Şād Wa Al-Qur'āni Dhī Adh-Dhikri  | 038-001 ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡ | صَاد وَالْقُرْآنِ ذِي الذِّكْرِ |
Bali Al-Ladhīna Kafarū Fī `Izzatin Wa Shiqāqin  | 038-002 ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡ | بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي عِزَّةٍ وَشِقَاقٍ |
Kam 'Ahlaknā Min Qablihim Min Qarnin Fanādaw Walāta Ĥīna Manāşin  | 038-003 ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡ | كَمْ أَهْلَكْنَا مِنْ قَبْلِهِمْ مِنْ قَرْنٍ فَنَادَوْا وَلاَتَ حِينَ مَنَاصٍ |
Wa `Ajibū 'An Jā'ahum Mundhirun Minhum Wa Qāla Al-Kāfirūna Hādhā Sāĥirun Kadhdhābun  | 038-004 ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም آ«ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነውآ» አሉ፡፡ | وَعَجِبُوا أَنْ جَاءَهُمْ مُنْذِرٌ مِنْهُمْ وَقَالَ الْكَافِرُونَ هَذَا سَاحِرٌ كَذَّابٌ |
'Aja`ala Al-'Ālihata 'Ilahāan Wāĥidāan 'Inna Hādhā Lashay'un `Ujābun  | 038-005 آ«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነውآ» (አሉ)፡፡ | أَجَعَلَ الآلِهَةَ إِلَهاً وَاحِداً إِنَّ هَذَا لَشَيْءٌ عُجَابٌ |
Wa Anţalaqa Al-Mala'u Minhum 'Ani Amshū Wa Aşbirū `Alá 'Ālihatikum 'Inna Hādhā Lashay'un Yurādu  | 038-006 ከእነርሱም መኳንንቶቹ آ«ሂዱ፤ በአማልክቶቻችሁም (መግገዛት) ላይ ታገሱ፡፡ ይህ (ከእኛ) የሚፈለግ ነገር ነውናآ» እያሉ አዘገሙ፡፡ | وَانطَلَقَ الْمَلَأُ مِنْهُمْ أَنِ امْشُوا وَاصْبِرُوا عَلَى آلِهَتِكُمْ إِنَّ هَذَا لَشَيْءٌ يُرَادُ |
Mā Sami`nā Bihadhā Fī Al-Millati Al-'Ākhirati 'In Hādhā 'Illā Akhtilāqun  | 038-007 آ«ይህንንም በኋለኛይቱ ሃይማኖት አልሰማንም፡፡ ይህ ውሸትን መፍጠር እንጅ ሌላ አይደለምآ» (እያሉም)፡፡ | مَا سَمِعْنَا بِهَذَا فِي الْمِلَّةِ الآخِرَةِ إِنْ هَذَا إِلاَّ اخْتِلاَقٌ |
'A'uunzila `Alayhi Adh-Dhikru Min Bayninā Bal Hum Fī Shakkin Min Dhikrī Bal Lammā Yadhūqū `Adhābi  | 038-008 آ«ከመካከላችን በእርሱ ላይ ቁርኣን ተወረደን?آ» (አሉ)፡፡ በእውነት እነርሱ ከግሳጼዬ (ከቁርኣን) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡ | أَؤُنزِلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ مِنْ بَيْنِنَا بَلْ هُمْ فِي شَكٍّ مِنْ ذِكْرِي بَلْ لَمَّا يَذُوقُوا عَذَابِ |
'Am `Indahum Khazā'inu Raĥmati Rabbika Al-`Azīzi Al-Wahhābi  | 038-009 ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? | أَمْ عِنْدَهُمْ خَزَائِنُ رَحْمَةِ رَبِّكَ الْعَزِيزِ الْوَهَّابِ |
'Am Lahum Mulku As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Mā Baynahumā Falyartaqū Fī Al-'Asbābi  | 038-010 ወይስ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የእነርሱ ነውን? (ነው ቢሉ) በመሰላሎችም ይውጡ፡፡ | أَمْ لَهُمْ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَلْيَرْتَقُوا فِي الأَسْبَابِ |
Jundun Mā Hunālika Mahzūmun Mina Al-'Aĥzābi  | 038-011 እዚያ ዘንድ ከአሕዛብ የሆኑ ተሸናፊ ሰራዊት ናቸው፡፡ | جُندٌ مَا هُنَالِكَ مَهْزُومٌ مِنَ الأَحْزَابِ |
Kadhdhabat Qablahum Qawmu Nūĥin Wa `Ādun Wa Fir`awnu Dhū Al-'Awtādi  | 038-012 ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድም፣ የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባበሉ፡፡ | كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ ذُو الأَوْتَادِ |
Wa Thamūdu Wa Qawmu Lūţin Wa 'Aşĥābu Al-'Aykati 'Ūlā'ika Al-'Aĥzābu  | 038-013 ሰሙድም፣ የሉጥ ሰዎችም፣ የአይከት ሰዎችም (አስተባበሉ)፡፡ እነዚህ አሕዛቦቹ ናቸው፡፡ | وَثَمُودُ وَقَوْمُ لُوطٍ وَأَصْحَابُ الأَيْكَةِ أُوْلَائِكَ الأَحْزَابُ |
'In Kullun 'Illā Kadhdhaba Ar-Rusula Faĥaqqa `Iqābi  | 038-014 ሁሉም መልክተኞቹን ያስዋሹ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ ቅጣቴም ተረጋገጠባቸው፡፡ | إِنْ كُلٌّ إِلاَّ كَذَّبَ الرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ |
Wa Mā Yanžuru Hā'uulā' 'Illā Şayĥatan Wāĥidatan Mā Lahā Min Fawāqin  | 038-015 እነዚህም ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲትን ጩኸት እንጅ ሌላን አይጠባበቁም፡፡ | وَمَا يَنظُرُ هَاؤُلاَء إِلاَّ صَيْحَةً وَاحِدَةً مَا لَهَا مِنْ فَوَاقٍ |
Wa Qālū Rabbanā `Ajjil Lanā Qiţţanā Qabla Yawmi Al-Ĥisābi  | 038-016 آ«ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት መጽሐፋችንን አስቸኩልልንآ» አሉም፡፡ | وَقَالُوا رَبَّنَا عَجِّلْ لَنَا قِطَّنَا قَبْلَ يَوْمِ الْحِسَابِ |
Aşbir `Alá Mā Yaqūlūna Wa Adhkur `Abdanā Dāwūda Dhā Al-'Aydi 'Innahu 'Awwābun  | 038-017 በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡ | اصْبِرْ عَلَى مَا يَقُولُونَ وَاذْكُرْ عَبْدَنَا دَاوُودَ ذَا الأَيْدِ إِنَّهُ أَوَّابٌ |
'Innā Sakhkharnā Al-Jibāla Ma`ahu Yusabbiĥna Bil-`Ashīyi Wa Al-'Ishrāqi  | 038-018 እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋድም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆኑ ገራንለት፡፡ | إِنَّا سَخَّرْنَا الْجِبَالَ مَعَهُ يُسَبِّحْنَ بِالْعَشِيِّ وَالإِشْرَاقِ |
Wa Aţ-Ţayra Maĥshūratan Kullun Lahu 'Awwābun  | 038-019 በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው (ገራንለት)፡፡ ሁሉም ለእርሱ (ማወደስ) የሚመላለስ ነው፡፡ | وَالطَّيْرَ مَحْشُورَةً كُلٌّ لَهُ أَوَّابٌ |
Wa Shadadnā Mulkahu Wa 'Ātaynāhu Al-Ĥikmata Wa Faşla Al-Khiţābi  | 038-020 መንግሥቱንም አበረታንለት፡፡ ጥበብንም ንግግርን መለየትንም ሰጠነው፡፡ | وَشَدَدْنَا مُلْكَهُ وَآتَيْنَاهُ الْحِكْمَةَ وَفَصْلَ الْخِطَابِ |
Wa Hal 'Atāka Naba'u Al-Khaşmi 'Idh Tasawwarū Al-Miĥrāba  | 038-021 የተከራካሪዎቹም ወሬ መጥቶልሃልን? ምኩራቡን በተንጠላጠሉ ጊዜ፡፡ | وَهَلْ أَتَاكَ نَبَأُ الْخَصْمِ إِذْ تَسَوَّرُوا الْمِحْرَابَ |
'Idh Dakhalū `Alá Dāwūda Fafazi`a Minhum Qālū Lā Takhaf Khaşmāni Baghá Ba`đunā `Alá Ba`đin Fāĥkum Baynanā Bil-Ĥaqqi Wa Lā Tushţiţ Wa Ahdinā 'Ilá Sawā'i Aş-Şirāţi  | 038-022 በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም በደነገጠ ጊዜ آ«አትፍራ፤ (እኛ) ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን፡፡ በመካከላችንም በእውነት ፍረድ፡፡ አታዳላም፡፡ ወደ መካከለኛውም መንገድ ምራን፤آ» አሉት፡፡ | إِذْ دَخَلُوا عَلَى دَاوُودَ فَفَزِعَ مِنْهُمْ قَالُوا لاَ تَخَفْ خَصْمَانِ بَغَى بَعْضُنَا عَلَى بَعْضٍ فَاحْكُمْ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَلاَ تُشْطِطْ وَاهْدِنَا إِلَى سَوَاءِ الصِّرَاطِ |
'Inna Hādhā 'Akhī Lahu Tis`un Wa Tis`ūna Na`jatan Wa Liya Na`jatun Wāĥidatun Faqāla 'Akfilnīhā Wa `Azzanī Fī Al-Khiţābi  | 038-023 آ«ይህ ወንድሜ ነው፤ ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴቶች በጎች አሉት፡፡ ለኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ፡፡ እርሷንም ዕድሌ አድርጋት አለኝ፡፡ በንግግርም አሸነፈኝآ» አለው፡፡ | إِنَّ هَذَا أَخِي لَهُ تِسْعٌ وَتِسْعُونَ نَعْجَةً وَلِيَ نَعْجَةٌ وَاحِدَةٌ فَقَالَ أَكْفِلْنِيهَا وَعَزَّنِي فِي الْخِطَابِ |
Qāla Laqad Žalamaka Bisu'uāli Na`jatika 'Ilá Ni`ājihi Wa 'Inna Kathīrāan Mina Al-Khulaţā'i Layabghī Ba`đuhum `Alá Ba`đin 'Illā Al-Ladhīna 'Āmanū Wa `Amilū Aş-Şāliĥāti Wa Qalīlun Mā Hum Wa Žanna Dāwūdu 'Annamā Fatannāhu Fāstaghfara Rabbahu Wa Kharra Rāki`āan Wa 'Anāba  | 038-024 آ«ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፡፡ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸውآ» አለ፡፡ ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡ | قَالَ لَقَدْ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعْجَتِكَ إِلَى نِعَاجِهِ وَإِنَّ كَثِيراً مِنَ الْخُلَطَاءِ لَيَبْغِي بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْض | Faghafarnā Lahu Dhālika Wa 'Inna Lahu `Indanā Lazulfá Wa Ĥusna Ma'ābin  | 038-025 ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ (ክብር) መልካም መመለሻም አለው፡፡ | فَغَفَرْنَا لَهُ ذَلِكَ وَإِنَّ لَهُ عِنْدَنَا لَزُلْفَى وَحُسْنَ مَآبٍ |
Yā Dāwūdu 'Innā Ja`alnāka Khalīfatan Fī Al-'Arđi Fāĥkum Bayna An-Nāsi Bil-Ĥaqqi Wa Lā Tattabi`i Al-Hawá Fayuđillaka `An Sabīli Al-Lahi 'Inna Al-Ladhīna Yađillūna `An Sabīli Al-Lahi Lahum `Adhābun Shadīdun Bimā Nasū Yawma Al-Ĥisābi  | 038-026 ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ ዝንባሌሀንም አትከተል፤ከአላህ መንገድ ያሳሳትሃልና፡፡ እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ | يَادَاوُودُ إِنَّا جَعَلْنَاكَ خَلِيفَةً فِي الأَرْضِ فَاحْكُمْ بَيْنَ النَّاسِ بِالْحَقِّ وَلاَ تَتَّبِعِ الْهَوَى فَيُضِلَّكَ عَنْ سَبِيلِ Wa Mā Khalaqnā As-Samā'a Wa Al-'Arđa Wa Mā Baynahumā Bāţilāan Dhālika Žannu Al-Ladhīna Kafarū Fawaylun Lilladhīna Kafarū Mina An-Nāri  | 038-027 ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው! | وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلاً ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ |
'Am Naj`alu Al-Ladhīna 'Āmanū Wa `Amilū Aş-Şāliĥāti Kālmufsidīna Fī Al-'Arđi 'Am Naj`alu Al-Muttaqīna Kālfujjāri  | 038-028 በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን? | أَمْ نَجْعَلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَالْمُفْسِدِينَ فِي الأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ الْمُتَّقِينَ كَالْفُجَّارِ |
Kitābun 'Anzalnāhu 'Ilayka Mubārakun Liyaddabbarū 'Āyātihi Wa Liyatadhakkara 'Ūlū Al-'Albābi  | 038-029 (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ | كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُوْلُوا الأَلْبَابِ |
Wa Wahabnā Lidāwūda Sulaymāna Ni`ma Al-`Abdu 'Innahu 'Awwābun  | 038-030 ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! (ሱለይማን)፣ እርሱ መላሳ ነው፡፡ | وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ نِعْمَ الْعَبْدُ إِنَّهُ أَوَّابٌ |
'Idh `Uriđa `Alayhi Bil-`Ashīyi Aş-Şāfinātu Al-Jiyādu  | 038-031 በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሦስት እግሮችና በአራተኛዋ ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌዎች ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (አስታውስ)፡፡ | إِذْ عُرِضَ عَلَيْهِ بِالْعَشِيِّ الصَّافِنَاتُ الْجِيَادُ |
Faqāla 'Innī 'Aĥbabtu Ĥubba Al-Khayri `An Dhikri Rabbī Ĥattá Tawārat Bil-Ĥijābi  | 038-032 አለም آ«እኔ (ፀሐይ) በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ፡፡آ» | فَقَالَ إِنِّي أَحْبَبْتُ حُبَّ الْخَيْرِ عَنْ ذِكْرِ رَبِّي حَتَّى تَوَارَتْ بِالْحِجَابِ |
Ruddūhā `Alayya Faţafiqa Masĥāan Bis-Sūqi Wa Al-'A`nāqi  | 038-033 آ«በእኔ ላይ መልሷትآ» (አለ) አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም ማበስ ያዘ፡፡ | رُدُّوهَا عَلَيَّ فَطَفِقَ مَسْحاً بِالسُّوقِ وَالأَعْنَاقِ |
Wa Laqad Fatannā Sulaymāna Wa 'Alqaynā `Alá Kursīyihi Jasadāan Thumma 'Anāba  | 038-034 ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ አካልን ጣልን፡፡ ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ፡፡ | وَلَقَدْ فَتَنَّا سُلَيْمَانَ وَأَلْقَيْنَا عَلَى كُرْسِيِّهِ جَسَداً ثُمَّ أَنَابَ |
Qāla Rabbi Aghfir Lī Wa Hab Lī Mulkāan Lā Yanbaghī Li'ĥadin Min Ba`dī 'Innaka 'Anta Al-Wahhābu  | 038-035 آ«ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህናآ» አለ፡፡ | قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَهَبْ لِي مُلْكاً لاَ يَنْبَغِي لِأحَدٍ مِنْ بَعْدِي إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ |
Fasakhkharnā Lahu Ar-Rīĥa Tajrī Bi'amrihi Rukhā'an Ĥaythu 'Aşāba  | 038-036 ነፋስንም በትእዛዙ ወደፈለገበት ስፍራ ልዝብ ኾና የምትፈስ ስትኾን ገራንለት፡፡ | فَسَخَّرْنَا لَهُ الرِّيحَ تَجْرِي بِأَمْرِهِ رُخَاءً حَيْثُ أَصَابَ |
Wa Ash-Shayāţīna Kulla Bannā'in Wa Ghawwāşin  | 038-037 ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰጣሚዎችን ሁሉ (ገራንለት)፡፡ | وَالشَّيَاطِينَ كُلَّ بَنَّاءٍ وَغَوَّاصٍ |
Wa 'Ākharīna Muqarranīna Fī Al-'Aşfādi  | 038-038 ሌሎችንም በፍንጆች ተቆራኞችን (ገራንለት)፡፡ | وَآخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِي الأَصْفَادِ |
Hādhā `Aţā'uunā Fāmnun 'Aw 'Amsik Bighayri Ĥisābin  | 038-039 آ«ይህ ስጦታችን ነው፡፡ ያለግምት ለግስ፤ ወይም ጨብጥآ» (አልነው)፡፡ | هَذَا عَطَاؤُنَا فَامْنُنْ أَوْ أَمْسِكْ بِغَيْرِ حِسَابٍ |
Wa 'Inna Lahu `Indanā Lazulfá Wa Ĥusna Ma'ābin  | 038-040 ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ፤ መልካም መመለሻም በእርግጥ አልለው፡፡ | وَإِنَّ لَهُ عِنْدَنَا لَزُلْفَى وَحُسْنَ مَآبٍ |
Wa Adhkur `Abdanā 'Ayyūba 'Idh Nādá Rabbahu 'Annī Massanī Ash-Shayţānu Binuşbin Wa `Adhābin  | 038-041 ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ آ«እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝآ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ | وَاذْكُرْ عَبْدَنَا أَيُّوبَ إِذْ نَادَى رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِي الشَّيْطَانُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ |
Arkuđ Birijlika Hādhā Mughtasalun Bāridun Wa Sharābun  | 038-042 آ«በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነውآ» (ተባለ)፡፡ | ارْكُضْ بِرِجْلِكَ هَذَا مُغْتَسَلٌ بَارِدٌ وَشَرَابٌ |
Wa Wahabnā Lahu 'Ahlahu Wa Mithlahum Ma`ahum Raĥmatan Minnā Wa Dhikrá Li'wlī Al-'Albābi  | 038-043 ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡ | وَوَهَبْنَا لَهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُمْ مَعَهُمْ رَحْمَةً مِنَّا وَذِكْرَى لِأوْلِي الأَلْبَابِ |
Wa Khudh Biyadika Đighthāan Fāđrib Bihi Wa Lā Taĥnath 'Innā Wa Jadnāhu Şābirāan Ni`ma Al-`Abdu 'Innahu 'Awwābun  | 038-044 آ«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስآ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡ | وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثاً فَاضْرِبْ بِهِ وَلاَ تَحْنَثْ إِنَّا وَجَدْنَاهُ صَابِراً نِعْمَ الْعَبْدُ إِنَّهُ أَوَّابٌ |
Wa Adhkur `Ibādanā 'Ibrāhīma Wa 'Isĥāqa Wa Ya`qūba 'Ūlī Al-'Aydī Wa Al-'Abşāri  | 038-045 ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡ | وَاذْكُرْ عِبَادَنَا إبْرَاهِيمَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ أُوْلِي الأَيْدِي وَالأَبْصَارِ |
'Innā 'Akhlaşnāhum Bikhālişatin Dhikrá Ad-Dāri  | 038-046 እኛ ጥሩ በኾነች ጠባይ መረጥናቸው፡፡ (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡ | إِنَّا أَخْلَصْنَاهُمْ بِخَالِصَةٍ ذِكْرَى الدَّارِ |
Wa 'Innahum `Indanā Lamina Al-Muşţafayna Al-'Akhyāri  | 038-047 እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው፡፡ | وَإِنَّهُمْ عِنْدَنَا لَمِنَ الْمُصْطَفَيْنَ الأَخْيَارِ |
Wa Adhkur 'Ismā`īla Wa Al-Yasa`a Wa Dhā Al-Kifli Wa Kullun Mina Al-'Akhyāri  | 038-048 ኢስማዒልንም፣ አልየሰዕንም፣ ዙልኪፍልንም አውሳ፡፡ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡ | وَاذْكُرْ إِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَذَا الْكِفْلِ وَكُلٌّ مِنَ الأَخْيَارِ |
Hādhā Dhikrun Wa 'Inna Lilmuttaqīna Laĥusna Ma'ābin  | 038-049 ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ ለአላህ ፈሪዎችም በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው፡፡ | هَذَا ذِكْرٌ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَآبٍ |
Jannāti `Adnin Mufattaĥatan Lahumu Al-'Abwābu  | 038-050 በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲኾኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡ | جَنَّاتِ عَدْنٍ مُفَتَّحَةً لَهُمُ الأَبْوَابُ |
Muttaki'īna Fīhā Yad`ūna Fīhā Bifākihatin Kathīratin Wa Sharābin  | 038-051 በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ኾነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ፡፡ | مُتَّكِئِينَ فِيهَا يَدْعُونَ فِيهَا بِفَاكِهَةٍ كَثِيرَةٍ وَشَرَابٍ |
Wa `Indahum Qāşirātu Aţ-Ţarfi 'Atrābun  | 038-052 እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች እኩያዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ | وَعِنْدَهُمْ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ أَتْرَابٌ |
Hādhā Mā Tū`adūna Liyawmi Al-Ĥisābi  | 038-053 ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተሰፋ ነው፡፡ | هَذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوْمِ الْحِسَابِ |
'Inna Hādhā Larizqunā Mā Lahu Min Nafādin  | 038-054 ይህ ሲሳያችን ነው፡፡ ለእርሱ ምንም ማለቅ የለውም፡፡ | إِنَّ هَذَا لَرِزْقُنَا مَا لَهُ مِنْ نَفَادٍ |
Hādhā Wa 'Inna Lilţţāghīna Lasharra Ma'ābin  | 038-055 ይህ (ለአማኞች ነው)፡፡ ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው፡፡ | هَذَا وَإِنَّ لِلطَّاغِينَ لَشَرَّ مَآبٍ |
Jahannama Yaşlawnahā Fabi'sa Al-Mihādu  | 038-056 የሚገቧት ስትኾን ገሀነም (አለቻቸው)፡፡ ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች፡፡ | جَهَنَّمَ يَصْلَوْنَهَا فَبِئْسَ الْمِهَادُ |
Hādhā Falyadhūqūhu Ĥamīmun Wa Ghassāqun  | 038-057 ይህ (ለከሓዲዎች ነው)፡፡ ይቅመሱትም፡፡ የፈላ ውሃና እዥ ነው፡፡ | هَذَا فَلْيَذُوقُوهُ حَمِيمٌ وَغَسَّاقٌ |
Wa 'Ākharu Min Shaklihi 'Azwājun  | 038-058 ሌላም ከመሰሉ ዓይነቶች አልሉ፡፡ | وَآخَرُ مِنْ شَكْلِهِ أَزْوَاجٌ |
Hādhā Fawjun Muqtaĥimun Ma`akum Lā Marĥabāan Bihim 'Innahum Şālū An-Nāri  | 038-059 ይህ ከእናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ጭፍራ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ለእነርሱ አይስፋቸው፡፡ እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)፡፡ | هَذَا فَوْجٌ مُقْتَحِمٌ مَعَكُمْ لاَ مَرْحَباً بِهِمْ إِنَّهُمْ صَالُوا النَّارِ |
Qālū Bal 'Antum Lā Marĥabāan Bikum 'Antum Qaddamtumūhu Lanā Fabi'sa Al-Qarāru  | 038-060 (ተከታዮቹ) ይላሉ آ«ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ፡፡ እናንተ (ክህደቱን) ለእኛ አቀረባችሁት፡፡ መርጊያይቱም (ገሀነም) ከፋች፡፡آ» | قَالُوا بَلْ أَنْتُمْ لاَ مَرْحَباً بِكُمْ أَنْتُمْ قَدَّمْتُمُوهُ لَنَا فَبِئْسَ الْقَرَارُ |
Qālū Rabbanā Man Qaddama Lanā Hādhā Fazid/hu `Adhābāan Đi`fāan Fī An-Nāri  | 038-061 آ«ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ እጥፍን ቅጣት ጨምርለትآ» ይላሉ፡፡ | قَالُوا رَبَّنَا مَنْ قَدَّمَ لَنَا هَذَا فَزِدْهُ عَذَاباً ضِعْفاً فِي النَّارِ |
Wa Qālū Mā Lanā Lā Nará Rijālāan Kunnā Na`udduhum Mina Al-'Ashrār  | 038-062 ይላሉም آ«ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች (እዚህ) አናይምሳ፡፡آ» | وَقَالُوا مَا لَنَا لاَ نَرَى رِجَالاً كُنَّا نَعُدُّهُمْ مِنَ الأَشْرَار |
'Āttakhadhnāhum Sikhrīyāan 'Am Zāghat `Anhumu Al-'Abşāru  | 038-063 آ«መቀለጃ አድርገን ያዝናቸውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነሱ ዋለሉ?آ» | أَاتَّخَذْنَاهُمْ سِخْرِيّاً أَمْ زَاغَتْ عَنْهُمُ الأَبْصَارُ |
'Inna Dhālika Laĥaqqun Takhāşumu 'Ahli An-Nāri  | 038-064 ይህ በእርግጥ እምነት ነው፡፡ (እርሱም) የእሳት ሰዎች (የእርስ በእርስ) መካሰስ ነው፡፡ | إِنَّ ذَلِكَ لَحَقٌّ تَخَاصُمُ أَهْلِ النَّارِ |
Qul 'Innamā 'Anā Mundhirun Wa Mā Min 'Ilahin 'Illā Al-Lahu Al-Wāĥidu Al-Qahhāru  | 038-065 آ«እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ፡፡ ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለምآ» በላቸው፡፡ | قُلْ إِنَّمَا أَنَا مُنذِرٌ وَمَا مِنْ إِلَهٍ إِلاَّ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ |
Rabbu As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Mā Baynahumā Al-`Azīzu Al-Ghaffāru  | 038-066 آ«የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡آ» | رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الْعَزِيزُ الْغَفَّارُ |
Qul Huwa Naba'un `Ažīmun  | 038-067 በላቸው آ«እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው፡፡ | قُلْ هُوَ نَبَأٌ عَظِيمٌ |
'Antum `Anhu Mu`riđūna  | 038-068 آ«እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ | أَنْتُمْ عَنْهُ مُعْرِضُونَ |
Mā Kāna Liya Min `Ilmin Bil-Mala'i Al-'A`lá 'Idh Yakhtaşimūna  | 038-069 (በአደም ነገር) آ«በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡ | مَا كَانَ لِيَ مِنْ عِلْمٍ بِالْمَلَإِ الأَعْلَى إِذْ يَخْتَصِمُونَ |
'In Yūĥá 'Ilayya 'Illā 'Annamā 'Anā Nadhīrun Mubīnun  | 038-070 آ«ወደእኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝምآ» (በል)፡፡ | إِنْ يُوحَى إِلَيَّ إِلاَّ أَنَّمَا أَنَا نَذِيرٌ مُبِينٌ |
'Idh Qāla Rabbuka Lilmalā'ikati 'Innī Khāliqun Basharāan Min Ţīnin  | 038-071 ጌታህ آ«ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜآ» (አስታውስ)፡፡ | إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلاَئِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَراً مِنْ طِينٍ |
Fa'idhā Sawwaytuhu Wa Nafakhtu Fīhi Min Rūĥī Faqa`ū Lahu Sājidīna  | 038-072 آ«ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁآ» (አልኩ)፡፡ | فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِنْ رُوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ |
Fasajada Al-Malā'ikatu Kulluhum 'Ajma`ūna  | 038-073 መላእክትም መላውም ባንድነት ሰገዱ፡፡ | فَسَجَدَ الْمَلاَئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ |
'Illā 'Iblīsa Astakbara Wa Kāna Mina Al-Kāfirīna  | 038-074 ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ኮራ፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡ | إِلاَّ إِبْلِيسَ اسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ |
Qāla Yā 'Iblīsu Mā Mana`aka 'An Tasjuda Limā Khalaqtu Biyadayya 'Āstakbarta 'Am Kunta Mina Al-`Ālīna  | 038-075 (አላህም) آ«ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?آ» አለው፡፡ | قَالَ يَاإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَنْ تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَيَّ أَاسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْعَالِينَ |
Qāla 'Anā Khayrun Minhu Khalaqtanī Min Nārin Wa Khalaqtahu Min Ţīnin  | 038-076 آ«እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ ከጭቃም ፈጠርከውآ» አለ፡፡ | قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِنْهُ خَلَقْتَنِي مِنْ نَارٍ وَخَلَقْتَهُ مِنْ طِينٍ |
Qāla Fākhruj Minhā Fa'innaka Rajīmun  | 038-077 (አላህ) አለው آ«ከእርሷ ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና፡፡آ» | قَالَ فَاخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ |
Wa 'Inna `Alayka La`natī 'Ilá Yawmi Ad-Dīni  | 038-078 آ«እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን፡፡آ» | وَإِنَّ عَلَيْكَ لَعْنَتِي إِلَى يَوْمِ الدِّينِ |
Qāla Rabbi Fa'anžirnī 'Ilá Yawmi Yub`athūna  | 038-079 آ«ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝምآ» አለ፡፡ | قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِي إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ |
Qāla Fa'innaka Mina Al-Munžarīna  | 038-080 (አላህም) አለው آ«አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡آ» | قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ الْمُنظَرِينَ |
'Ilá Yawmi Al-Waqti Al-Ma`lūmi  | 038-081 آ«እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡آ» | إِلَى يَوْمِ الْوَقْتِ الْمَعْلُومِ |
Qāla Fabi`izzatika La'ughwiyannahum 'Ajma`īna  | 038-082 (እርሱም) አለ آ«በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡آ» | قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ |
'Illā `Ibādaka Minhumu Al-Mukhlaşīna  | 038-083 آ«ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡آ» | إِلاَّ عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ |
Qāla Fālĥaqqu Wa Al-Ĥaqqa 'Aqūlu  | 038-084 (አላህ) አለው آ«እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡ | قَالَ فَالْحَقُّ وَالْحَقَّ أَقُولُ |
La'amla'anna Jahannama Minka Wa Mimman Tabi`aka Minhum 'Ajma`īna  | 038-085 ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡آ» | لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنْكَ وَمِمَّنْ تَبِعَكَ مِنْهُمْ أَجْمَعِينَ |
Qul Mā 'As'alukum `Alayhi Min 'Ajrin Wa Mā 'Anā Mina Al-Mutakallifīna  | 038-086 በላቸው آ«በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም፡፡ | قُلْ مَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُتَكَلِّفِينَ |
'In Huwa 'Illā Dhikrun Lil`ālamīna  | 038-087 آ«እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ | إِنْ هُوَ إِلاَّ ذِكْرٌ لِلْعَالَمِينَ |
Wa Lata`lamunna Naba'ahu Ba`da Ĥīnin  | 038-088 آ«ትንቢቱንም (እውነት መኾኑን) ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡آ» | وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ |