53) Sūrat An-Najm

Printed format

53) سُورَة النَّجْم

Wa An-Najmi 'Idhā Hawá 053-001 በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡ وَال‍‍ن‍ّ‍‍َ‍‍ج‍‍ْمِ إِذَا هَوَى
Mā Đalla Şāĥibukum Wa Mā Ghawá 053-002 ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَى
Wa Mā Yanţiqu `Ani Al-Hawá 053-003 ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ وَمَا يَ‍‍ن‍‍ْطِقُ عَنِ ا‍لْهَوَى
'In Huwa 'Illā Waĥyun Yūĥá 053-004 እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلاَّ وَحْي‍‍‍ٌ يُوحَى
`Allamahu Shadīdu Al-Quwá 053-005 ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡ عَلَّمَهُ شَد‍ِي‍دُ ا‍لْقُوَى
Dhū Mirratin Fāstawá 053-006 የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡ ذُو مِرَّة‍‍‍ٍ فَاسْتَوَى
Wa Huwa Bil-'Ufuqi Al-'A`lá 053-007 እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡ وَهُوَ بِ‍‍ا‍لأُفُقِ ا‍لأَعْلَى
Thumma Danā Fatadallá 053-008 ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ دَنَا فَتَدَلَّى
Fakāna Qāba Qawsayni 'Aw 'Adná 053-009 (ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡ فَك‍‍َ‍ا‍نَ ق‍‍َ‍ا‍بَ قَوْسَيْنِ أَوْ أَ‍د‍‍ْنَى
Fa'awĥá 'Ilá `Abdihi Mā 'Awĥá 053-010 ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡ فَأَوْحَى إِلَى عَ‍‍ب‍‍ْدِهِ مَ‍‍ا‍ أَوْحَى
Mā Kadhaba Al-Fu'uādu Mā Ra'á 053-011 (ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ مَا كَذَبَ ا‍لْفُؤ‍َا‍دُ مَا رَأَى
'Afatumārūnahu `Alá Mā Yará 053-012 ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? أَفَتُمَارُونَهُ عَلَى مَا يَرَى
Wa Laqad Ra'āhu Nazlatan 'Ukh 053-013 በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡ وَلَقَ‍‍د‍ْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَى
`Inda Sidrati Al-Muntahá 053-014 በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ عِ‍‍ن‍‍ْدَ سِ‍‍د‍‍ْرَةِ ا‍لْمُ‍‍ن‍‍ْتَهَى
`Indahā Jannatu Al-Ma'wá 053-015 እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ عِ‍‍ن‍‍ْدَهَا جَ‍‍ن‍ّ‍‍َةُ ا‍لْمَأْوَى
'Idh Yaghshá As-Sidrata Mā Yaghshá 053-016 ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ إِذْ يَغْشَى ا‍لسِّ‍‍د‍‍ْرَةَ مَا يَغْشَى
Mā Zāgha Al-Başaru Wa Mā Ţaghá 053-017 ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡ مَا ز‍َا‍غَ ا‍لْبَصَرُ وَمَا طَغَى
Laqad Ra'á Min 'Āyāti Rabbihi Al-Kub 053-018 ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡ لَقَ‍‍د‍ْ رَأَى مِ‍‍ن‍ْ آي‍‍َ‍ا‍تِ رَبِّهِ ا‍لْكُ‍‍ب‍‍ْرَى
'Afara'aytumu Al-Lāta Wa Al-`Uzzá 053-019 አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? أَفَرَأَيْتُمُ ا‍للاَّتَ وَا‍لْعُزَّى
Wa Manāata Ath-Thālithata Al-'Ukh 053-020 ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) وَمَن‍‍َ‍ا‍ةَ ا‍لثَّالِثَةَ ا‍لأُخْرَى
'Alakumu Adh-Dhakaru Wa Lahu Al-'Unthá 053-021 ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን? أَلَكُمُ ا‍لذَّكَرُ وَلَهُ ا‍لأُن‍ثَى
Tilka 'Idhāan Qismatun Đīzá 053-022 ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡ تِلْكَ إِذا‍ً قِسْمَة‍‍‍ٌ ضِيزَى
'In Hiya 'Illā 'Asmā'un Sammaytumūhā 'Antum Wa 'Ābā'uukum Mā 'Anzala Al-Lahu Bihā Min Sulţānin 'In Yattabi`ūna 'Illā Až-Žanna Wa Mā Tahwá Al-'Anfusu Wa Laqad Jā'ahum Min Rabbihimu Al-Hudá 053-023 እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡ إِنْ هِيَ إِلاَّ أَسْم‍‍َ‍ا‍ء‍ٌ سَ‍‍م‍ّ‍‍َيْتُمُوهَ‍‍ا‍ أَ‍ن‍‍ْتُمْ وَآب‍‍َ‍ا‍ؤُكُ‍‍م‍ْ مَ‍‍ا‍ أَن‍زَلَ ا‍للَّهُ بِهَا مِ‍‍ن‍ْ سُلْط‍‍َ‍ا‍ن‍‍‍ٍ إِ&
'Am Lil'insāni Mā Tamanná 053-024 ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን? أَمْ لِلإِن‍س‍‍َ‍ا‍نِ مَا تَمَ‍‍ن‍ّ‍‍َى
Falillāhi Al-'Ākhiratu Wa Al-'Ū 053-025 መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ فَلِلَّهِ ا‍لآخِرَةُ وَا‍لأ‍ُ‍ولَى
Wa Kam Min Malakin As-Samāwāti Lā TughShafā`atuhum Shay'āan 'Illā Min Ba`di 'An Ya'dhana Al-Lahu Liman Yashā'u Wa Yarđá 053-026 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَ‍‍م‍ْ مِ‍‍ن‍ْ مَلَك‍‍‍ٍ فِي ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ لاَ تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئا‍ً إِلاَّ مِ‍‍ن‍ْ بَعْدِ أَ‍ن‍ْ يَأْذَنَ ا‍للَّهُ لِمَ‍‍ن‍ْ يَش‍‍َ‍ا‍ءُ وَيَرْضَى
'Inna Al-Ladhīna Lā Yu'uminūna Bil-'Ākhirati Layusammūna Al-Malā'ikata Tasmiyata Al-'Unthá 053-027 እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡ إِ‍نّ‍‍َ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ لاَ يُؤْمِن‍‍ُ‍و‍نَ بِ‍‍ا‍لآخِرَةِ لَيُسَ‍‍م‍ّ‍‍ُ‍و‍نَ ا‍لْمَلاَئِكَةَ تَسْمِيَةَ ا‍لأُ‍ن‍‍ْثَى
Wa Mā Lahum Bihi Min `Ilmin 'In Yattabi`ūna 'Illā Až-Žanna Wa 'Inna Až-Žanna Lā Yughnī Mina Al-Ĥaqqi Shay'āan 053-028 ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ وَمَا لَهُ‍‍م‍ْ بِهِ مِنْ عِلْم‍‍‍ٍ إِ‍ن‍ْ يَتَّبِع‍‍ُ‍و‍نَ إِلاَّ ا‍لظَّ‍‍ن‍ّ‍‍َ وَإِ‍نّ‍‍َ ا‍لظَّ‍‍ن‍ّ‍‍َ لاَ يُغْنِي مِنَ ا‍لْحَقِّ شَيْئا‍ً
Fa'a`riđ `An Man Tawallá `An Dhikrinā Wa Lam Yurid 'Illā Al-Ĥayāata Ad-Dun 053-029 ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡ فَأَعْ‍‍ر‍‍ِضْ عَ‍‍ن‍ْ مَ‍‍ن‍ْ تَوَلَّى عَ‍‍ن‍ْ ذِكْ‍‍ر‍‍ِنَا وَلَمْ يُ‍‍ر‍‍ِ‍د‍ْ إِلاَّ ا‍لْحَي‍‍َ‍ا‍ةَ ا‍لدُّ‍‍ن‍‍ْيَا
Dhālika Mablaghuhum Mina Al-`Ilmi 'Inna Rabbaka Huwa 'A`lamu Biman Đalla `An Sabīlihi Wa Huwa 'A`lamu Bimani Ahtadá 053-030 ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ ذَلِكَ مَ‍‍ب‍‍ْلَغُهُ‍‍م‍ْ مِنَ ا‍لْعِلْمِ إِ‍نّ‍‍َ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَ‍‍ن‍ْ ضَلَّ عَ‍‍ن‍ْ سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ ا‍هْتَدَى
Wa Lillahi Mā Fī As-Samāwāti Wa Mā Fī Al-'Arđi Liyajziya Al-Ladhīna 'Asā'ū Bimā `Amilū Wa Yajziya Al-Ladhīna 'Aĥsanū Bil-Ĥusná 053-031 በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡ وَلِلَّهِ مَا فِي ا‍لسَّمَاو‍َا‍تِ وَمَا فِي ا‍لأَرْضِ لِيَ‍‍ج‍‍ْزِيَ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ أَس‍‍َ‍ا‍ء‍ُ‍وا بِمَا عَمِلُو‍‍ا‍ وَيَ‍‍ج‍‍ْزِيَ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ أَحْسَنُو‍‍ا‍ بِ‍‍ا‍لْحُسْنَى
Al-Ladhīna Yajtanibūna Kabā'ira Al-'Ithmi Wa Al-Fawāĥisha 'Illā Al-Lamama 'Inna Rabbaka Wāsi`u Al-Maghfirati Huwa 'A`lamu Bikum 'Idh 'Ansha'akum Mina Al-'Arđi Wa 'Idh 'Antum 'Ajinnatun Fī Buţūni 'Ummahātikum Falā Tuzakkū 'Anfusakum Huwa 'A`lamu Bimani Attaqá 053-032 (እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ ا‍لَّذ‍ِي‍نَ يَ‍‍ج‍‍ْتَنِب‍‍ُ‍و‍نَ كَب‍‍َ‍ا‍ئِ‍‍ر‍َ ا‍لإِثْمِ وَا‍لْفَوَاحِشَ إِلاَّ ا‍للَّمَمَ إِ‍نّ‍‍َ رَبَّكَ وَ 'Afara'ayta Al-Ladhī Tawallá 053-033 ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን? أَفَرَأَيْتَ ا‍لَّذِي تَوَلَّى
Wa 'A`ţá Qalīlāan Wa 'Akdá 053-034 ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?) وَأَعْطَى قَلِيلا‍ً وَأَكْدَى
'A`indahu `Ilmu Al-Ghaybi Fahuwa Yará 053-035 የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን? أَعِ‍‍ن‍‍ْدَهُ عِلْمُ ا‍لْغَيْبِ فَهُوَ يَرَى
'Am Lam Yunabba' Bimā Fī Şuĥufi Mūsá 053-036 ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَى
Wa 'Ibrāhīma Al-Ladhī Wa Ffá 053-037 በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) وَإِ‍ب‍‍ْرَاه‍‍ِ‍ي‍مَ ا‍لَّذِي وَفَّى
'Allā Taziru Wāziratun Wizra 'Ukh 053-038 (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ أَلاَّ تَزِ‍ر‍ُ وَا‍زِرَة‍‍‍ٌ وِزْرَ أُخْرَى
Wa 'An Laysa Lil'insāni 'Illā Mā Sa`á 053-039 ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ وَأَ‍ن‍ْ لَيْسَ لِلإِن‍س‍‍َ‍ا‍نِ إِلاَّ مَا سَعَى
Wa 'Anna Sa`yahu Sawfa Yurá 053-040 ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَى
Thumma Yujzāhu Al-Jazā'a Al-'Awfá 053-041 ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡ ثُ‍‍م‍ّ‍‍َ يُ‍‍ج‍‍ْز‍َا‍هُ ا‍لْجَز‍َا‍ءَ ا‍لأَوْفَى
Wa 'Anna 'Ilá Rabbika Al-Muntahá 053-042 መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َ إِلَى رَبِّكَ ا‍لْمُ‍‍ن‍‍ْتَهَى
Wa 'Annahu Huwa 'Ađĥaka Wa 'Ab 053-043 እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ هُوَ أَضْحَكَ وَأَ‍ب‍‍ْكَى
Wa 'Annahu Huwa 'Amāta Wa 'Aĥyā 053-044 እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ هُوَ أَم‍‍َ‍ا‍تَ وَأَحْيَا
Wa 'Annahu Khalaqa Az-Zawjayni Adh-Dhakara Wa Al-'Unthá 053-045 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ خَلَقَ ا‍لزَّوْجَيْنِ ا‍لذَّكَرَ وَا‍لأُ‍ن‍‍ْثَى
Min Nuţfatin 'Idhā Tumná 053-046 ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ مِ‍‍ن‍ْ نُ‍‍ط‍‍ْفَة‍‍‍ٍ إِذَا تُمْنَى
Wa 'Anna `Alayhi An-Nash'ata Al-'Ukh 053-047 የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َ عَلَيْهِ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍َشْأَةَ ا‍لأُخْرَى
Wa 'Annahu Huwa 'Aghná Wa 'Aqná 053-048 እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ هُوَ أَغْنَى وَأَ‍ق‍‍ْنَى
Wa 'Annahu Huwa Rabbu Ash-Shi`rá 053-049 እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ هُوَ رَبُّ ا‍لشِّعْرَى
Wa 'Annahu 'Ahlaka `Ādāan Al-'Ū 053-050 እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡ وَأَ‍نّ‍‍َهُ أَهْلَكَ عَادا‍ً ا‍لأ‍ُ‍ولَى
Wa Thamūda Famā 'Abqá 053-051 ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡ وَثَم‍‍ُ‍و‍دَ فَمَ‍‍ا‍ أَ‍ب‍‍ْقَى
Wa Qawma Nūĥin Min Qablu 'Innahum Kānū Hum 'Ažlama Wa 'Aţghá 053-052 በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡ وَقَوْمَ ن‍‍ُ‍و‍ح‍‍‍ٍ مِ‍‍ن‍ْ قَ‍‍ب‍‍ْلُ إِ‍نّ‍‍َهُمْ كَانُو‍‍ا‍ هُمْ أَظْلَمَ وَأَ‍ط‍‍ْغَى
Wa Al-Mu'utafikata 'Ahwá 053-053 የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡ وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَى
Faghashshāhā Mā Ghashshá 053-054 ያለበሳትንም አለበሳት፡፡ فَغَشَّاهَا مَا غَشَّى
Fabi'ayyi 'Ālā'i Rabbika Tatamārá 053-055 ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ? فَبِأَيِّ آلاَءِ رَبِّكَ تَتَمَارَى
dhā Nadhīrun Mina An-Nudhuri Al-'Ū 053-056 ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡ هَذَا نَذ‍ِي‍ر‍ٌ مِنَ ا‍ل‍‍ن‍ّ‍‍ُذُ‍ر‍ِ ا‍لأ‍ُ‍ولَى
'Azifati Al-'Āzifahu 053-057 ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡ أَزِفَتِ ا‍لآزِفَةُ
Laysa Lahā Min Dūni Al-Lahi Kāshifahun 053-058 ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡ لَيْسَ لَهَا مِ‍‍ن‍ْ د‍ُو‍نِ ا‍للَّهِ كَاشِفَة‍‍‍ٌ
'Afamin Hādhā Al-Ĥadīthi Ta`jabūna 053-059 ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን? أَفَمِنْ هَذَا ا‍لْحَد‍ِي‍ثِ تَعْجَب‍‍ُ‍و‍نَ
Wa Tađĥakūna Wa Lā Tabkūna 053-060 ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? وَتَضْحَك‍‍ُ‍و‍نَ وَلاَ تَ‍‍ب‍‍ْك‍‍ُ‍و‍نَ
Wa 'Antum Sāmidūna 053-061 እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ وَأَ‍ن‍‍ْتُمْ سَامِد‍ُو‍نَ
Fāsjudū Lillahi Wa A`budū 053-062 ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ فَاسْجُدُوا‍ لِلَّهِ وَا‍عْبُدُوا‍
Next Sūrah