Wa Aş-Şāffāti Şaffāan  | 037-001 መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ | وَالصَّافَّاتِ صَفّاً |
Fālzzājirāti Zajrāan  | 037-002 መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ | فَالزَّاجِرَاتِ زَجْراً |
Fālttāliyāti Dhikrāan  | 037-003 ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ | فَالتَّالِيَاتِ ذِكْراً |
'Inna 'Ilahakum Lawāĥidun  | 037-004 አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ | إِنَّ إِلَهَكُمْ لَوَاحِدٌ |
Rabbu As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Mā Baynahumā Wa Rabbu Al-Mashāriqi  | 037-005 የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ | رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ |
'Innā Zayyannā As-Samā'a Ad-Dunyā Bizīnatin Al-Kawākib  | 037-006 እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ | إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِب |
Wa Ĥifžāan Min Kulli Shayţānin Māridin  | 037-007 አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ | وَحِفْظاً مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ مَارِدٍ |
Lā Yassamma`ūna 'Ilá Al-Mala'i Al-'A`lá Wa Yuqdhafūna Min Kulli Jānibin  | 037-008 ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ | لاَ يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الأَعْلَى وَيُقْذَفُونَ مِنْ كُلِّ جَانِبٍ |
Duĥūrāan Wa Lahum `Adhābun Wa Aşibun  | 037-009 የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ | دُحُوراً وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ |
'Illā Man Khaţifa Al-Khaţfata Fa'atba`ahu Shihābun Thāqibāun  | 037-010 ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ | إِلاَّ مَنْ خَطِفَ الْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ ثَاقِباٌ |
Fāstaftihim 'Ahum 'Ashaddu Khalqāan 'Am Man Khalaqnā 'Innā Khalaqnāhum Min Ţīnin Lāzibin  | 037-011 ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ | فَاسْتَفْتِهِمْ أَهُمْ أَشَدُّ خَلْقاً أَمْ مَنْ خَلَقْنَا إِنَّا خَلَقْنَاهُمْ مِنْ طِينٍ لاَزِبٍ |
Bal `Ajibta Wa Yaskharūna  | 037-012 ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ | بَلْ عَجِبْتَ وَيَسْخَرُونَ |
Wa 'Idhā Dhukkirū Lā Yadhkurūna  | 037-013 በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ | وَإِذَا ذُكِّرُوا لاَ يَذْكُرُونَ |
Wa 'Idhā Ra'aw 'Āyatan Yastaskhirūna  | 037-014 ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ | وَإِذَا رَأَوْا آيَةً يَسْتَسْخِرُونَ |
Wa Qālū 'In Hādhā 'Illā Siĥrun Mubīnun  | 037-015 ይላሉም آ«ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ | وَقَالُوا إِنْ هَذَا إِلاَّ سِحْرٌ مُبِينٌ |
'A'idhā Mitnā Wa Kunnā Turābāan Wa `Ižāmāan 'A'innā Lamab`ūthūna  | 037-016 آ«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን? | أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَاباً وَعِظَاماً أَئِنَّا لَمَبْعُوثُونَ |
'Awa'ābā'uunā Al-'Awwalūna  | 037-017 آ«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ | أَوَآبَاؤُنَا الأَوَّلُونَ |
Qul Na`am Wa 'Antum Dākhirūna  | 037-018 آ«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)آ» በላቸው፡፡ | قُلْ نَعَمْ وَأَنْتُمْ دَاخِرُونَ |
Fa'innamā Hiya Zajratun Wāĥidatun Fa'idhā Hum Yanžurūna  | 037-019 እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ | فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ فَإِذَا هُمْ يَنظُرُونَ |
Wa Qālū Yā Waylanā Hādhā Yawmu Ad-Dīni  | 037-020 آ«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነውآ» ይላሉም፡፡ | وَقَالُوا يَاوَيْلَنَا هَذَا يَوْمُ الدِّينِ |
Hādhā Yawmu Al-Faşli Al-Ladhī Kuntum Bihi Tukadhdhibūna  | 037-021 آ«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነውآ» (ይባላሉ)፡፡ | هَذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنتُمْ بِهِ تُكَذِّبُونَ |
Aĥshurū Al-Ladhīna Žalamū Wa 'Azwājahum Wa Mā Kānū Ya`budūna  | 037-022 (ለመላእክቶችም) آ«እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ | احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ وَمَا كَانُوا يَعْبُدُونَ |
Min Dūni Al-Lahi Fāhdūhum 'Ilá Şirāţi Al-Jaĥīmi  | 037-023 آ«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ | مِنْ دُونِ اللَّهِ فَاهْدُوهُمْ إِلَى صِرَاطِ الْجَحِيمِ |
Wa Qifūhum 'Innahum Mas'ūlūna  | 037-024 آ«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውናآ» (ይባላል)፡፡ | وَقِفُوهُمْ إِنَّهُمْ مَسْئُولُونَ |
Mā Lakum Lā Tanāşarūna  | 037-025 (ለእነርሱም) آ«የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ | مَا لَكُمْ لاَ تَنَاصَرُونَ |
Bal Humu Al-Yawma Mustaslimūna  | 037-026 በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ | بَلْ هُمُ الْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ |
Wa 'Aqbala Ba`đuhum `Alá Ba`đin Yatasā'alūna  | 037-027 የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ | وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ |
Qālū 'Innakum Kuntum Ta'tūnanā `Ani Al-Yamīni  | 037-028 (ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ | قَالُوا إِنَّكُمْ كُنتُمْ تَأْتُونَنَا عَنِ الْيَمِينِ |
Qālū Bal Lam Takūnū Mu'uminīna  | 037-029 (አስከታዮቹም) ይላሉ آ«አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ | قَالُوا بَلْ لَمْ تَكُونُوا مُؤْمِنِينَ |
Wa Mā Kāna Lanā `Alaykum Min Sulţānin Bal Kuntum Qawmāan Ţāghīna  | 037-030 آ«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ | وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيْكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ بَلْ كُنتُمْ قَوْماً طَاغِينَ |
Faĥaqqa `Alaynā Qawlu Rabbinā 'Innā Ladhā'iqūna  | 037-031 آ«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ | فَحَقَّ عَلَيْنَا قَوْلُ رَبِّنَا إِنَّا لَذَائِقُونَ |
Fa'aghwaynākum 'Innā Kunnā Ghāwīna  | 037-032 آ«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንናآ» (ይላሉ)፡፡ | فَأَغْوَيْنَاكُمْ إِنَّا كُنَّا غَاوِينَ |
Fa'innahum Yawma'idhin Fī Al-`Adhābi Mushtarikūna  | 037-033 ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ | فَإِنَّهُمْ يَوْمَئِذٍ فِي الْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ |
'Innā Kadhālika Naf`alu Bil-Mujrimīna  | 037-034 እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ | إِنَّا كَذَلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ |
'Innahum Kānū 'Idhā Qīla Lahum Lā 'Ilāha 'Illā Al-Lahu Yastakbirūna  | 037-035 እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ | إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ |
Wa Yaqūlūna 'A'innā Latārikū 'Ālihatinā Lishā`irin Majnūnin  | 037-036 እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ | وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوا آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَجْنُونٍ |
Bal Jā'a Bil-Ĥaqqi Wa Şaddaqa Al-Mursalīna  | 037-037 አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ | بَلْ جَاءَ بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ |
'Innakum Ladhā'iqū Al-`Adhābi Al-'Alīmi  | 037-038 እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ | إِنَّكُمْ لَذَائِقُو الْعَذَابِ الأَلِيمِ |
Wa Mā Tujzawna 'Illā Mā Kuntum Ta`malūna  | 037-039 ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ | وَمَا تُجْزَوْنَ إِلاَّ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ |
'Illā `Ibāda Al-Lahi Al-Mukhlaşīna  | 037-040 ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ | إِلاَّ عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
'Ūlā'ika Lahum Rizqun Ma`lūmun  | 037-041 እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ | أُوْلَائِكَ لَهُمْ رِزْقٌ مَعْلُومٌ |
Fawākihu Wa Hum Mukramūna  | 037-042 ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ | فَوَاكِهُ وَهُمْ مُكْرَمُونَ |
Fī Jannāti An-Na`īmi  | 037-043 በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ | فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ |
`Alá Sururin Mutaqābilīna  | 037-044 ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ | عَلَى سُرُرٍ مُتَقَابِلِينَ |
Yuţāfu `Alayhim Bika'sin Min Ma`īnin  | 037-045 ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ | يُطَافُ عَلَيْهِمْ بِكَأْسٍ مِنْ مَعِينٍ |
Bayđā'a Ladhdhatin Lilshshāribīna  | 037-046 ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ | بَيْضَاءَ لَذَّةٍ لِلشَّارِبِينَ |
Lā Fīhā Ghawlun Wa Lā Hum `Anhā Yunzafūna  | 037-047 በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ | لاَ فِيهَا غَوْلٌ وَلاَ هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ |
Wa `Indahum Qāşirātu Aţ-Ţarfi `Īnun  | 037-048 እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ | وَعِنْدَهُمْ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ عِينٌ |
Ka'annahunna Bayđun Maknūnun  | 037-049 እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ | كَأَنَّهُنَّ بَيْضٌ مَكْنُونٌ |
Fa'aqbala Ba`đuhum `Alá Ba`đin Yatasā'alūna  | 037-050 የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ | فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ |
Qāla Qā'ilun Minhum 'Innī Kāna Lī Qarīnun  | 037-051 ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል آ«እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ | قَالَ قَائِلٌ مِنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ |
Yaqūlu 'A'innaka Lamina Al-Muşaddiqīna  | 037-052 آ«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡ | يَقُولُ أَئِنَّكَ لَمِنَ الْمُصَدِّقِينَ |
'A'idhā Mitnā Wa Kunnā Turābāan Wa `Ižāmāan 'A'innā Lamadīnūna  | 037-053 آ«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?آ» (የሚል)፡፡ | أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَاباً وَعِظَاماً أَئِنَّا لَمَدِينُونَ |
Qāla Hal 'Antum Muţţali`ūna  | 037-054 እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ | قَالَ هَلْ أَنْتُمْ مُطَّلِعُونَ |
Fāţţala`a Fara'āhu Fī Sawā'i Al-Jaĥīmi  | 037-055 ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ | فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاءِ الْجَحِيمِ |
Qāla Ta-Allāhi 'In Kidta Laturdīni  | 037-056 ይላል آ«በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ | قَالَ تَاللَّهِ إِنْ كِدْتَ لَتُرْدِينِ |
Wa Lawlā Ni`matu Rabbī Lakuntu Mina Al-Muĥđarīna  | 037-057 آ«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡آ» | وَلَوْلاَ نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ |
'Afamā Naĥnu Bimayyitīna  | 037-058 (የገነት ሰዎች ይላሉ) آ«እኛ የምንሞት አይደለንምን? | أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ |
'Illā Mawtatanā Al-'Ūlá Wa Mā Naĥnu Bimu`adhdhabīna  | 037-059 آ«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?آ» (ይላሉ)፡፡ | إِلاَّ مَوْتَتَنَا الأُولَى وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ |
'Inna Hādhā Lahuwa Al-Fawzu Al-`Ažīmu  | 037-060 ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ | إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ |
Limithli Hādhā Falya`mali Al-`Āmilūna  | 037-061 ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ | لِمِثْلِ هَذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ |
'Adhalika Khayrun Nuzulāan 'Am Shajaratu Az-Zaqqūmi  | 037-062 በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ? | أَذَلِكَ خَيْرٌ نُزُلاً أَمْ شَجَرَةُ الزَّقُّومِ |
'Innā Ja`alnāhā Fitnatan Lilžžālimīna  | 037-063 እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡ | إِنَّا جَعَلْنَاهَا فِتْنَةً لِلظَّالِمِينَ |
'Innahā Shajaratun Takhruju Fī 'Aşli Al-Jaĥīmi  | 037-064 እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ | إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخْرُجُ فِي أَصْلِ الْجَحِيمِ |
Ţal`uhā Ka'annahu Ru'ūsu Ash-Shayāţīni  | 037-065 እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ | طَلْعُهَا كَأَنَّهُ رُءُوسُ الشَّيَاطِينِ |
Fa'innahum La'ākilūna Minhā Famāli'ūna Minhā Al-Buţūna  | 037-066 እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ | فَإِنَّهُمْ لَآكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ |
Thumma 'Inna Lahum `Alayhā Lashawbāan Min Ĥamīmin  | 037-067 ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡ | ثُمَّ إِنَّ لَهُمْ عَلَيْهَا لَشَوْباً مِنْ حَمِيمٍ |
Thumma 'Inna Marji`ahum La'ilá Al-Jaĥīmi  | 037-068 ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡ | ثُمَّ إِنَّ مَرْجِعَهُمْ لَإِلَى الْجَحِيمِ |
'Innahum 'Alfaw 'Ābā'ahum Đāllīna  | 037-069 እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡ | إِنَّهُمْ أَلْفَوْا آبَاءَهُمْ ضَالِّينَ |
Fahum `Alá 'Āthārihim Yuhra`ūna  | 037-070 እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡ | فَهُمْ عَلَى آثَارِهِمْ يُهْرَعُونَ |
Wa Laqad Đalla Qablahum 'Aktharu Al-'Awwalīna  | 037-071 ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡ | وَلَقَدْ ضَلَّ قَبْلَهُمْ أَكْثَرُ الأَوَّلِينَ |
Wa Laqad 'Arsalnā Fīhim Mundhirīna  | 037-072 በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡ | وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِمْ مُنذِرِينَ |
Fānžur Kayfa Kāna `Āqibatu Al-Mundharīna  | 037-073 የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ | فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُنذَرِينَ |
'Illā `Ibāda Al-Lahi Al-Mukhlaşīna  | 037-074 ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ | إِلاَّ عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
Wa Laqad Nādānā Nūĥun Falani`ma Al-Mujībūna  | 037-075 ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን! | وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ |
Wa Najjaynāhu Wa 'Ahlahu Mina Al-Karbi Al-`Ažīmi  | 037-076 እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡ | وَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ |
Wa Ja`alnā Dhurrīyatahu Humu Al-Bāqīna  | 037-077 ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤ | وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُ هُمُ الْبَاقِينَ |
Wa Taraknā `Alayhi Fī Al-'Ākhirīna  | 037-078 በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡ | وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الآخِرِينَ |
Salāmun `Alá Nūĥin Fī Al-`Ālamīna  | 037-079 آ«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡آ» | سَلاَمٌ عَلَى نُوحٍ فِي الْعَالَمِينَ |
'Innā Kadhālika Najzī Al-Muĥsinīna  | 037-080 እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ | إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
'Innahu Min `Ibādinā Al-Mu'uminīna  | 037-081 እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡ | إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
Thumma 'Aghraqnā Al-'Ākharīna  | 037-082 ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ | ثُمَّ أَغْرَقْنَا الآخَرِينَ |
Wa 'Inna Min Shī`atihi La'ibrāhīma  | 037-083 ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ | وَإِنَّ مِنْ شِيعَتِهِ لَإِبْرَاهِيمَ |
'Idh Jā'a Rabbahu Biqalbin Salīmin  | 037-084 ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡ | إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ |
'Idh Qāla Li'abīhi Wa Qawmihi Mādhā Ta`budūna  | 037-085 آ«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?آ» ባለ ጊዜ፡፡ | إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَاذَا تَعْبُدُونَ |
'A'ifkāan 'Ālihatan Dūna Al-Lahi Turīdūna  | 037-086 آ«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን? | أَئِفْكاً آلِهَةً دُونَ اللَّهِ تُرِيدُونَ |
Famā Žannukum Birabbi Al-`Ālamīna  | 037-087 آ«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?آ» አለ፡፡ | فَمَا ظَنُّكُمْ بِرَبِّ الْعَالَمِينَ |
Fanažara Nažratan Fī An-Nujūmi  | 037-088 በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡ | فَنَظَرَ نَظْرَةً فِي النُّجُومِ |
Faqāla 'Innī Saqīmun  | 037-089 آ«እኔ በሽተኛ ነኝምآ» አለ፡፡ | فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٌ |
Fatawallaw `Anhu Mudbirīna  | 037-090 ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡ | فَتَوَلَّوْا عَنْهُ مُدْبِرِينَ |
Farāgha 'Ilá 'Ālihatihim Faqāla 'Alā Ta'kulūna  | 037-091 ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- آ«አትበሉምን?آ» | فَرَاغَ إِلَى آلِهَتِهِمْ فَقَالَ أَلاَ تَأْكُلُونَ |
Mā Lakum Lā Tanţiqūna  | 037-092 آ«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?آ» | مَا لَكُمْ لاَ تَنطِقُونَ |
Farāgha `Alayhim Đarbāan Bil-Yamīni  | 037-093 በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ | فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْباً بِالْيَمِينِ |
Fa'aqbalū 'Ilayhi Yaziffūna  | 037-094 ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡ | فَأَقْبَلُوا إِلَيْهِ يَزِفُّونَ |
Qāla 'Ata`budūna Mā Tanĥitūna  | 037-095 አላቸው آ«የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?آ» | قَالَ أَتَعْبُدُونَ مَا تَنْحِتُونَ |
Wa Allāhu Khalaqakum Wa Mā Ta`malūna  | 037-096 آ«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡آ» | وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ |
Qālū Abnū Lahu Bunyānāan Fa'alqūhu Fī Al-Jaĥīmi  | 037-097 آ«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትምآ» አሉ፡፡ | قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَاناً فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ |
Fa'arādū Bihi Kaydāan Faja`alnāhumu Al-'Asfalīna  | 037-098 በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡ | فَأَرَادُوا بِهِ كَيْداً فَجَعَلْنَاهُمُ الأَسْفَلِينَ |
Wa Qāla 'Innī Dhāhibun 'Ilá Rabbī Sayahdīni  | 037-099 አለም آ«እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡آ» | وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَى رَبِّي سَيَهْدِينِ |
Rabbi Hab Lī Mina Aş-Şāliĥīna  | 037-100 ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ | رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ |
Fabashsharnāhu Bighulāmin Ĥalīmin  | 037-101 ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ | فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلاَمٍ حَلِيمٍ |
Falammā Balagha Ma`ahu As-Sa`ya Qāla Yā Bunayya 'Innī 'Ará Fī Al-Manāmi 'Annī 'Adhbaĥuka Fānžur Mādhā Tará Qāla Yā 'Abati Af`al Mā Tu'umaru Satajidunī 'In Shā'a Al-Lahu Mina Aş-Şābirīna  | 037-102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ آ«ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?آ» አለው፡፡ آ«አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህآ» አለ፡፡ | فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَابُنَيَّ إِنِّي أَرَى فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَى قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ سَتَجِدُنِي إِنْ شFalammā 'Aslamā Wa Tallahu Liljabīni  | 037-103 ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ | فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ |
Wa Nādaynāhu 'An Yā 'Ibrāhīmu  | 037-104 ጠራነውም፤ (አልነው) آ«ኢብራሂም ሆይ! | وَنَادَيْنَاهُ أَنْ يَا إِبْرَاهِيمُ |
Qad Şaddaqta Ar-Ru'uyā 'Innā Kadhālika Najzī Al-Muĥsinīna  | 037-105 ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡آ» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ | قَد صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
'Inna Hādhā Lahuwa Al-Balā'u Al-Mubīnu  | 037-106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ | إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْبَلاَءُ الْمُبِينُ |
Wa Fadaynāhu Bidhibĥin `Ažīmin  | 037-107 በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ | وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ |
Wa Taraknā `Alayhi Fī Al-'Ākhirīna  | 037-108 በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ | وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الآخِرِينَ |
Salāmun `Alá 'Ibrāhīma  | 037-109 ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ | سَلاَمٌ عَلَى إِبْرَاهِيمَ |
Kadhālika Najzī Al-Muĥsinīna  | 037-110 እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ | كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
'Innahu Min `Ibādinā Al-Mu'uminīna  | 037-111 እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ | إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
Wa Bashsharnāhu Bi'isĥāqa Nabīyāan Mina Aş-Şāliĥīna  | 037-112 በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ | وَبَشَّرْنَاهُ بِإِسْحَاقَ نَبِيّاً مِنَ الصَّالِحِينَ |
Wa Bāraknā `Alayhi Wa `Alá 'Isĥāqa Wa Min Dhurrīyatihimā Muĥsinun Wa Žālimun Linafsihi Mubīnun  | 037-113 በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ | وَبَارَكْنَا عَلَيْهِ وَعَلَى إِسْحَاقَ وَمِنْ ذُرِّيَّتِهِمَا مُحْسِنٌ وَظَالِمٌ لِنَفْسِهِ مُبِينٌ |
Wa Laqad Manannā `Alá Mūsá Wa Hārūna  | 037-114 በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ | وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَى مُوسَى وَهَارُونَ |
Wa Najjaynāhumā Wa Qawmahumā Mina Al-Karbi Al-`Ažīmi  | 037-115 እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ | وَنَجَّيْنَاهُمَا وَقَوْمَهُمَا مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ |
Wa Naşarnāhum Fakānū Humu Al-Ghālibīna  | 037-116 ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ | وَنَصَرْنَاهُمْ فَكَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ |
Wa 'Ātaynāhumā Al-Kitāba Al-Mustabīna  | 037-117 በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ | وَآتَيْنَاهُمَا الْكِتَابَ الْمُسْتَبِينَ |
Wa Hadaynāhumā Aş-Şirāţa Al-Mustaqīma  | 037-118 ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ | وَهَدَيْنَاهُمَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ |
Wa Taraknā `Alayhimā Fī Al-'Ākhirīna  | 037-119 በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ | وَتَرَكْنَا عَلَيْهِمَا فِي الآخِرِينَ |
Salāmun `Alá Mūsá Wa Hārūna  | 037-120 ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ | سَلاَمٌ عَلَى مُوسَى وَهَارُونَ |
'Innā Kadhālika Najzī Al-Muĥsinīna  | 037-121 እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ | إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
'Innahumā Min `Ibādinā Al-Mu'uminīna  | 037-122 ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ | إِنَّهُمَا مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
Wa 'Inna 'Ilyāsa Lamina Al-Mursalīna  | 037-123 ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ | وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ |
'Idh Qāla Liqawmihi 'Alā Tattaqūna  | 037-124 ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን? | إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلاَ تَتَّقُونَ |
'Atad`ūna Ba`lāan Wa Tadharūna 'Aĥsana Al-Khāliqīna  | 037-125 በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? | أَتَدْعُونَ بَعْلاً وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ |
Al-Laha Rabbakum Wa Rabba 'Ābā'ikumu Al-'Awwalīna  | 037-126 አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)? | اللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الأَوَّلِينَ |
Fakadhdhabūhu Fa'innahum Lamuĥđarūna  | 037-127 አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ | فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ |
'Illā `Ibāda Al-Lahi Al-Mukhlaşīna  | 037-128 ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ | إِلاَّ عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
Wa Taraknā `Alayhi Fī Al-'Ākhirīna  | 037-129 በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ | وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الآخِرِينَ |
Salāmun `Alá 'Il Yā -Sīn  | 037-130 ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ | سَلاَمٌ عَلَى إِلْ يَا-سِين |
'Innā Kadhālika Najzī Al-Muĥsinīna  | 037-131 እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ | إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
'Innahu Min `Ibādinā Al-Mu'uminīna  | 037-132 እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ | إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
Wa 'Inna Lūţāan Lamina Al-Mursalīna  | 037-133 ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ | وَإِنَّ لُوطاً لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ |
'Idh Najjaynāhu Wa 'Ahlahu 'Ajma`īna  | 037-134 እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ | إِذْ نَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ أَجْمَعِينَ |
'Illā `Ajūzāan Fī Al-Ghābirīna  | 037-135 (በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ | إِلاَّ عَجُوزاً فِي الْغَابِرِينَ |
Thumma Dammarnā Al-'Ākharīna  | 037-136 ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ | ثُمَّ دَمَّرْنَا الآخَرِينَ |
Wa 'Innakum Latamurrūna `Alayhim Muşbiĥīna  | 037-137 እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ | وَإِنَّكُمْ لَتَمُرُّونَ عَلَيْهِمْ مُصْبِحِينَ |
Wa Bil-Layli 'Afalā Ta`qilūna  | 037-138 በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን? | وَبِاللَّيْلِ أَفَلاَ تَعْقِلُونَ |
Wa 'Inna Yūnis Lamina Al-Mursalīna  | 037-139 ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ | وَإِنَّ يُونِس لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ |
'Idh 'Abaqa 'Ilá Al-Fulki Al-Mashĥūni  | 037-140 ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ | إِذْ أَبَقَ إِلَى الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ |
Fasāhama Fakāna Mina Al-Mudĥađīna  | 037-141 ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ | فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ الْمُدْحَضِينَ |
Fāltaqamahu Al-Ĥūtu Wa Huwa Mulīmun  | 037-142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ | فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ |
Falawlā 'Annahu Kāna Mina Al-Musabbiĥīna  | 037-143 እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ | فَلَوْلاَ أَنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُسَبِّحِينَ |
Lalabitha Fī Baţnihi 'Ilá Yawmi Yub`athūna  | 037-144 እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ | لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ |
Fanabadhnāhu Bil-`Arā'i Wa Huwa Saqīmun  | 037-145 እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ | فَنَبَذْنَاهُ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ سَقِيمٌ |
Wa 'Anbatnā `Alayhi Shajaratan Min Yaqţīnin  | 037-146 በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ | وَأَنْبَتْنَا عَلَيْهِ شَجَرَةً مِنْ يَقْطِينٍ |
Wa 'Arsalnāhu 'Ilá Miā'ati 'Alfin 'Aw Yazīdūna  | 037-147 ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ | وَأَرْسَلْنَاهُ إِلَى مِائَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ |
Fa'āmanū Famatta`nāhum 'Ilá Ĥīnin  | 037-148 አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ | فَآمَنُوا فَمَتَّعْنَاهُمْ إِلَى حِينٍ |
Fāstaftihim 'Alirabbika Al-Banātu Wa Lahumu Al-Banūna  | 037-149 (የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ آ«ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?آ» | فَاسْتَفْتِهِمْ أَلِرَبِّكَ الْبَنَاتُ وَلَهُمُ الْبَنُونَ |
'Am Khalaqnā Al-Malā'ikata 'Ināthāan Wa Hum Shāhidūna  | 037-150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? | أَمْ خَلَقْنَا الْمَلاَئِكَةَ إِنَاثاً وَهُمْ شَاهِدُونَ |
'Alā 'Innahum Min 'Ifkihim Layaqūlūna  | 037-151 ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡- | أَلاَ إِنَّهُمْ مِنْ إِفْكِهِمْ لَيَقُولُونَ |
Walada Al-Lahu Wa 'Innahum Lakādhibūna  | 037-152 آ«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡آ» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ | وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ |
'Āşţafá Al-Banāti `Alá Al-Banīna  | 037-153 በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን? | أَاصْطَفَى الْبَنَاتِ عَلَى الْبَنِينَ |
Mā Lakum Kayfa Taĥkumūna  | 037-154 ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ! | مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ |
'Afalā Tadhakkarūn  | 037-155 አትገነዘቡምን? | أَفَلاَ تَذَكَّرُون |
'Am Lakum Sulţānun Mubīnun  | 037-156 ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን? | أَمْ لَكُمْ سُلْطَانٌ مُبِينٌ |
Fa'tū Bikitābikum 'In Kuntum Şādiqīna  | 037-157 آ«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡآ» (በላቸው)፡፡ | فَأْتُوا بِكِتَابِكُمْ إِنْ كُنتُمْ صَادِقِينَ |
Wa Ja`alū Baynahu Wa Bayna Al-Jinnati Nasabāan Wa Laqad `Alimati Al-Jinnatu 'Innahum Lamuĥđarūna  | 037-158 በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡ | وَجَعَلُوا بَيْنَهُ وَبَيْنَ الْجِنَّةِ نَسَباً وَلَقَدْ عَلِمَتِ الْجِنَّةُ إِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ |
Subĥāna Al-Lahi `Ammā Yaşifūna  | 037-159 አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ | سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ |
'Illā `Ibāda Al-Lahi Al-Mukhlaşīna  | 037-160 ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡ | إِلاَّ عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
Fa'innakum Wa Mā Ta`budūna  | 037-161 እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤ | فَإِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ |
Mā 'Antum `Alayhi Bifātinīna  | 037-162 በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡ | مَا أَنْتُمْ عَلَيْهِ بِفَاتِنِينَ |
'Illā Man Huwa Şālī Al-Jaĥīmi  | 037-163 ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡ | إِلاَّ مَنْ هُوَ صَالِي الْجَحِيمِ |
Wa Mā Minnā 'Illā Lahu Maqāmun Ma`lūmun  | 037-164 (ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡ | وَمَا مِنَّا إِلاَّ لَهُ مَقَامٌ مَعْلُومٌ |
Wa 'Innā Lanaĥnu Aş-Şāffūna  | 037-165 እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡ | وَإِنَّا لَنَحْنُ الصَّافُّونَ |
Wa 'Innā Lanaĥnu Al-Musabbiĥūna  | 037-166 እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡ | وَإِنَّا لَنَحْنُ الْمُسَبِّحُونَ |
Wa 'In Kānū Layaqūlūna  | 037-167 እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡- | وَإِنْ كَانُوا لَيَقُولُونَ |
Law 'Anna `Indanā Dhikrāan Mina Al-'Awwalīna  | 037-168 آ«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤ | لَوْ أَنَّ عِنْدَنَا ذِكْراً مِنَ الأَوَّلِينَ |
Lakunnā `Ibāda Al-Lahi Al-Mukhlaşīna  | 037-169 آ«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡آ» | لَكُنَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
Fakafarū Bihi Fasawfa Ya`lamūna  | 037-170 ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ | فَكَفَرُوا بِهِ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ |
Wa Laqad Sabaqat Kalimatunā Li`ibādinā Al-Mursalīn  | 037-171 (የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡ | وَلَقَدْ سَبَقَتْ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا الْمُرْسَلِين |
'Innahum Lahumu Al-Manşūrūna  | 037-172 እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ | إِنَّهُمْ لَهُمُ الْمَنصُورُونَ |
Wa 'Inna Jundanā Lahumu Al-Ghālibūna  | 037-173 ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ | وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ الْغَالِبُونَ |
Fatawalla `Anhum Ĥattá Ĥīnin  | 037-174 ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡ | فَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّى حِينٍ |
Wa 'Abşirhum Fasawfa Yubşirūna  | 037-175 እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡ | وَأَبْصِرْهُمْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ |
'Afabi`adhābinā Yasta`jilūna  | 037-176 በቅጣታችንም ያቻኩላሉን? | أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ |
Fa'idhā Nazala Bisāĥatihim Fasā'a Şabāĥu Al-Mundharīna  | 037-177 በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ! | فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمْ فَسَاءَ صَبَاحُ الْمُنذَرِينَ |
Wa Tawalla `Anhum Ĥattá Ĥīnin  | 037-178 እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡ | وَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّى حِينٍ |
Wa 'Abşir Fasawfa Yubşirūna  | 037-179 ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡ | وَأَبْصِرْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ |
Subĥāna Rabbika Rabbi Al-`Izzati `Ammā Yaşifūna  | 037-180 የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ | سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ |
Wa Salāmun `Alá Al-Mursalīna  | 037-181 በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤ | وَسَلاَمٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ |
Wa Al-Ĥamdu Lillahi Rabbi Al-`Ālamīna  | 037-182 ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡ | وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ |