57) Sūrat Al-Ĥadīd

Printed format

57) سُورَة الحَدِيد

Sabbaĥa Lillahi Mā Fī As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Huwa Al-`Azīzu Al-Ĥakīmu 057-001 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ وَهُوَ ا‍لْعَز‍ِي‍زُ ا‍لْحَك‍‍ِ‍ي‍مُ
Lahu Mulku As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Yuĥyī Wa Yumītu Wa Huwa `Alá Kulli Shay'in Qadīrun 057-002 የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ لَهُ مُلْكُ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ يُحْيِي وَيُم‍‍ِ‍ي‍تُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْء‍ٍ قَد‍ِي‍ر‍ٌ
Huwa Al-'Awwalu Wa Al-'Ākhiru Wa Až-Žāhiru Wa Al-Bāţinu Wa Huwa Bikulli Shay'in `Alīmun 057-003 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ا‍لأَوَّلُ وَا‍لآخِ‍‍ر‍ُ وَا‍لظَّاهِ‍‍ر‍ُ وَا‍لْبَاطِنُ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَل‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ
Huwa Al-Ladhī Khalaqa As-Samāwāti Wa Al-'Arđa Fī Sittati 'Ayyāmin Thumma Astawá `Alá Al-`Arshi Ya`lamu Mā Yaliju Fī Al-'Arđi Wa Mā Yakhruju Minhā Wa Mā Yanzilu Mina As-Samā'i Wa Mā Ya`ruju Fīhā Wa Huwa Ma`akum 'Ayna Mā Kuntum Wa Allāhu Bimā Ta`malūna Başīrun 057-004 እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ هُوَ ا‍لَّذِي خَلَقَ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيّ‍‍َ‍ا‍م‍‍‍ٍ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ ا‍سْتَوَى عَلَى ا‍لْعَرْشِ يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِي ا‍ Lahu Mulku As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa 'Ilá Al-Lahi Turja`u Al-'Umūru 057-005 የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡ لَهُ مُلْكُ ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَا‍لأَرْضِ وَإِلَى ا‍للَّهِ تُرْجَعُ ا‍لأُم‍‍ُ‍و‍رُ
Yūliju Al-Layla Fī An-Nahāri Wa Yūliju An-Nahāra Fī Al-Layli Wa Huwa `Alīmun Bidhāti Aş-Şudūri 057-006 ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፡፡ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነወ፡፡ يُولِجُ ا‍للَّيْلَ فِي ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َه‍‍َ‍ا‍ر‍ِ وَيُولِجُ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َه‍‍َ‍ا‍رَ فِي ا‍للَّيْلِ وَهُوَ عَل‍‍ِ‍ي‍م‍‍‍ٌ بِذ‍َا‍تِ ا‍لصُّد‍ُو‍ر‍ِ
'Āminū Bil-Lahi Wa Rasūlihi Wa 'Anfiqū Mimmā Ja`alakum Mustakhlafīna Fīhi Fa-Al-Ladhīna 'Āmanū Minkum Wa 'Anfaqū Lahum 'Ajrun Kabīrun 057-007 በአላህና በመልክተኛው እመኑ፡፡ (አላህ) በእርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፡፡ እነዚያም ከእናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡ آمِنُو‍‍ا‍ بِ‍‍ا‍للَّهِ وَرَسُولِهِ وَأَ‍ن‍‍ْفِقُو‍‍ا‍ مِ‍‍م‍ّ‍‍َا جَعَلَكُ‍‍م‍ْ مُسْتَخْلَف‍‍ِ‍ي‍نَ ف‍‍ِ‍ي‍هِ فَالَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ مِ‍‍ن‍‍ْكُمْ وَأَ‍ن‍‍ْفَقُو‍‍ا‍ لَهُمْ أَ‍ج‍‍ْر‍ٌ كَب‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ
Wa Mā Lakum Lā Tu'uminūna Bil-Lahi Wa Ar-Rasūlu Yad`ūkum Litu'uminū Birabbikum Wa Qad 'Akhadha Mīthāqakum 'In Kuntum Mu'uminīna 057-008 መልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲኾን (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም የያዘባችሁ ሲኾን በአላህ የማታምኑት ለእናንተ ምን አልላችሁ? የምታምኑ ብትኾኑ (ወደ እምነት ቸኩሉ)፡፡ وَمَا لَكُمْ لاَ تُؤْمِن‍‍ُ‍و‍نَ بِ‍‍ا‍للَّهِ وَا‍لرَّس‍‍ُ‍و‍لُ يَ‍‍د‍‍ْعُوكُمْ لِتُؤْمِنُو‍‍ا‍ بِرَبِّكُمْ وَقَ‍‍د‍ْ أَخَذَ مِيثَاقَكُمْ إِ‍ن‍ْ كُ‍‍ن‍‍ْتُ‍‍م‍ْ مُؤْمِن‍‍ِ‍ي‍نَ
Huwa Al-Ladhī Yunazzilu `Alá `Abdihi 'Āyātin Bayyinātin Liyukhrijakum Mina Až-Žulumāti 'Ilá An-Nūri Wa 'Inna Al-Laha Bikum Lara'ūfun Raĥīmun 057-009 እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የኾኑን አንቀጾች በበሪያው ላይ የሚያወርድ ነው፡፡ አላህም ለእናንተ በእርግጥ ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ هُوَ ا‍لَّذِي يُنَزِّلُ عَلَى عَ‍‍ب‍‍ْدِهِ آي‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ بَيِّن‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٍ لِيُخْ‍‍ر‍‍ِجَكُ‍‍م‍ْ مِنَ ا‍لظُّلُم‍‍َ‍ا‍تِ إِلَى ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُ‍و‍ر‍ِ وَإِ‍نّ‍‍َ ا‍للَّهَ بِكُمْ لَرَء‍ُو‍ف‍‍‍ٌ رَح‍
Wa Mā Lakum 'Allā Tunfiqū Fī Sabīli Al-Lahi Wa Lillahi Mīrāthu As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Lā Yastawī Minkum Man 'Anfaqa Min Qabli Al-Fatĥi Wa Qātala 'Ūlā'ika 'A`žamu Darajatan Mina Al-Ladhīna 'Anfaqū Min Ba`du Wa Qātalū Wa Kullāan Wa`ada Al-Lahu Al-Ĥusná Wa Allāhu Bimā Ta`malūna Khabīrun 057-010 የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ሲኾን በአላህ መንገድ የማትለግሱትም ለእናንተ ምን አልላችሁ? ከእናንተ ውስጥ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው (ከተከፈተች በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይስተካከልም፡፡ ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ وَمَا لَكُمْ أَلاَّ تُ‍‍ن‍‍ْفِقُو‍‍ا‍ فِي سَب‍‍ِ‍ي‍لِ ا‍للَّهِ وَلِلَّهِ مِير‍َا‍ثُ Man Dhā Al-Ladhī Yuqriđu Al-Laha Qarđāan Ĥasanāan Fayuđā`ifahu Lahu Wa Lahu 'Ajrun Karīmun 057-011 ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለእርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አልለው፡፡ مَ‍‍ن‍ْ ذَا ا‍لَّذِي يُ‍‍ق‍‍ْ‍‍ر‍‍ِضُ ا‍للَّهَ قَرْضاً حَسَنا‍ً فَيُضَاعِفَهُ لَهُ وَلَهُ أَ‍ج‍‍ْر‍ٌ كَ‍‍ر‍‍ِي‍م‍‍‍ٌ
Yawma Tará Al-Mu'uminīna Wa Al-Mu'umināti Yas`á Nūruhum Bayna 'Aydīhim Wa Bi'aymānihim Bushrākumu Al-Yawma Jannātun Tajrī Min Taĥtihā Al-'Anhāru Khālidīna Fīhā Dhālika Huwa Al-Fawzu Al-`Ažīmu 057-012 ምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲኾን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)፡፡ ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቁ ዕድል ነው፡፡ يَوْمَ تَرَى ا‍لْمُؤْمِن‍‍ِ‍ي‍نَ وَا‍لْمُؤْمِن‍‍َ‍ا‍تِ يَسْعَى نُورُهُ‍‍م‍ْ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِ‍‍م‍ْ بُشْرَاكُمُ ا‍لْيَوْمَ جَ‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍ت‍‍‍ٌ تَ‍‍ج‍‍ْ‍‍ر‍‍ِي مِ‍ Yawma Yaqūlu Al-Munāfiqūna Wa Al-Munāfiqātu Lilladhīna 'Āmanū Anžurūnā Naqtabis Minrikum Qīla Arji`ū Warā'akum Fāltamisū Nūrāan Fađuriba Baynahum Bisūrin Lahu Bābun Bāţinuhu Fīhi Ar-Raĥmatu Wa Žāhiruhu Min Qibalihi Al-`Adhābu 057-013 መናፍቃንና መናፍቃት ለእነዚያ ለአመኑት آ«ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንናآ» የሚሉበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ آ«ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፡፡ ብርሃንንም ፈልጉآ» ይባላሉ፡፡ ግቢው በውስጡ ችሮታ (ገነት) ያለበት ውጭውም ከበኩሉ ስቃይ (እሳት) ያለበት የኾነ (ደጃፍ ባለው አጥር)፡፡ يَوْمَ يَق‍‍ُ‍و‍لُ ا‍لْمُنَافِق‍‍ُ‍و‍نَ وَا‍لْمُنَافِق‍‍َ‍ا‍تُ لِلَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ ا‍ن‍‍ْظُرُونَا نَ‍‍ق‍‍ْتَبِسْ مِ‍‍ن‍ْ نُو‍ر‍‍ِكُمْ ق‍Yunādūnahum 'Alam Nakun Ma`akum Qālū Balá Wa Lakinnakum Fatantum 'Anfusakum Wa Tarabbaştum Wa Artabtum Wa Gharratkumu Al-'Amānīyu Ĥattá Jā'a 'Amru Al-Lahi Wa Gharrakum Bil-Lahi Al-Gharūru 057-014 آ«ከእናንተ ጋር አልነበርንምን?آ» በማለት ይጠሩዋቸዋል፡፡ آ«እውነት ነው፡፡ ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ፡፡ (በነቢዩ አደጋዎችን) ተጠባበቃችሁም፡፡ ተጠራጠራችሁም፡፡ የአላህም ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) ሸነገላችሁ፤آ» ይሏቸዋል፡፡ يُنَادُونَهُمْ أَلَمْ نَكُ‍‍ن‍ْ مَعَكُمْ قَالُو‍‍ا‍ بَلَى وَلَكِ‍‍ن‍ّ‍‍َكُمْ فَتَ‍‍ن‍‍ْتُمْ أَ‍ن‍‍ْفُسَكُمْ وَتَرَبَّصْتُمْ وَا‍رْتَ‍‍ب‍‍ْتُمْ وَغَرَّتْكُمُ ا‍لأَمَانِيُّ حَتَّى ج‍‍َ‍ا‍ءَ أَمْرُ Fālyawma Lā Yu'ukhadhu Minkum Fidyatun Wa Lā Mina Al-Ladhīna Kafarū Ma'wākumu An-Nāru Hiya Mawlākum Wa Bi'sa Al-Maşīru 057-015 آ«ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፡፡ ከእነዚያ ከካዱትም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፡፡ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!آ» (ይሏቸዋል)፡፡ فَالْيَوْمَ لاَ يُؤْخَذُ مِ‍‍ن‍‍ْكُمْ فِ‍‍د‍‍ْيَة‍‍‍ٌ وَلاَ مِنَ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُوا‍ مَأْوَاكُمُ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍رُ هِيَ مَوْلاَكُمْ وَبِئْسَ ا‍لْمَص‍‍ِ‍ي‍‍ر‍ُ
'Alam Ya'ni Lilladhīna 'Āmanū 'An Takhsha`a Qulūbuhum Lidhikri Al-Lahi Wa Mā Nazala Mina Al-Ĥaqqi Wa Lā Yakūnū Kālladhīna 'Ū Al-Kitāba Min Qablu Faţāla `Alayhimu Al-'Amadu Faqasat Qulūbuhum Wa Kathīrun Minhum Fāsiqūna 057-016 ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذ‍ِي‍نَ آمَنُ‍‍و‍‍ا‍ أَ‍ن‍ْ تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْ‍‍ر‍ِ ا‍للَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ا‍لْحَقِّ وَلاَ يَكُونُو‍‍ا‍ كَالَّذ‍ِي‍نَ أ‍ُ‍وتُو‍‍ا‍ ا‍لْكِت‍‍َ‍ا‍بَ مِ‍ A`lamū 'Anna Al-Laha Yuĥyī Al-'Arđa Ba`da Mawtihā Qad Bayyannā Lakumu Al-'Āyāti La`allakum Ta`qilūna 057-017 አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው የሚያደርጋት መኾኑን ዕወቁ፡፡ ታወቁ ዘንድ አንቀጾችን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ፡፡ ا‍عْلَمُ‍‍و‍‍ا‍ أَ‍نّ‍‍َ ا‍للَّهَ يُحْيِي ا‍لأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا قَ‍‍د‍ْ بَيَّ‍‍ن‍ّ‍‍َا لَكُمُ ا‍لآي‍‍َ‍ا‍تِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِل‍‍ُ‍و‍نَ
'Inna Al-Muşşaddiqīna Wa Al-Muşşaddiqāti Wa 'Aqrađū Al-Laha Qarđāan Ĥasanāan Yuđā`afu Lahum Wa Lahum 'Ajrun Karīmun 057-018 የመጸወቱ ወንዶችና፣ የመጸወቱ ሴቶች፣ ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለእነርሱ መልካም ምንዳ አልላቸው፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لْمُصَّدِّق‍‍ِ‍ي‍نَ وَا‍لْمُصَّدِّق‍‍َ‍ا‍تِ وَأَ‍ق‍‍ْرَضُو‍‍ا‍ ا‍للَّهَ قَرْضاً حَسَنا‍ً يُضَاعَفُ لَهُمْ وَلَهُمْ أَ‍ج‍‍ْر‍ٌ كَ‍‍ر‍‍ِي‍م‍‍‍ٌ
Wa Al-Ladhīna 'Āmanū Bil-Lahi Wa Rusulihi 'Ūlā'ika Humu Aş-Şiddīqūna Wa Ash-Shuhadā'u `Inda Rabbihim Lahum 'Ajruhum Wa Nūruhum Wa Al-Ladhīna Kafarū Wa Kadhdhabū Bi'āyātinā 'Ūlā'ika 'Aşĥābu Al-Jaĥīmi 057-019 እነዚያም በአላህና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ وَالَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ بِ‍‍ا‍للَّهِ وَرُسُلِهِ أ‍ُ‍وْل‍‍َ‍ا‍ئِكَ هُمُ ا‍لصِّدِّيق‍‍ُ‍و‍نَ وَا‍لشُّهَد‍َا‍ءُ عِ‍‍ن‍‍ْدَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَ‍ج‍‍ْرُهُمْ وَنُورُهُمْ وَا‍لَّذ‍ِي‍نَ كَفَرُو A`lamū 'Annamā Al-Ĥayāatu Ad-Dunyā La`ibun Wa Lahwun Wa Zīnatun Wa Tafākhurun Baynakum Wa Takāthurun Al-'Amwli Wa Al-'Awlādi Kamathali Ghaythin 'A`jaba Al-Kuffāra Nabātuhu Thumma Yahīju Fatarāhu Muşfarrāan Thumma Yakūnu Ĥuţāmāan Wa Fī Al-'Ākhirati `Adhābun Shadīdun Wa Maghfiratun Mina Al-Lahi Wa Riđwānun Wa Mā Al-Ĥayāatu Ad-Dunyā 'Illā Matā`u Al-Ghurūri 057-020 ቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ ا‍عْلَمُ‍‍و‍‍ا‍ أَ‍نّ‍‍َمَا ا‍لْحَي‍Sābiqū 'Ilá Maghfiratin Min Rabbikum Wa Jannatin `Arđuhā Ka`arđi As-Samā'i Wa Al-'Arđi 'U`iddat Lilladhīna 'Āmanū Bil-Lahi Wa Rusulihi Dhālika Fađlu Al-Lahi Yu'utīhi Man Yashā'u Wa Allāhu Dhū Al-Fađli Al-`Ažīmi 057-021 ከጌታችሁ ወደ ኾነች ምሕረት፣ ወርዷ እደ ሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፡፡ ለእነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች፡፡ ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ سَابِقُ‍‍و‍‍ا‍ إِلَى مَغْفِرَة‍‍‍ٍ مِ‍‍ن‍ْ رَبِّكُمْ وَجَ‍‍ن‍ّ‍‍َةٍ عَرْضُهَا كَعَرْضِ ا‍لسَّم‍‍َ‍ا‍ءِ وَا‍لأَرْضِ أُعِدَّتْ لِلَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ بِ‍‍ا‍للَّهِ وَرُسُلِهِ ذَلِكَ فَضْلُ ا‍للَّهِ يُؤْت‍‍ِ‍ي&z
Mā 'Aşāba Min Muşībatin Al-'Arđi Wa Lā Fī 'Anfusikum 'Illā Fī Kitābin Min Qabli 'An Nabra'ahā 'Inna Dhālika `Alá Al-Lahi Yasīrun 057-022 በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ مَ‍‍ا‍ أَص‍‍َ‍ا‍بَ مِ‍‍ن‍ْ مُصِيبَة‍‍‍ٍ فِي ا‍لأَرْضِ وَلاَ فِ‍‍ي‍ أَ‍ن‍‍ْفُسِكُمْ إِلاَّ فِي كِت‍‍َ‍ا‍ب‍‍‍ٍ مِ‍‍ن‍ْ قَ‍‍ب‍‍ْلِ أَ‍ن‍ْ نَ‍‍ب‍‍ْرَأَهَ‍‍ا إِ‍نّ‍‍َ ذَلِكَ عَلَى ا‍للَّهِ يَس‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ
Likaylā Ta'saw `Alá Mā Fātakum Wa Lā Tafraĥū Bimā 'Ātākum Wa Allāhu Lā Yuĥibbu Kulla Mukhtālin Fakhūrin 057-023 (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም፡፡ لِكَيْلاَ تَأْسَوْا عَلَى مَا فَاتَكُمْ وَلاَ تَفْرَحُو‍‍ا‍ بِمَ‍‍ا آتَاكُمْ وَا‍للَّهُ لاَ يُحِبُّ كُلَّ مُخْت‍‍َ‍ا‍ل‍‍‍ٍ فَخ‍‍ُ‍و‍ر‍ٍ
Al-Ladhīna Yabkhalūna Wa Ya'murūna An-Nāsa Bil-Bukhli Wa Man Yatawalla Fa'inna Al-Laha Huwa Al-Ghanīyu Al-Ĥamīdu 057-024 (እነርሱም) እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት የሚያዝዙ ናቸው፡፡ (ከእውነት) የሚሸሽም ሰው (ጥፋቱ በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ يَ‍‍ب‍‍ْخَل‍‍ُ‍و‍نَ وَيَأْمُر‍ُو‍نَ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َ‍ا‍سَ بِ‍‍ا‍لْبُخْلِ وَمَ‍‍ن‍ْ يَتَوَلَّ فَإِ‍نّ‍‍َ ا‍للَّهَ هُوَ ا‍لْغَنِيُّ ا‍لْحَم‍‍ِ‍ي‍‍د‍ُ
Laqad 'Arsalnā Rusulanā Bil-Bayyināti Wa 'Anzalnā Ma`ahumu Al-Kitāba Wa Al-Mīzāna Liyaqūma An-Nāsu Bil-Qisţi Wa 'Anzalnā Al-Ĥadīda Fīhi Ba'sun Shadīdun Wa Manāfi`u Lilnnāsi Wa Liya`lama Al-Lahu Man Yanşuruhu Wa Rusulahu Bil-Ghaybi 'Inna Al-Laha Qawīyun `Azīzun 057-025 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደእነርሱ አወረድን፤ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያልሉበት ሲኾን አወረድን፡፡ (እንዲጠቀሙበት) አላህም ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን በሩቅ ኾኖ የሚረዳውን ሰው ሊያውቅ (ሊገልጽ አወረደው)፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ لَقَ‍‍د‍ْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِ‍‍ا‍لْبَيِّن‍‍َ‍ا‍تِ وَأَ‍ن‍‍ْزَلْنَا مَعَهُمُ ا‍لْكِت‍‍َ‍ا‍بَ وَا‍لْمِيز Wa Laqad 'Arsalnā Nūĥāan Wa 'Ibrāhīma Wa Ja`alnā Fī Dhurrīyatihimā An-Nubūwata Wa Al-Kitāba Faminhum Muhtadin Wa Kathīrun Minhum Fāsiqūna 057-026 ኑሕን፣ ኢብራሂምንም በእርግጥ ላክን፡፡ በዘሮቻቸውም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፎችን አደረግን፡፡ ከእነርሱም ቅን አልለ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ أَرْسَلْنَا نُوحا‍ً وَإِ‍ب‍‍ْرَاه‍‍ِ‍ي‍مَ وَجَعَلْنَا فِي ذُرِّيَّتِهِمَا ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُبُوَّةَ وَا‍لْكِت‍‍َ‍ا‍بَ فَمِنْهُ‍‍م‍ْ مُهْتَد‍ٍ وَكَث‍‍ِ‍ي‍ر‍ٌ مِنْهُمْ فَاسِق‍‍ُ‍و‍نَ
Thumma Qaffaynā `Alá 'Āthārihim Birusulinā Wa Qaffaynā Bi`īsá Abni Maryama Wa 'Ātaynāhu Al-'Injīla Wa Ja`alnā Fī Qulūbi Al-Ladhīna Attaba`ūhu Ra'fatan Wa Raĥmatan Wa Rahbānīyatan Abtada`ūhā Mā Katabnāhā `Alayhim 'Illā Abtighā'a Riđwāni Al-Lahi Famā Ra`awhā Ĥaqqa Ri`āyatihā Fa'ātaynā Al-Ladhīna 'Āmanū Minhum 'Ajrahum Wa Kathīrun Minhum Fāsiqūna 057-027 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት (ሰዎች) ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን፣ አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፡፡ በእነርሱ ላይ (ምንኩስናን) አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ (ፈጠሩዋት)፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም፤ አልጠበቋትም፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ قَفَّيْنَا عَلَى آثَا‍ر‍‍ِ
Yā 'Ayyuhā Al-Ladhīna 'Āmanū Attaqū Al-Laha Wa 'Āminū Birasūlihi Yu'utikum Kiflayni Min Raĥmatihi Wa Yaj`al Lakum Nūrāan Tamshūna Bihi Wa Yaghfir Lakum Wa Allāhu Ghafūrun Raĥīmun 057-028 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ በመልእክተኛውም እመኑ፡፡ ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና፡፡ ለእናንተም በእርሱ የምትኼዱበት የኾነ ብርሃንን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ ي‍َا‍أَيُّهَا ا‍لَّذ‍ِي‍نَ آمَنُو‍‍ا‍ ا‍تَّقُو‍‍ا‍ ا‍للَّهَ وَآمِنُو‍‍ا‍ بِرَسُولِهِ يُؤْتِكُمْ كِفْلَيْنِ مِ‍‍ن‍ْ رَحْمَتِهِ وَيَ‍‍ج‍‍ْعَ‍‍ل‍ْ لَكُمْ نُورا‍ً تَمْش‍‍ُ‍و‍نَ بِهِ وَيَغْفِرْ لَكُمْ وَا‍للَّهُ غَف&zw
Li'allā Ya`lama 'Ahlu Al-Kitābi 'Allā Yaqdirūna `Alá Shay'in Min Fađli Al-Lahi Wa 'Anna Al-Fađla Biyadi Al-Lahi Yu'utīhi Man Yashā'u Wa Allāhu Dhū Al-Fađli Al-`Ažīmi 057-029 (ይህም) የመጽሐፉ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መኾናቸውን ችሮታም በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል ማለትን እንዲያውቁ ነው፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ لِئَلاَّ يَعْلَمَ أَهْلُ ا‍لْكِت‍‍َ‍ا‍بِ أَلاَّ يَ‍‍ق‍‍ْدِر‍ُو‍نَ عَلَى شَيْء‍ٍ مِ‍‍ن‍ْ فَضْلِ ا‍للَّهِ وَأَ‍نّ‍‍َ ا‍لْفَضْلَ بِيَدِ ا‍للَّهِ يُؤْت‍‍ِ‍ي‍هِ مَ‍‍ن‍ْ يَش‍‍َ‍ا‍ءُ وَا‍للَّهُ ذُو ا‍لْفَضْلِ ا‍لْعَظ‍‍ِ‍ي‍م
Next Sūrah