Ar-Raĥmānu  | 055-001 አል-ረሕማን፤ | الرَّحمَانُ |
`Allama Al-Qur'āna  | 055-002 ቁርኣንን አስተማረ፡፡ | عَلَّمَ الْقُرْآنَ |
Khalaqa Al-'Insāna  | 055-003 ሰውን ፈጠረ፡፡ | خَلَقَ الإِنسَانَ |
`Allamahu Al-Bayāna  | 055-004 መናገርን አስተማረው፡፡ | عَلَّمَهُ الْبَيَانَ |
Ash-Shamsu Wa Al-Qamaru Biĥusbānin  | 055-005 ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡ | الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ بِحُسْبَانٍ |
Wa An-Najmu Wa Ash-Shajaru Yasjudāni  | 055-006 ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡ | وَالنَّجْمُ وَالشَّجَرُ يَسْجُدَانِ |
Wa As-Samā'a Rafa`ahā Wa Wađa`a Al-Mīzāna  | 055-007 ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ | وَالسَّمَاءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ الْمِيزَانَ |
'Allā Taţghaw Fī Al-Mīzāni  | 055-008 በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡ | أَلاَّ تَطْغَوْا فِي الْمِيزَانِ |
Wa 'Aqīmū Al-Wazna Bil-Qisţi Wa Lā Tukhsirū Al-Mīzāna  | 055-009 መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡ | وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلاَ تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ |
Wa Al-'Arđa Wađa`ahā Lil'anāmi  | 055-010 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ | وَالأَرْضَ وَضَعَهَا لِلأَنَامِ |
Fīhā Fākihatun Wa An-Nakhlu Dhātu Al-'Akmāmi  | 055-011 በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡ | فِيهَا فَاكِهَةٌ وَالنَّخْلُ ذَاتُ الأَكْمَامِ |
Wa Al-Ĥabbu Dhū Al-`Aşfi Wa Ar-Rayĥānu  | 055-012 የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡ | وَالْحَبُّ ذُو الْعَصْفِ وَالرَّيْحَانُ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-013 (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Khalaqa Al-'Insāna Min Şalşālin Kālfakhkhāri  | 055-014 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ | خَلَقَ الإِنسَانَ مِنْ صَلْصَالٍ كَالْفَخَّارِ |
Wa Khalaqa Al-Jānna Min Mārijin Min Nārin  | 055-015 ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡ | وَخَلَقَ الْجَانَّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-016 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Rabbu Al-Mashriqayni Wa Rabbu Al-Maghribayni  | 055-017 የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡ | رَبُّ الْمَشْرِقَيْنِ وَرَبُّ الْمَغْرِبَيْنِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-018 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Maraja Al-Baĥrayni Yaltaqiyāni  | 055-019 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ | مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ |
Baynahumā Barzakhun Lā Yabghiyāni  | 055-020 (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡ | بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لاَ يَبْغِيَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-021 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?â€؛ | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Yakhruju Minhumā Al-Lu'ulu'uu Wa Al-Marjānu  | 055-022 ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡ | يَخْرُجُ مِنْهُمَا اللُّؤْلُؤُ وَالْمَرْجَانُ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-023 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Wa Lahu Al-Jawāri Al-Munsha'ātu Fī Al-Baĥri Kāl'a`lāmi  | 055-024 እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡ | وَلَهُ الْجَوَارِ الْمُنشَآتُ فِي الْبَحْرِ كَالأَعْلاَمِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-025 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Kullu Man `Alayhā Fānin  | 055-026 በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ | كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ |
Wa Yabqá Wajhu Rabbika Dhū Al-Jalāli Wa Al-'Ikrāmi  | 055-027 የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡ | وَيَبْقَى وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-028 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Yas'aluhu Man Fī As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Kulla Yawmin Huwa Fī Sha'nin  | 055-029 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡ | يَسْأَلُهُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ كُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِي شَأْنٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-030 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?â€؛ | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Sanafrughu Lakum 'Ayyuhā Ath-Thaqalāni  | 055-031 እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡ | سَنَفْرُغُ لَكُمْ أَيُّهَا الثَّقَلاَنِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-032 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Yā Ma`shara Al-Jinni Wa Al-'Insi 'Ini Astaţa`tum 'An Tanfudhū Min 'Aqţāri As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Fānfudhū Lā Tanfudhūna 'Illā Bisulţānin  | 055-033 የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም) | يَامَعْشَرَ الْجِنِّ وَالإِنسِ إِنِ اسْتَطَعْتُمْ أَنْ تَنفُذُوا مِنْ أَقْطَارِ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ فَانفُذُوا لاَ تَنفُذُونَ إِلاَّ بِسُلْطَانٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-034 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Yursalu `Alaykumā Shuwāžun Min Nārin Wa Nuĥāsun Falā Tantaşirāni  | 055-035 በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡ | يُرْسَلُ عَلَيْكُمَا شُوَاظٌ مِنْ نَارٍ وَنُحَاسٌ فَلاَ تَنتَصِرَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-036 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fa'idhā Anshaqqati As-Samā'u Fakānat Wardatan Kālddihāni  | 055-037 ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡ | فَإِذَا انشَقَّتِ السَّمَاءُ فَكَانَتْ وَرْدَةً كَالدِّهَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-038 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fayawma'idhin Lā Yus'alu `An Dhanbihi 'Insun Wa Lā Jānnun  | 055-039 በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ | فَيَوْمَئِذٍ لاَ يُسْأَلُ عَنْ ذَنْبِهِ إِنسٌ وَلاَ جَانٌّ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-040 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Yu`rafu Al-Mujrimūna Bisīmāhum Fayu'ukhadhu Bin-Nawāşī Wa Al-'Aqdāmi  | 055-041 ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡ | يُعْرَفُ الْمُجْرِمُونَ بِسِيمَاهُمْ فَيُؤْخَذُ بِالنَّوَاصِي وَالأَقْدَامِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-042 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡ | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Hadhihi Jahannamu Allatī Yukadhdhibu Bihā Al-Mujrimūna  | 055-043 ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡ | هَذِهِ جَهَنَّمُ الَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا الْمُجْرِمُونَ |
Yaţūfūna Baynahā Wa Bayna Ĥamīmin 'Ānin  | 055-044 በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡ | يَطُوفُونَ بَيْنَهَا وَبَيْنَ حَمِيمٍ آنٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-045 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Wa Liman Khāfa Maqāma Rabbihi Jannatāni  | 055-046 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡ | وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-047 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Dhawātā 'Afnānin  | 055-048 የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡ | ذَوَاتَا أَفْنَانٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-049 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhimā `Aynāni Tajriyāni  | 055-050 በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡ | فِيهِمَا عَيْنَانِ تَجْرِيَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-051 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhimā Min Kulli Fākihatin Zawjāni  | 055-052 በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡ | فِيهِمَا مِنْ كُلِّ فَاكِهَةٍ زَوْجَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-053 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Muttaki'īna `Alá Furushin Baţā'inuhā Min 'Istabraqin Wa Janá Al-Jannatayni Dānin  | 055-054 የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡ | مُتَّكِئِينَ عَلَى فُرُشٍ بَطَائِنُهَا مِنْ إِسْتَبْرَقٍ وَجَنَى الْجَنَّتَيْنِ دَانٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-055 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhinna Qāşirātu Aţ-Ţarfi Lam Yaţmithhunna 'Insun Qablahum Wa Lā Jānnun  | 055-056 በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ | فِيهِنَّ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنْسٌ قَبْلَهُمْ وَلاَ جَانٌّ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-057 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Ka'annahunna Al-Yāqūtu Wa Al-Marjānu  | 055-058 ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡ | كَأَنَّهُنَّ الْيَاقُوتُ وَالْمَرْجَانُ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-059 ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Hal Jazā'u Al-'Iĥsāni 'Illā Al-'Iĥsānu  | 055-060 የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን? | هَلْ جَزَاءُ الإِحْسَانِ إِلاَّ الإِحْسَانُ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-061 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Wa Min Dūnihimā Jannatāni  | 055-062 ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡ | وَمِنْ دُونِهِمَا جَنَّتَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-063 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?â€؛ | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Mud/hāmmatāni  | 055-064 ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡ | مُدْهَامَّتَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-065 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhimā `Aynāni Nađđākhatāni  | 055-066 በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡ | فِيهِمَا عَيْنَانِ نَضَّاخَتَانِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-067 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhimā Fākihatun Wa Nakhlun Wa Rummānun  | 055-068 በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡ | فِيهِمَا فَاكِهَةٌ وَنَخْلٌ وَرُمَّانٌ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-069 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Fīhinna Khayrātun Ĥisānun  | 055-070 በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ | فِيهِنَّ خَيْرَاتٌ حِسَانٌ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-071 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Ĥūrun Maqşūrātun Fī Al-Khiyāmi  | 055-072 በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ | حُورٌ مَقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-073 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Lam Yaţmithhunna 'Insun Qablahum Wa Lā Jānnun  | 055-074 ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ | لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنسٌ قَبْلَهُمْ وَلاَ جَانٌّ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-075 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Muttaki'īna `Alá Rafrafin Khuđrin Wa `Abqarīyin Ĥisānin  | 055-076 በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡ | مُتَّكِئِينَ عَلَى رَفْرَفٍ خُضْرٍ وَعَبْقَرِيٍّ حِسَانٍ |
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbikumā Tukadhdhibāni  | 055-077 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? | فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ |
Tabāraka Asmu Rabbika Dhī Al-Jalāli Wa Al-'Ikrāmi  | 055-078 የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡ | تَبَارَكَ اسْمُ رَبِّكَ ذِي الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ |