاً عَلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ |
Qul Huwa Al-Ladhī 'Ansha'akum Wa Ja`ala Lakumu As-Sam`a Wa Al-'Abşāra Wa Al-'Af'idata Qalīlāan Mā Tashkurūna  | 067-023 آ«እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን፣ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው፡፡ ጥቂትንም አታመስግኑምآ» በላቸው፡፡ | قُلْ هُوَ الَّذِي أَنشَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالأَبْصَارَ وَالأَفْئِدَةَ قَلِيلاً مَا تَشْكُرُونَ |
Qul Huwa Al-Ladhī Dhara'akum Fī Al-'Arđi Wa 'Ilayhi Tuĥsharūna  | 067-024 آ«እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናቸሁ ነው፡፡ ወደእርሱም ትሰበሰባላችሁآ» በላቸው፡፡ | قُلْ هُوَ الَّذِي ذَرَأَكُمْ فِي الأَرْضِ وَإِلَيْهِ تُحْشَرُونَ |
Wa Yaqūlūna Matá Hādhā Al-Wa`du 'In Kuntum Şādiqīna  | 067-025 آ«እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?آ» ይላሉ፡፡ | وَيَقُولُونَ مَتَى هَذَا الْوَعْدُ إِنْ كُنتُمْ صَادِقِينَ |
Qul 'Innamā Al-`Ilmu `Inda Al-Lahi Wa 'Innamā 'Anā Nadhīrun Mubīnun  | 067-026 آ«ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁምآ» በላቸው፡፡ | قُلْ إِنَّمَا الْعِلْمُ عِنْدَ اللَّهِ وَإِنَّمَا أَنَا نَذِيرٌ مُبِينٌ |
Falammā Ra'awhu Zulfatan Sī'at Wujūhu Al-Ladhīna Kafarū Wa Qīla Hādhā Al-Ladhī Kuntum Bihi Tadda`ūna  | 067-027 (ቅጣቱን) ቅርብ ኾኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይክከፋሉ፡፡ آ«ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነውآ» ይባላሉም፡፡ | فَلَمَّا رَأَوْهُ زُلْفَةً سِيئَتْ وُجُوهُ الَّذِينَ كَفَرُوا وَقِيلَ هَذَا الَّذِي كُنتُمْ بِهِ تَدَّعُونَ |
Qul 'Ara'aytum 'In 'Ahlakaniya Al-Lahu Wa Man Ma`ī 'Aw Raĥimanā Faman Yujīru Al-Kāfirīna Min `Adhābin 'Alīmin  | 067-028 آ«አያችሁን? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም (በማቆየት) ቢያዝንልን ከሓዲዎችን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው?آ» በላቸው፡፡ | قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَهْلَكَنِيَ اللَّهُ وَمَنْ مَعِي أَوْ رَحِمَنَا فَمَنْ يُجِيرُ الْكَافِرِينَ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ |
Qul Huwa Ar-Raĥmānu 'Āmannā Bihi Wa `Alayhi Tawakkalnā Fasata`lamūna Man Huwa Fī Đalālin Mubīnin  | 067-029 آ«እርሱ (እመኑበት የምላችሁ) አልረሕማን ነው፡፡ (እኛ) በእርሱ አመንን፡፡ በርሱም ላይ ተጠጋን፡፡ ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የኾነው እርሱ ማን አንደ ኾነ በእርግጥ ታውቃላችሁآ» በላቸው፡፡ | قُلْ هُوَ الرَّحْمَنُ آمَنَّا بِهِ وَعَلَيْهِ تَوَكَّلْنَا فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ هُوَ فِي ضَلاَلٍ مُبِينٍ |
Qul 'Ara'aytum 'In 'Aşbaĥa Mā'uukum Ghawrāan Faman Ya'tīkum Bimā'in Ma`īnin  | 067-030 آ«አያችሁን? ውሃችሁ ሠራጊ ቢኾን ፈሳሺን ውሃ የሚያመጣላቸሁ ማን ነው?آ» በላቸው፡፡ (አላህ የዓለማት ጌታ ያመጣዋል)፡፡ | قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَصْبَحَ مَاؤُكُمْ غَوْراً فَمَنْ يَأْتِيكُمْ بِمَاءٍ مَعِينٍ |