Qāf Wa Al-Qur'āni Al-Majīdi  | 050-001 ቀ (ቃፍ) በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ (በሙሐመድ አላመኑም)፡፡ | قَاف وَالْقُرْآنِ الْمَجِيدِ |
Bal `Ajibū 'An Jā'ahum Mundhirun Minhum Faqāla Al-Kāfirūna Hādhā Shay'un `Ajībun  | 050-002 ይልቁንም ከነሱ ጎሳ የኾነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም آ«ይህ አስደናቂ ነገር ነውآ» አሉ፡፡ | بَلْ عَجِبُوا أَنْ جَاءَهُمْ مُنْذِرٌ مِنْهُمْ فَقَالَ الْكَافِرُونَ هَذَا شَيْءٌ عَجِيبٌ |
'A'idhā Mitnā Wa Kunnā Turābāan Dhālika Raj`un Ba`īdun  | 050-003 آ«በሞትንና ዐፈር በኾን ጊዜ (እንመለሳለን?) ይህ ሩቅ የኾነ መመለስ ነው፤آ» (አሉ)፡፡ | أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَاباً ذَلِكَ رَجْعٌ بَعِيدٌ |
Qad `Alimnā Mā Tanquşu Al-'Arđu Minhum Wa `Indanā Kitābun Ĥafīžun  | 050-004 ከእነርሱ (አካል) ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አልለ፡፡ | قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنْقُصُ الأَرْضُ مِنْهُمْ وَعِنْدَنَا كِتَابٌ حَفِيظٌ |
Bal Kadhdhabū Bil-Ĥaqqi Lammā Jā'ahum Fahum Fī 'Amrin Marījin  | 050-005 (አልተመለከቱም)፡፡ ይልቁንም በቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ፡፡ እነርሱም በተማታ ነገር ውሰጥ ናቸው፡፡ | بَلْ كَذَّبُوا بِالْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ فَهُمْ فِي أَمْرٍ مَرِيجٍ |
'Afalam Yanžurū 'Ilá As-Samā'i Fawqahum Kayfa Banaynāhā Wa Zayyannāhā Wa Mā Lahā Min Furūjin  | 050-006 ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትኾን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏት ኾና እንዴት እንደ ገነባናትና (በከዋክብት) እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን? | أَفَلَمْ يَنْظُرُوا إِلَى السَّمَاءِ فَوْقَهُمْ كَيْفَ بَنَيْنَاهَا وَزَيَّنَّاهَا وَمَا لَهَا مِنْ فُرُوجٍ |
Wa Al-'Arđa Madadnāhā Wa 'Alqaynā Fīhā Rawāsiya Wa 'Anbatnā Fīhā Min Kulli Zawjin Bahījin  | 050-007 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ በውስጧም ከሚያስደስት ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ | وَالأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْبَتْنَا فِيهَا مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ |
Tabşiratan Wa Dhikrá Likulli `Abdin Munībin  | 050-008 (ይህንን ያደረግነው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው፡፡ | تَبْصِرَةً وَذِكْرَى لِكُلِّ عَبْدٍ مُنِيبٍ |
Wa Nazzalnā Mina As-Samā'i Mā'an Mubārakāan Fa'anbatnā Bihi Jannātin Wa Ĥabba Al-Ĥaşīdi  | 050-009 ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን (አዝመራ) ፍሬ አበቀልን፡፡ | وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُبَارَكاً فَأَنْبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ |
Wa An-Nakhla Bāsiqātin Lahā Ţal`un Nađīdun  | 050-010 ዘምባባንም ረዣዢም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትኾን (አበቀልን)፡፡ | وَالنَّخْلَ بَاسِقَاتٍ لَهَا طَلْعٌ نَضِيدٌ |
Rizqāan Lil`ibādi Wa 'Aĥyaynā Bihi Baldatan Maytāan Kadhālika Al-Khurūju  | 050-011 ለባሮቹ ሲሳይ ትኾን ዘንድ (አዘጋጀናት)፡፡ በእርሱም የሞተችን አገር ሕያው አደረግንበት፡፡ (ከመቃብር) መውጣትም እንደዚሁ ነው፡፡ | رِزْقاً لِلْعِبَادِ وَأَحْيَيْنَا بِهِ بَلْدَةً مَيْتاً كَذَلِكَ الْخُرُوجُ |
Kadhdhabat Qablahum Qawmu Nūĥin Wa 'Aşĥābu Ar-Rassi Wa Thamūdu  | 050-012 ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦችና የረሰስ ሰዎች፤ ሰሙድም አስተባበሉ፡፡ | كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَأَصْحَابُ الرَّسِّ وَثَمُودُ |
Wa `Ādun Wa Fir`awnu Wa 'Ikhwānu Lūţin  | 050-013 ዓድም ፈርዖንም፤ የሉጥ ወንድሞችም፤ | وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ وَإِخْوَانُ لُوطٍ |
Wa 'Aşĥābu Al-'Aykati Wa Qawmu Tubba`in Kullun Kadhdhaba Ar-Rusula Faĥaqqa Wa`īdi  | 050-014 የአይከት ሰዎችም የቱብበዕ ሕዝቦችም ሁሉም መልከተኞቹን አስተባበሉ፡፡ ዛቻዬም ተረጋገጠባቸው፡፡ | وَأَصْحَابُ الأَيْكَةِ وَقَوْمُ تُبَّعٍ كُلٌّ كَذَّبَ الرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ |
'Afa`ayīnā Bil-Khalqi Al-'Awwali Bal Hum Fī Labsin Min Khalqin Jadīdin  | 050-015 በፊተኛው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ | أَفَعَيِينَا بِالْخَلْقِ الأَوَّلِ بَلْ هُمْ فِي لَبْسٍ مِنْ خَلْقٍ جَدِيدٍ |
Wa Laqad Khalaqnā Al-'Insāna Wa Na`lamu Mā Tuwaswisu Bihi Nafsuhu Wa Naĥnu 'Aqrabu 'Ilayhi Min Ĥabli Al-Warīdi  | 050-016 ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡ | وَلَقَدْ خَلَقْنَا الإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ |
'Idh Yatalaqqá Al-Mutalaqqiyāni `Ani Al-Yamīni Wa `Ani Ash-Shimāli Qa`īdun  | 050-017 ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ | إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ |
Mā Yalfižu Min Qawlin 'Illā Ladayhi Raqībun `Atīdun  | 050-018 ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡ | مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلاَّ لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ |
Wa Jā'at Sakratu Al-Mawti Bil-Ĥaqqi Dhālika Mā Kunta Minhu Taĥīdu  | 050-019 የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች፡፡ (ሰው ሆይ)፡- آ«ይህ ያ ከርሱ ትሸሸው የነበርከው ነውآ» (ይባላል)፡፡ | وَجَاءَتْ سَكْرَةُ الْمَوْتِ بِالْحَقِّ ذَلِكَ مَا كُنْتَ مِنْهُ تَحِيدُ |
Wa Nufikha Fī Aş-Şūri Dhālika Yawmu Al-Wa`īdi  | 050-020 በቀንዱም ውስጥ ይንነፋል፡፡ ያ (ቀን) የዛቻው (መፈጸሚያ) ቀን ነው፡፡ | وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ذَلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ |
Wa Jā'at Kullu Nafsin Ma`ahā Sā'iqun Wa Shahīdun  | 050-021 ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጂና መስካሪ ያለባት ኾና ትመጣለች፡፡ | وَجَاءَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَعَهَا سَائِقٌ وَشَهِيدٌ |
Laqad Kunta Fī Ghaflatin Min Hādhā Fakashafnā `Anka Ghiţā'aka Fabaşaruka Al-Yawma Ĥadīdun  | 050-022 آ«ከዚህ ነገር በእርግጥ በዝንጋቴ ውስጥ ነበርክ፡፡ ሺፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነውآ» (ይባላል)፡፡ | لَقَدْ كُنْتَ فِي غَفْلَةٍ مِنْ هَذَا فَكَشَفْنَا عَنْكَ غِطَاءَكَ فَبَصَرُكَ الْيَوْمَ حَدِيدٌ |
Wa Qāla Qarīnuhu Hādhā Mā Ladayya `Atīdun  | 050-023 ቁራኛውም (መልአክ) آ«ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነውآ» ይላል፡፡ | وَقَالَ قَرِينُهُ هَذَا مَا لَدَيَّ عَتِيدٌ |
'Alqiyā Fī Jahannama Kulla Kaffārin `Anīdin  | 050-024 آ«ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ፡፡آ» | أَلْقِيَا فِي جَهَنَّمَ كُلَّ كَفَّارٍ عَنِيدٍ |
Mannā`in Lilkhayri Mu`tadin Murībin  | 050-025 آ«ለበጎ ሥራ ከልካይ፣ በዳይ፣ ተጠራጣሪ የኾነን ሁሉ፤آ» (ጣሉ)፡፡ | مَنَّاعٍ لِلْخَيْرِ مُعْتَدٍ مُرِيبٍ |
Al-Ladhī Ja`ala Ma`a Al-Lahi 'Ilahāan 'Ākhara Fa'alqiyāhu Fī Al-`Adhābi Ash-Shadīdi  | 050-026 آ«ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት፤آ» (ይባላል)፡፡ | الَّذِي جَعَلَ مَعَ اللَّهِ إِلَهاً آخَرَ فَأَلْقِيَاهُ فِي الْعَذَابِ الشَّدِيدِ |
Qāla Qarīnuhu Rabbanā Mā 'Aţghaytuhu Wa Lakin Kāna Fī Đalālin Ba`īdin  | 050-027 ቁራኛው (ሰይጣን) آ«ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም፡፡ ግን (ራሱ) በሩቅ ስሕተት ውስጥ ነበርآ» ይላል፡፡ | قَالَ قَرِينُهُ رَبَّنَا مَا أَطْغَيْتُهُ وَلَكِنْ كَانَ فِي ضَلاَلٍ بَعِيدٍ |
Qāla Lā Takhtaşimū Ladayya Wa Qad Qaddamtu 'Ilaykum Bil-Wa`īdi  | 050-028 (አላህ) آ«ወደእናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁآ» ይላቸዋል፡፡ | قَالَ لاَ تَخْتَصِمُوا لَدَيَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُمْ بِالْوَعِيدِ |
Mā Yubaddalu Al-Qawlu Ladayya Wa Mā 'Anā Bižallāmin Lil`abīdi  | 050-029 آ«ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም፡፡ እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁምآ» (ይላቸዋል)፡፡ | مَا يُبَدَّلُ الْقَوْلُ لَدَيَّ وَمَا أَنَا بِظَلاَّمٍ لِلْعَبِيدِ |
Yawma Naqūlu Lijahannama Hal Amtala'ti Wa Taqūlu Hal Min Mazīdin  | 050-030 ለገሀነም آ«ሞላሽን? የምንልበትንና ጭማሪ አለን? የምትልበትን ቀንآ» (አስጠንቅቃቸው)፡፡ | يَوْمَ نَقُولُ لِجَهَنَّمَ هَلْ امْتَلَأْتِ وَتَقُولُ هَلْ مِنْ مَزِيدٍ |
Wa 'Uzlifati Al-Jannatu Lilmuttaqīna Ghayra Ba`īdin  | 050-031 ገነትም አላህን ለፈሩት እሩቅ ባልኾነ ስፍራ ትቅቀረባለች፡፡ | وَأُزْلِفَتِ الْجَنَّةُ لِلْمُتَّقِينَ غَيْرَ بَعِيدٍ |
Hādhā Mā Tū`adūna Likulli 'Awwābin Ĥafīžin  | 050-032 آ«ይህ ወደ አላህ ተመላሽና (ሕግጋቱን) ጠባቂ ለኾነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነውآ» (ይባላሉ)፡፡ | هَذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِيظٍ |
Man Khashiya Ar-Raĥmana Bil-Ghaybi Wa Jā'a Biqalbin Munībin  | 050-033 آ«አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራና በንጹሕ ልብ ለመጣآ» (ትቅቀረባለች)፡፡ | مَنْ خَشِيَ الرَّحْمَنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُنِيبٍ |
Adkhulūhā Bisalāmin Dhālika Yawmu Al-Khulūdi  | 050-034 آ«በሰላም ግቧት ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነውآ» (ይባላሉ)፡፡ | ادْخُلُوهَا بِسَلاَمٍ ذَلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ |
Lahum Mā Yashā'ūna Fīhā Wa Ladaynā Mazīdun  | 050-035 ለነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡ | لَهُمْ مَا يَشَاءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ |
Wa Kam 'Ahlaknā Qablahum Min Qarnin Hum 'Ashaddu Minhum Baţshāan Fanaqqabū Fī Al-Bilādi Hal Min Maĥīşin  | 050-036 ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን እነርሱ በኀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ የኾኑትን (ማምለጫ ፍለጋ) በየአገሮቹም የመረመሩትን አጥፍተናል፡፡ ማምለጫ አለን? | وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُمْ مِنْ قَرْنٍ هُمْ أَشَدُّ مِنْهُمْ بَطْشاً فَنَقَّبُوا فِي الْبِلاَدِ هَلْ مِنْ مَحِيصٍ |
'Inna Fī Dhālika Ladhikrá Liman Kāna Lahu Qalbun 'Aw 'Alqá As-Sam`a Wa Huwa Shahīdun  | 050-037 በዚህ ውሰጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ (በልቡ) የተጣደ ኾኖ (ወደሚነበብለት) ጆሮውን ለጣለ ሰው ግሳጼ አለበት፡፡ | إِنَّ فِي ذَلِكَ لَذِكْرَى لِمَنْ كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ |
Wa Laqad Khalaqnā As-Samāwāti Wa Al-'Arđa Wa Mā Baynahumā Fī Sittati 'Ayyāmin Wa Mā Massanā Min Lughūbin  | 050-038 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ | وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِنْ لُغُوبٍ |
Fāşbir `Alá Mā Yaqūlūna Wa Sabbiĥ Biĥamdi Rabbika Qabla Ţulū`i Ash-Shamsi Wa Qabla Al-Ghurūbi  | 050-039 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡ | فَاصْبِرْ عَلَى مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ |
Wa Mina Al-Layli Fasabbiĥhu Wa 'Adbāra As-Sujūdi  | 050-040 ከሌሊቱም አወድሰው ከስግደቶችም በኋላዎች (አወድሰው)፡፡ | وَمِنَ اللَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَأَدْبَارَ السُّجُودِ |
Wa Astami` Yawma Yunādi Al-Munādi Min Makānin Qarībin  | 050-041 (የሚነገርህን) አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን (ከመቃብራቸው ይወጣሉ)፡፡ | وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِنْ مَكَانٍ قَرِيبٍ |
Yawma Yasma`ūna Aş-Şayĥata Bil-Ĥaqqi Dhālika Yawmu Al-Khurūji  | 050-042 ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ (ከመቃብር) የመውጫው ቀን ነው፡፡ | يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ذَلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ |
'Innā Naĥnu Nuĥyī Wa Numītu Wa 'Ilaynā Al-Maşīru  | 050-043 እኛ እኛው ሕያው እናደርጋለን፡፡ እንገድላለንም፡፡ መመለሻም ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ | إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَإِلَيْنَا الْمَصِيرُ |
Yawma Tashaqqaqu Al-'Arđu `Anhum Sirā`āan Dhālika Ĥashrun `Alaynā Yasīrun  | 050-044 የሚፈጥኑ ኾነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫው ቀን ነው)፡፡ ይህ በእኛ ላይ ገር የኾነ መሰብሰብ ነው፡፡ | يَوْمَ تَشَقَّقُ الأَرْضُ عَنْهُمْ سِرَاعاً ذَلِكَ حَشْرٌ عَلَيْنَا يَسِيرٌ |
Naĥnu 'A`lamu Bimā Yaqūlūna Wa Mā 'Anta `Alayhim Bijabbārin Fadhakkir Bil-Qur'āni Man Yakhāfu Wa`īdi  | 050-045 /p> | نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ وَمَا أَنْتَ عَلَيْهِمْ بِجَبَّارٍ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَنْ يَخَافُ وَعِيدِ |