Wa Adh-Dhāriyāti Dharwan  | 051-001 መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡ | وَالذَّارِيَاتِ ذَرْواً |
Fālĥāmilāti Wiqrāan  | 051-002 ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡ | فَالْحَامِلاَتِ وِقْراً |
Fāljāriyāti Yusrāan  | 051-003 ገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡ | فَالْجَارِيَاتِ يُسْراً |
Fālmuqassimāti 'Amrāan  | 051-004 ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡ | فَالْمُقَسِّمَاتِ أَمْراً |
'Innamā Tū`adūna Laşādiqun  | 051-005 የምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡ | إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٌ |
Wa 'Inna Ad-Dīna Lawāqi`un  | 051-006 (እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡ | وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ |
Wa As-Samā'i Dhāti Al-Ĥubuki  | 051-007 የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ | وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْحُبُكِ |
'Innakum Lafī Qawlin Mukhtalifin  | 051-008 እናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡ | إِنَّكُمْ لَفِي قَوْلٍ مُخْتَلِفٍ |
Yu'ufaku `Anhu Man 'Ufika  | 051-009 ከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡ | يُؤْفَكُ عَنْهُ مَنْ أُفِكَ |
Qutila Al-Kharrāşūna  | 051-010 በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡ | قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ |
Al-Ladhīna Hum Fī Ghamratin Sāhūna  | 051-011 እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡ | الَّذِينَ هُمْ فِي غَمْرَةٍ سَاهُونَ |
Yas'alūna 'Ayyāna Yawmu Ad-Dīni  | 051-012 የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡ | يَسْأَلُونَ أَيَّانَ يَوْمُ الدِّينِ |
Yawma Hum `Alá An-Nāri Yuftanūna  | 051-013 (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡ | يَوْمَ هُمْ عَلَى النَّارِ يُفْتَنُونَ |
Dhūqū Fitnatakum Hādhā Al-Ladhī Kuntum Bihi Tasta`jilūna  | 051-014 آ«መከራችሁን ቅመሱ፤ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነውآ» (ይባላሉ)፡፡ | ذُوقُوا فِتْنَتَكُمْ هَذَا الَّذِي كُنتُمْ بِهِ تَسْتَعْجِلُونَ |
'Inna Al-Muttaqīna Fī Jannātin Wa `Uyūnin  | 051-015 አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ | إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
'Ākhidhīna Mā 'Ātāhum Rabbuhum 'Innahum Kānū Qabla Dhālika Muĥsinīna  | 051-016 ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡ | آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَلِكَ مُحْسِنِينَ |
Kānū Qalīlāan Mina Al-Layli Mā Yahja`ūna  | 051-017 ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡ | كَانُوا قَلِيلاً مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ |
Wa Bil-'Asĥāri Hum Yastaghfirūna  | 051-018 በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ | وَبِالأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ |
Wa Fī 'Amwālihim Ĥaqqun Lilssā'ili Wa Al-Maĥrūmi  | 051-019 በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡ | وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ |
Wa Fī Al-'Arđi 'Āyātun Lilmūqinīna  | 051-020 በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡ | وَفِي الأَرْضِ آيَاتٌ لِلْمُوقِنِينَ |
Wa Fī 'Anfusikum 'Afalā Tubşirūna  | 051-021 በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?â€؛ | وَفِي أَنفُسِكُمْ أَفَلاَ تُبْصِرُونَ |
Wa Fī As-Samā'i Rizqukum Wa Mā Tū`adūna  | 051-022 ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው፡፡ | وَفِي السَّمَاءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ |
Fawarabbi As-Samā'i Wa Al-'Arđi 'Innahu Laĥaqqun Mithla Mā 'Annakum Tanţiqūna  | 051-023 በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ ነው፡፡ | فَوَرَبِّ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ إِنَّهُ لَحَقٌّ مِثْلَ مَا أَنَّكُمْ تَنطِقُونَ |
Hal 'Atāka Ĥadīthu Đayfi 'Ibrāhīma Al-Mukramīna  | 051-024 የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? | هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ |
'Idh Dakhalū `Alayhi Faqālū Salāmāan Qāla Salāmun Qawmun Munkarūna  | 051-025 በእርሱ ላይ በገቡና آ«ሰለምآ» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ آ«ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤آ» አላቸው፡፡ | إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلاَماً قَالَ سَلاَمٌ قَوْمٌ مُنكَرُونَ |
Farāgha 'Ilá 'Ahlihi Fajā'a Bi`ijlin Samīnin  | 051-026 ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤آ» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ፡፡ | فَرَاغَ إِلَى أَهْلِهِ فَجَاءَ بِعِجْلٍ سَمِينٍ |
Faqarrabahu 'Ilayhim Qāla 'Alā Ta'kulūna  | 051-027 ወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ آ«አትበሉም ወይ?آ» አላቸው፡፡ | فَقَرَّبَهُ إِلَيْهِمْ قَالَ أَلاَ تَأْكُلُونَ |
Fa'awjasa Minhum Khīfatan Qālū Lā Takhaf Wa Bashsharūhu Bighulāmin `Alīmin  | 051-028 ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ آ«አትፍራآ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡ | فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً قَالُوا لاَ تَخَفْ وَبَشَّرُوهُ بِغُلاَمٍ عَلِيمٍ |
Fa'aqbalati Amra'atuhu Fī Şarratin Faşakkat Wajhahā Wa Qālat `Ajūzun `Aqīmun  | 051-029 ሚስቱም እየጮኸች መጣች፡፡ ፊቷንም መታች፡፡ آ«መካን አሮጊት ነኝآ» አለችም፡፡ | فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ |
Qālū Kadhāliki Qāla Rabbuki 'Innahu Huwa Al-Ĥakīmu Al-`Alīmu  | 051-030 እንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ آ«እነሆ እርሱ ጥበባ ዐዋቂ ነውናآ» አሏት፡፡ | قَالُوا كَذَلِكِ قَالَ رَبُّكِ إِنَّهُ هُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ |
Qāla Famā Khaţbukum 'Ayyuhā Al-Mursalūna  | 051-031 آ«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?آ» አላቸው፡፡ | قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ |
Qālū 'Innā 'Ursilnā 'Ilá Qawmin Mujrimīna  | 051-032 (እነርሱም) አሉ፡- آ«እኛ ወደ አመጸኞች ሕዝቦች ተልከናል፡፡آ» | قَالُوا إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَى قَوْمٍ مُجْرِمِينَ |
Linursila `Alayhim Ĥijāratan Min Ţīnin  | 051-033 በእነርሱ ላይ ከጭቃ የኾኑን ድንጋዮች ልንለቅባቸው (ተላክን)፡፡ | لِنُرْسِلَ عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِنْ طِينٍ |
Musawwamatan `Inda Rabbika Lilmusrifīna  | 051-034 በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትኾን፡፡ | مُسَوَّمَةً عِنْدَ رَبِّكَ لِلْمُسْرِفِينَ |
Fa'akhrajnā Man Kāna Fīhā Mina Al-Mu'uminīna  | 051-035 ከምእምናንም፤ በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን፡፡ | فَأَخْرَجْنَا مَنْ كَانَ فِيهَا مِنَ الْمُؤْمِنِينَ |
Famā Wajadnā Fīhā Ghayra Baytin Mina Al-Muslimīna  | 051-036 በውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም፡፡ | فَمَا وَجَدْنَا فِيهَا غَيْرَ بَيْتٍ مِنَ الْمُسْلِمِينَ |
Wa Taraknā Fīhā 'Āyatan Lilladhīna Yakhāfūna Al-`Adhāba Al-'Alīma  | 051-037 በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን፡፡ | وَتَرَكْنَا فِيهَا آيَةً لِلَّذِينَ يَخَافُونَ الْعَذَابَ الأَلِيمَ |
Wa Fī Mūsá 'Idh 'Arsalnāhu 'Ilá Fir`awna Bisulţānin Mubīnin  | 051-038 በሙሳም (ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)፡፡ | وَفِي مُوسَى إِذْ أَرْسَلْنَاهُ إِلَى فِرْعَوْنَ بِسُلْطَانٍ مُبِينٍ |
Fatawallá Biruknihi Wa Qāla Sāĥirun 'Aw Majnūnun  | 051-039 ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፡፡ (እርሱ) آ«ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነውآ» አለም፡፡ | فَتَوَلَّى بِرُكْنِهِ وَقَالَ سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ |
Fa'akhadhnāhu Wa Junūdahu Fanabadhnāhum Fī Al-Yammi Wa Huwa Mulīmun  | 051-040 እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፡፡ እርሱ ተወቃሽ ሲኾን በባሕር ውስጥም ጣልናቸው፡፡ | فَأَخَذْنَاهُ وَجُنُودَهُ فَنَبَذْنَاهُمْ فِي الْيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٌ |
Wa Fī `Ādin 'Idh 'Arsalnā `Alayhimu Ar-Rīĥa Al-`Aqīma  | 051-041 በዓድም በእነርሱ ላይ መካንን ነፋስ በላክን ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡ | وَفِي عَادٍ إِذْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الرِّيحَ الْعَقِيمَ |
Mā Tadharu Min Shay'in 'Atat `Alayhi 'Illā Ja`alat/hu Kālrramīmi  | 051-042 በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትኾን እንጂ አትተወውም፡፡ | مَا تَذَرُ مِنْ شَيْءٍ أَتَتْ عَلَيْهِ إِلاَّ جَعَلَتْهُ كَالرَّمِيمِ |
Wa Fī Thamūda 'Idh Qīla Lahum Tamatta`ū Ĥattá Ĥīnin  | 051-043 በሰሙድም ለእነርሱ آ«እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙآ» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡ | وَفِي ثَمُودَ إِذْ قِيلَ لَهُمْ تَمَتَّعُوا حَتَّى حِينٍ |
Fa`ataw `An 'Amri Rabbihim Fa'akhadhat/humu Aş-Şā`iqatu Wa Hum Yanžurūna  | 051-044 ከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ፡፡ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው፡፡ | فَعَتَوْا عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ فَأَخَذَتْهُمُ الصَّاعِقَةُ وَهُمْ يَنظُرُونَ |
Famā Astaţā`ū Min Qiyāmin Wa Mā Kānū Muntaşirīna  | 051-045 መቆምንም ምንም አልቻሉም፡፡ የሚርረዱም አልነበሩም፡፡ | فَمَا اسْتَطَاعُوا مِنْ قِيَامٍ وَمَا كَانُوا مُنتَصِرِينَ |
Wa Qawma Nūĥin Min Qablu 'Innahum Kānū Qawmāan Fāsiqīna  | 051-046 የኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡ | وَقَوْمَ نُوحٍ مِنْ قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْماً فَاسِقِينَ |
Wa As-Samā'a Banaynāhā Bi'ayydin Wa 'Innā Lamūsi`ūna  | 051-047 ሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ | وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْيدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ |
Wa Al-'Arđa Farashnāhā Fani`ma Al-Māhidūna  | 051-048 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!) | وَالأَرْضَ فَرَشْنَاهَا فَنِعْمَ الْمَاهِدُونَ |
Wa Min Kulli Shay'in Khalaqnā Zawjayni La`allakum Tadhakkarūna  | 051-049 ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡ | وَمِنْ كُلِّ شَيْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ |
Fafirrū 'Ilá Al-Lahi 'Innī Lakum Minhu Nadhīrun Mubīnun  | 051-050 آ«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝናآ» (በላቸው)፡፡ | فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ إِنِّي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ مُبِينٌ |
Wa Lā Taj`alū Ma`a Al-Lahi 'Ilahāan 'Ākhara 'Innī Lakum Minhu Nadhīrun Mubīnun  | 051-051 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና፡፡ | وَلاَ تَجْعَلُوا مَعَ اللَّهِ إِلَهاً آخَرَ إِنِّي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ مُبِينٌ |
Kadhālika Mā 'Atá Al-Ladhīna Min Qablihim Min Rasūlin 'Illā Qālū Sāĥirun 'Aw Majnūnun  | 051-052 (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፡፡ (እርሱ) آ«ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነውآ» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡ | كَذَلِكَ مَا أَتَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ مِنْ رَسُولٍ إِلاَّ قَالُوا سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ |
'Atawāşaw Bihi Bal Hum Qawmun Ţāghūna  | 051-053 በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው፡፡ | أَتَوَاصَوْا بِهِ بَلْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ |
Fatawalla `Anhum Famā 'Anta Bimalūmin  | 051-054 ከእነርሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፡፡ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና፡፡ | فَتَوَلَّ عَنْهُمْ فَمَا أَنْتَ بِمَلُومٍ |
Wa Dhakkir Fa'inna Adh-Dhikrá Tanfa`u Al-Mu'uminīna  | 051-055 ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡ | وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَى تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ |
Wa Mā Khalaqtu Al-Jinna Wa Al-'Insa 'Illā Liya`budūni  | 051-056 ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ | وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالإِنسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ |
Mā 'Urīdu Minhum Min Rizqin Wa Mā 'Urīdu 'An Yuţ`imūni  | 051-057 ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ | مَا أُرِيدُ مِنْهُمْ مِنْ رِزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَنْ يُطْعِمُونِ |
'Inna Al-Laha Huwa Ar-Razzāqu Dhū Al-Qūwati Al-Matīnu  | 051-058 አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡ | إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ |
Fa'inna Lilladhīna Žalamū Dhanūbāan Mithla Dhanūbi 'Aşĥābihim Falā Yasta`jilūni  | 051-059 ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ (የቅጣት) ፋንታ አልላቸው፡፡ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ፡፡ | فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذَنُوباً مِثْلَ ذَنُوبِ أَصْحَابِهِمْ فَلاَ يَسْتَعْجِلُونِ |
Fawaylun Lilladhīna Kafarū Min Yawmihimu Al-Ladhī Yū`adūna  | 051-060 ለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው፡ | فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ يَوْمِهِمُ الَّذِي يُوعَدُونَ |