'Alif-Lām-Rā Tilka 'Āyātu Al-Kitābi Wa Qur'ānin Mubīnin  | 015-001 አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾችና ገላጭ ከኾነው ቁርኣን ናት፡፡ | أَلِف-لَام-رَا تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ وَقُرْآنٍ مُبِينٍ |
Rubamā Yawaddu Al-Ladhīna Kafarū Law Kānū Muslimīna  | 015-002 እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ | رُبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ |
Dharhum Ya'kulū Wa Yatamatta`ū Wa Yulhihimu Al-'Amalu Fasawfa Ya`lamūna  | 015-003 ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡ | ذَرْهُمْ يَأْكُلُوا وَيَتَمَتَّعُوا وَيُلْهِهِمُ الأَمَلُ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ |
Wa Mā 'Ahlaknā Min Qaryatin 'Illā Wa Lahā Kitābun Ma`lūmun  | 015-004 ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ (ጊዜያት) ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም፡፡ | وَمَا أَهْلَكْنَا مِنْ قَرْيَةٍ إِلاَّ وَلَهَا كِتَابٌ مَعْلُومٌ |
Mā Tasbiqu Min 'Ummatin 'Ajalahā Wa Mā Yasta'khirūna  | 015-005 ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜዋን ምንም አትቀድምም፡፡ (ከእርሱ) አይቆዩምም፡፡ | مَا تَسْبِقُ مِنْ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسْتَأْخِرُونَ |
Wa Qālū Yā 'Ayyuhā Al-Ladhī Nuzzila `Alayhi Adh-Dhikru 'Innaka Lamajnūnun  | 015-006 آ«አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህآ» አሉም፡፡ | وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ |
Law Mā Ta'tīnā Bil-Malā'ikati 'In Kunta Mina Aş-Şādiqīna  | 015-007 آ«ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት (መስካሪ) ለምን አትመጣንምآ» (አሉ)፡፡ | لَوْ مَا تَأْتِينَا بِالْمَلاَئِكَةِ إِنْ كُنْتَ مِنَ الصَّادِقِينَ |
Mā Nunazzilu Al-Malā'ikata 'Illā Bil-Ĥaqqi Wa Mā Kānū 'Idhāan Munžarīna  | 015-008 መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡ | مَا نُنَزِّلُ الْمَلاَئِكَةَ إِلاَّ بِالْحَقِّ وَمَا كَانُوا إِذاً مُنْظَرِينَ |
'Innā Naĥnu Nazzalnā Adh-Dhikra Wa 'Innā Lahu Laĥāfižūna  | 015-009 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ | إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ |
Wa Laqad 'Arsalnā Min Qablika Fī Shiya`i Al-'Awwalīna  | 015-010 ከአንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልክተኞችን) በእርግጥ ልከናል፡፡ | وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ فِي شِيَعِ الأَوَّلِينَ |
Wa Mā Ya'tīhim Min Rasūlin 'Illā Kānū Bihi Yastahzi'ūna  | 015-011 ማንኛውም መልእክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ኾነው እንጅ አይመጣቸውም ነበር፡፡ | وَمَا يَأْتِيهِمْ مِنْ رَسُولٍ إِلاَّ كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ |
Kadhālika Naslukuhu Fī Qulūbi Al-Mujrimīna  | 015-012 እንደዚሁ (ማስተባበልን) በአመጸኞቹ ልቦች ውስጥ እናገባዋለን፡፡ | كَذَلِكَ نَسْلُكُهُ فِي قُلُوبِ الْمُجْرِمِينَ |
Lā Yu'uminūna Bihi Wa Qad Khalat Sunnatu Al-'Awwalīna  | 015-013 በእርሱ አያምኑበትም፡፡ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች፤ (እንደጠፉ ይጠፋሉ)፡፡ | لاَ يُؤْمِنُونَ بِهِ وَقَدْ خَلَتْ سُنَّةُ الأَوَّلِينَ |
Wa Law Fataĥnā `Alayhim Bābāan Mina As-Samā'i Fažallū Fīhi Ya`rujūna  | 015-014 በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ፤ | وَلَوْ فَتَحْنَا عَلَيْهِمْ بَاباً مِنَ السَّمَاءِ فَظَلُّوا فِيهِ يَعْرُجُونَ |
Laqālū 'Innamā Sukkirat 'Abşārunā Bal Naĥnu Qawmun Masĥūrūna  | 015-015 آ«የተዘጉት ዓይኖቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነንآ» ባሉ ነበር፡፡ | لَقَالُوا إِنَّمَا سُكِّرَتْ أَبْصَارُنَا بَلْ نَحْنُ قَوْمٌ مَسْحُورُونَ |
Wa Laqad Ja`alnā Fī As-Samā'i Burūjāan Wa Zayyannāhā Lilnnāžirīna  | 015-016 በሰማይም ላይ ቡርጆችን በእርግጥ አድርገናል፡፡ ለተመልካቾችም (በከዋክብት) አጊጠናታል፡፡ | وَلَقَدْ جَعَلْنَا فِي السَّمَاءِ بُرُوجاً وَزَيَّنَّاهَا لِلنَّاظِرِينَ |
Wa Ĥafižnāhā Min Kulli Shayţānin Rajīmin  | 015-017 ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል፡፡ | وَحَفِظْنَاهَا مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ رَجِيمٍ |
'Illā Mani Astaraqa As-Sam`a Fa'atba`ahu Shihābun Mubīnun  | 015-018 ግን (ወሬ) መስማትን የሚሰርቅ ወዲየውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል፡፡ (ያቃጥለዋል)፡፡ | إِلاَّ مَنِ اسْتَرَقَ السَّمْعَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ مُبِينٌ |
Wa Al-'Arđa Madadnāhā Wa 'Alqaynā Fīhā Rawāsiya Wa 'Anbatnā Fīhā Min Kulli Shay'in Mawzūnin  | 015-019 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ በውስጧም (የተለካን) በቃይ ሁሉ አበቀልንባት፡፡ | وَالأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْبَتْنَا فِيهَا مِنْ كُلِّ شَيْءٍ مَوْزُونٍ |
Wa Ja`alnā Lakum Fīhā Ma`āyisha Wa Man Lastum Lahu Birāziqīna  | 015-020 በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልኾናችሁትንም (እንስሳትን) አደረግንላችሁ፡፡ | وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَايِشَ وَمَنْ لَسْتُمْ لَهُ بِرَازِقِينَ |
Wa 'In Min Shay'in 'Illā `Indanā Khazā'inuhu Wa Mā Nunazziluhu 'Illā Biqadarin Ma`lūmin  | 015-021 መካዚኖቹም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡ | وَإِنْ مِنْ شَيْءٍ إِلاَّ عِنْدَنَا خَزَائِنُهُ وَمَا نُنَزِّلُهُ إِلاَّ بِقَدَرٍ مَعْلُومٍ |
Wa 'Arsalnā Ar-Riyāĥa Lawāqiĥa Fa'anzalnā Mina As-Samā'i Mā'an Fa'asqaynākumūhu Wa Mā 'Antum Lahu Bikhāzinīna  | 015-022 ነፋሶችንም (ደመናን) ተሸካሚዎች አድርገን ላክን፡፡ ከሰማይም (ከደመና) ዝናብን አወረድን፡፡ እርሱንም አጠጣናችሁ፡፡ እናንተም ለእርሱ አድላቢዎች አይደላችሁም፡፡ | وَأَرْسَلْنَا الرِّيَاحَ لَوَاقِحَ فَأَنْزَلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَسْقَيْنَاكُمُوهُ وَمَا أَنْتُمْ لَهُ بِخَازِنِينَ |
Wa 'Innā Lanaĥnu Nuĥyī Wa Numītu Wa Naĥnu Al-Wārithūna  | 015-023 እኛም ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን፡፡ እኛም (ፍጡርን ሁሉ ) የምንወርስ (ቀሪ) ነን፡፡ | وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَنَحْنُ الْوَارِثُونَ |
Wa Laqad `Alimnā Al-Mustaqdimīna Minkum Wa Laqad `Alimnā Al-Musta'khirīna  | 015-024 ከእናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ወደ ኋላም ቀሪዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ | وَلَقَدْ عَلِمْنَا الْمُسْتَقْدِمِينَ مِنْكُمْ وَلَقَدْ عَلِمْنَا الْمُسْتَأْخِرِينَ |
Wa 'Inna Rabbaka Huwa Yaĥshuruhum 'Innahu Ĥakīmun `Alīmun  | 015-025 ጌታህም እርሱ ይሰበስባችኋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡ | وَإِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَحْشُرُهُمْ إِنَّهُ حَكِيمٌ عَلِيمٌ |
Wa Laqad Khalaqnā Al-'Insāna Min Şalşālin Min Ĥama'iin Masnūnin  | 015-026 ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው፡፡ | وَلَقَدْ خَلَقْنَا الإِنسَانَ مِنْ صَلْصَالٍ مِنْ حَمَإٍ مَسْنُونٍ |
Wa Al-Jānna Khalaqnāhu Min Qablu Min Nāri As-Samūmi  | 015-027 ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡ | وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِنْ قَبْلُ مِنْ نَارِ السَّمُومِ |
Wa 'Idh Qāla Rabbuka Lilmalā'ikati 'Innī Khāliqun Basharāan Min Şalşālin Min Ĥama'iin Masnūnin  | 015-028 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ፡፡ | وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلاَئِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَراً مِنْ صَلْصَالٍ مِنْ حَمَإٍ مَسْنُونٍ |
Fa'idhā Sawwaytuhu Wa Nafakhtu Fīhi Min Rūĥī Faqa`ū Lahu Sājidīna  | 015-029 (ፍጥረቱን) ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ፡፡ | فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِنْ رُوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ |
Fasajada Al-Malā'ikatu Kulluhum 'Ajma`ūna  | 015-030 መላእክትም መላውም ተሰብስበው ሰገዱ፡፡ | فَسَجَدَ الْمَلاَئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ |
'Illā 'Iblīsa 'Abá 'An Yakūna Ma`a As-Sājidīna  | 015-031 ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር፡፡ ከሰጋጆቹ ጋር ከመኾን እንቢ አለ፡፡ | إِلاَّ إِبْلِيسَ أَبَى أَنْ يَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ |
Qāla Yā 'Iblīsu Mā Laka 'Allā Takūna Ma`a As-Sājidīna  | 015-032 (አላህም) آ«ኢብሊስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ላንተ ምን ምክንያት አለህآ» አለው፡፡ | قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا لَكَ أَلاَّ تَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ |
Qāla Lam 'Akun Li'sjuda Libasharin Khalaqtahu Min Şalşālin Min Ĥama'iin Masnūnin  | 015-033 آ«ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝምآ» አለ፡፡ | قَالَ لَمْ أَكُنْ لِأسْجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقْتَهُ مِنْ صَلْصَالٍ مِنْ حَمَإٍ مَسْنُونٍ |
Qāla Fākhruj Minhā Fa'innaka Rajīmun  | 015-034 (አላህ) አለው آ«ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡آ» | قَالَ فَاخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ |
Wa 'Inna `Alayka Al-La`nata 'Ilá Yawmi Ad-Dīni  | 015-035 آ«ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ፡፡آ» | وَإِنَّ عَلَيْكَ اللَّعْنَةَ إِلَى يَوْمِ الدِّينِ |
Qāla Rabbi Fa'anžirnī 'Ilá Yawmi Yub`athūna  | 015-036 آ«ጌታዬ ሆይ! እንግዲውያስ (ሰዎች) እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝآ» አለ፡፡ | قَالَ رَبِّ فَأَنْظِرْنِي إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ |
Qāla Fa'innaka Mina Al-Munžarīna  | 015-037 (አላህም) አለ آ«አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡ | قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ الْمُنْظَرِينَ |
'Ilá Yawmi Al-Waqti Al-Ma`lūmi  | 015-038 آ«እስከታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡آ» | إِلَى يَوْمِ الْوَقْتِ الْمَعْلُومِ |
Qāla Rabbi Bimā 'Aghwaytanī La'uzayyinanna Lahum Fī Al-'Arđi Wa La'ughwiyannahum 'Ajma`īna  | 015-039 (ኢብሊስ) አለ آ«ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ (ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡آ» | قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِي الأَرْضِ وَلَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ |
'Illā `Ibādaka Minhumu Al-Mukhlaşīna  | 015-040 آ«ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡آ» | إِلاَّ عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ |
Qāla Hādhā Şirāţun `Alayya Mustaqīmun  | 015-041 (አላህም) አለ آ«ይህ በእኔ ላይ (መጠበቁ የተገባ) ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡آ» | قَالَ هَذَا صِرَاطٌ عَلَيَّ مُسْتَقِيمٌ |
'Inna `Ibādī Laysa Laka `Alayhim Sulţānun 'Illā Mani Attaba`aka Mina Al-Ghāwīna  | 015-042 آ«እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡آ» | إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ إِلاَّ مَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْغَاوِينَ |
Wa 'Inna Jahannama Lamaw`iduhum 'Ajma`īna  | 015-043 آ«ገሀነምም (ለርሱና ለተከተሉት) ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ | وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ |
Lahā Sab`atu 'Abwābin Likulli Bābin Minhum Juz'un Maqsūmun  | 015-044 آ«ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ | لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَابٍ لِكُلِّ بَابٍ مِنْهُمْ جُزْءٌ مَقْسُومٌ |
'Inna Al-Muttaqīna Fī Jannātin Wa `Uyūnin  | 015-045 آ«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ | إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
Adkhulūhā Bisalāmin 'Āminīna  | 015-046 آ«ጸጥተኞች ኾናችሁ በሰላም ግቧት (ይባላሉ)፡፡ | ادْخُلُوهَا بِسَلاَمٍ آمِنِينَ |
Wa Naza`nā Mā Fī Şudūrihim Min Ghillin 'Ikhwānāan `Alá Sururin Mutaqābilīna  | 015-047 آ«ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡ | وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِمْ مِنْ غِلٍّ إِخْوَاناً عَلَى سُرُرٍ مُتَقَابِلِينَ |
Lā Yamassuhum Fīhā Naşabun Wa Mā Hum Minhā Bimukhrajīna  | 015-048 آ«በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካቸውም፡፡ እነሱም ከእርሷ የሚወጡ አይደሉም፡፡آ» | لاَ يَمَسُّهُمْ فِيهَا نَصَبٌ وَمَا هُمْ مِنْهَا بِمُخْرَجِينَ |
Nabbi' `Ibādī 'Annī 'Anā Al-Ghafūru Ar-Raĥīmu  | 015-049 ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡ | نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ |
Wa 'Anna `Adhābī Huwa Al-`Adhābu Al-'Alīmu  | 015-050 ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡ | وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الأَلِيمُ |
Wa Nabbi'hum `An Đayfi 'Ibrāhīma  | 015-051 ከኢብራሂም እንግዶችም (ወሬ) ንገራቸው፡፡ | وَنَبِّئْهُمْ عَنْ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ |
'Idh Dakhalū `Alayhi Faqālū Salāmāan Qāla 'Innā Minkum Wajilūna  | 015-052 በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን (አስታውስ)፡፡ (እርሱም) آ«እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነንآ» አላቸው፡፡ | إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلاَماً قَالَ إِنَّا مِنْكُمْ وَجِلُونَ |
Qālū Lā Tawjal 'Innā Nubashshiruka Bighulāmin `Alīmin  | 015-053 آ«አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለንآ» አሉት፡፡ | قَالُوا لاَ تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلاَمٍ عَلِيمٍ |
Qāla 'Abashshartumūnī `Alá 'An Massaniya Al-Kibaru Fabima Tubashshirūna  | 015-054 آ«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁآ» አለ፡፡ | قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِي عَلَى أَنْ مَسَّنِيَ الْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ |
Qālū Bashsharnāka Bil-Ĥaqqi Falā Takun Mina Al-Qāniţīna  | 015-055 آ«በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹንآ» አሉ፡፡ | قَالُوا بَشَّرْنَاكَ بِالْحَقِّ فَلاَ تَكُنْ مِنَ الْقَانِطِينَ |
Qāla Wa Man Yaqnaţu Min Raĥmati Rabbihi 'Illā Ađ-Đāllūna  | 015-056 آ«ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነውآ» አለ፡፡ | قَالَ وَمَنْ يَقْنَطُ مِنْ رَحْمَةِ رَبِّهِ إِلاَّ الضَّالُّونَ |
Qāla Famā Khaţbukum 'Ayyuhā Al-Mursalūna  | 015-057 آ«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ኧረ ለመኾኑ ነገራችሁ ምንድን ነውآ» አለ፡፡ | قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ |
Qālū 'Innā 'Ursilnā 'Ilá Qawmin Mujrimīna  | 015-058 آ«እኛ አመጸኞች ወደ ኾኑ ሕዝቦች ተልከናልآ» አሉት፡፡ | قَالُوا إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَى قَوْمٍ مُجْرِمِينَ |
'Illā 'Āla Lūţin 'Innā Lamunajjūhum 'Ajma`īna  | 015-059 آ«የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነርሱን) እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን፡፡ | إِلاَّ آلَ لُوطٍ إِنَّا لَمُنَجُّوهُمْ أَجْمَعِينَ |
'Illā Amra'atahu Qaddarnā 'Innahā Lamina Al-Ghābirīna  | 015-060 آ«ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷን (በቅጣቱ ውስጥ) ከሚቀሩት መኾኗን ወሰነናልآ» (አሉ)፡፡ | إِلاَّ امْرَأَتَهُ قَدَّرْنَا إِنَّهَا لَمِنَ الْغَابِرِينَ |
Falammā Jā'a 'Āla Lūţin Al-Mursalūna  | 015-061 መልክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ፤ | فَلَمَّا جَاءَ آلَ لُوطٍ الْمُرْسَلُونَ |
Qāla 'Innakum Qawmun Munkarūna  | 015-062 (ሉጥ) آ«እናንተ የተሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁآ» አላቸው፡፡ | قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ مُنْكَرُونَ |
Qālū Bal Ji'nāka Bimā Kānū Fīhi Yamtarūna  | 015-063 آ«አይደለም እኛ ሕዝቦችህ በርሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንህآ» አሉት፡፡ | قَالُوا بَلْ جِئْنَاكَ بِمَا كَانُوا فِيهِ يَمْتَرُونَ |
Wa 'Ataynāka Bil-Ĥaqqi Wa 'Innā Laşādiqūna  | 015-064 آ«እውነትንም ይዘን መጣንህ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡ | وَأَتَيْنَاكَ بِالْحَقِّ وَإِنَّا لَصَادِقُونَ |
Fa'asri Bi'ahlika Biqiţ`in Mina Al-Layli Wa Attabi` 'Adbārahum Wa Lā Yaltafit Minkum 'Aĥadun Wa Amđū Ĥaythu Tu'umarūna  | 015-065 ከቤተሰብህም ጋር በሌሊቱ ከፊል ኺድ፡፡ ከኋላቸውም ተከተል፡፡ ከእናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ፡፡ ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉآ» (አሉት)፡፡ | فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِنَ اللَّيْلِ وَاتَّبِعْ أَدْبَارَهُمْ وَلاَ يَلْتَفِتْ مِنْكُمْ أَحَدٌ وَامْضُوا حَيْثُ تُؤْمَرُونَ |
Wa Qađaynā 'Ilayhi Dhālika Al-'Amra 'Anna Dābira Hā'uulā' Maqţū`un Muşbiĥīna  | 015-066 ወደርሱም ያንን ትእዛዝ አወረድን፡፡ (እርሱም) የእነዚህ (ሕዝቦች) መጨረሻ ያነጉ ሲኾኑ (ሥራቸው) መቆረጥ ነው፡፡ | وَقَضَيْنَا إِلَيْهِ ذَلِكَ الأَمْرَ أَنَّ دَابِرَ هَاؤُلاَء مَقْطُوعٌ مُصْبِحِينَ |
Wa Jā'a 'Ahlu Al-Madīnati Yastabshirūna  | 015-067 የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ኾነው መጡ፡፡ | وَجَاءَ أَهْلُ الْمَدِينَةِ يَسْتَبْشِرُونَ |
Qāla 'Inna Hā'uulā' Đayfī Falā Tafđaĥūni  | 015-068 (ሉጥም) አለ آ«እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ፡፡ | قَالَ إِنَّ هَاؤُلاَء ضَيْفِي فَلاَ تَفْضَحُونِ |
Wa Attaqū Al-Laha Wa Lā Tukhzūni  | 015-069 آ«አላህንም ፍሩ፤ አታሳፍሩኝም፡፡آ» | وَاتَّقُوا اللَّهَ وَلاَ تُخْزُونِ |
Qālū 'Awalam Nanhaka `Ani Al-`Ālamīna  | 015-070 آ«ከዓለማት (ማንንም እንዳታስተናግድ) አልከለከልንህምንآ» አሉት፡፡ | قَالُوا أَوَلَمْ نَنْهَكَ عَنِ الْعَالَمِينَ |
Qāla Hā'uulā' Banātī 'In Kuntum Fā`ilīna  | 015-071 (ሉጥም) آ«እነኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (አግቧቸው)آ» አለ፡፡ | قَالَ هَاؤُلاَء بَنَاتِي إِنْ كُنْتُمْ فَاعِلِينَ |
La`amruka 'Innahum Lafī Sakratihim Ya`mahūna  | 015-072 በዕድሜህ እንምላለን እነሱ በእርግጥ በስከራቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡ | لَعَمْرُكَ إِنَّهُمْ لَفِي سَكْرَتِهِمْ يَعْمَهُونَ |
Fa'akhadhat/humu Aş-Şayĥatu Mushriqīna  | 015-073 ጩኸቲቱም ፀሐይ የወጣችባቸው ሲኾኑ ያዘቻቸው፡፡ | فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ مُشْرِقِينَ |
Faja`alnā `Āliyahā Sāfilahā Wa 'Amţarnā `Alayhim Ĥijāratan Min Sijjīlin  | 015-074 ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ | فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِنْ سِجِّيلٍ |
'Inna Fī Dhālika La'āyātin Lilmutawassimīna  | 015-075 በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡ | إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لِلْمُتَوَسِّمِينَ |
Wa 'Innahā Labisabīlin Muqīmin  | 015-076 እሷም (ከተማይቱ) በቀጥታ መንገድ ላይ ናት፡፡ | وَإِنَّهَا لَبِسَبِيلٍ مُقِيمٍ |
'Inna Fī Dhālika La'āyatan Lilmu'uminīna  | 015-077 በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለምእምናን መገሰጫ አለ፡፡ | إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَةً لِلْمُؤْمِنِينَ |
Wa 'In Kāna 'Aşĥābu Al-'Aykati Lažālimīna  | 015-078 እነሆ የአይከት ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ፤ | وَإِنْ كَانَ أَصْحَابُ الأَيْكَةِ لَظَالِمِينَ |
Fāntaqamnā Minhum Wa 'Innahumā Labi'imāmin Mubīnin  | 015-079 ከነሱም ተበቀልን ሁለቱም (የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች) በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው፡፡ | فَانْتَقَمْنَا مِنْهُمْ وَإِنَّهُمَا لَبِإِمَامٍ مُبِينٍ |
Wa Laqad Kadhdhaba 'Aşĥābu Al-Ĥijri Al-Mursalīna  | 015-080 የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ | وَلَقَدْ كَذَّبَ أَصْحَابُ الْحِجْرِ الْمُرْسَلِينَ |
Wa 'Ātaynāhum 'Āyātinā Fakānū `Anhā Mu`riđīna  | 015-081 ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡ | وَآتَيْنَاهُمْ آيَاتِنَا فَكَانُوا عَنْهَا مُعْرِضِينَ |
Wa Kānū Yanĥitūna Mina Al-Jibāli Buyūtāan 'Āminīna  | 015-082 ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡ | وَكَانُوا يَنْحِتُونَ مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتاً آمِنِينَ |
Fa'akhadhat/humu Aş-Şayĥatu Muşbiĥīna  | 015-083 ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡ | فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ مُصْبِحِينَ |
Famā 'Aghná `Anhum Mā Kānū Yaksibūna  | 015-084 ይሠሩትም የነበሩት ሕንጻ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ | فَمَا أَغْنَى عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَكْسِبُونَ |
Wa Mā Khalaqnā As-Samāwāti Wa Al-'Arđa Wa Mā Baynahumā 'Illā Bil-Ĥaqqi Wa 'Inna As-Sā`ata La'ātiyatun Fāşfaĥi Aş-Şafĥa Al-Jamīla  | 015-085 ሰማያትንና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ (በላግጣ) አልፈጠርንም፡፡ ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት፡፡ መልካምንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡ | وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا إِلاَّ بِالْحَقِّ وَإِنَّ السَّاعَةَ لَآتِيَةٌ فَاصْفَحِ الصَّفْحَ الْجَمِيلَ |
'Inna Rabbaka Huwa Al-Khallāqu Al-`Alīmu  | 015-086 ጌታህ እርሱ (ያልነበረን) ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡ | إِنَّ رَبَّكَ هُوَ الْخَلاَّقُ الْعَلِيمُ |
Wa Laqad 'Ātaynāka Sab`āan Mina Al-Mathānī Wa Al-Qur'āna Al-`Ažīma  | 015-087 ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ | وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعاً مِنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ |
Lā Tamuddanna `Aynayka 'Ilá Mā Matta`nā Bihi 'Azwājāan Minhum Wa Lā Taĥzan `Alayhim Wa Akhfiđ Janāĥaka Lilmu'uminīna  | 015-088 ከእነርሱ (ከከሓዲዎች) ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፡፡ በእነሱም ላይ (ባያምኑ) አትዘን፡፡ ክንፍህንም ለምእምናን አለዝብ፡፡ | لاَ تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَى مَا مَتَّعْنَا بِهِ أَزْوَاجاً مِنْهُمْ وَلاَ تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَاخْفِضْ جَنَاحَكَ لِلْمُؤْمِنِينَ |
Wa Qul 'Innī 'Anā An-Nadhīru Al-Mubīnu  | 015-089 በልም آ«እኔ ግልጽ አስፈራሪው እኔ ነኝ፡፡آ» | وَقُلْ إِنِّي أَنَا النَّذِيرُ الْمُبِينُ |
Kamā 'Anzalnā `Alá Al-Muqtasimīna  | 015-090 (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (በኾነ ቅጣት አሰፈራሪያችሁ ነኝ በል)፡፡ | كَمَا أَنْزَلْنَا عَلَى الْمُقْتَسِمِينَ |
Al-Ladhīna Ja`alū Al-Qur'āna `Iđīna  | 015-091 (እነርሱም) እነዚያ ቁርኣንንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው፡፡ | الَّذِينَ جَعَلُوا الْقُرْآنَ عِضِينَ |
Fawarabbika Lanas'alannahum 'Ajma`īna  | 015-092 በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ | فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ |
`Ammā Kānū Ya`malūna  | 015-093 ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡ | عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ |
Fāşda` Bimā Tu'umaru Wa 'A`riđ `Ani Al-Mushrikīna  | 015-094 የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡ | فَاصْدَعْ بِمَا تُؤْمَرُ وَأَعْرِضْ عَنِ الْمُشْرِكِينَ |
'Innā Kafaynāka Al-Mustahzi'īna  | 015-095 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡ | إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ |
Al-Ladhīna Yaj`alūna Ma`a Al-Lahi 'Ilahāan 'Ākhara Fasawfa Ya`lamūna  | 015-096 (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፡፡ በእርግጥም (ፍጻሜያቸውን) ወደፊት ያውቃሉ፡፡ | الَّذِينَ يَجْعَلُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَهاً آخَرَ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ |
Wa Laqad Na`lamu 'Annaka Yađīqu Şadruka Bimā Yaqūlūna  | 015-097 አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ | وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدْرُكَ بِمَا يَقُولُونَ |
Fasabbiĥ Biĥamdi Rabbika Wa Kun Mina As-Sājidīna  | 015-098 ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡ | فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُنْ مِنَ السَّاجِدِينَ |
Wa A`bud Rabbaka Ĥattá Ya'tiyaka Al-Yaqīnu  | 015-099 እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡ | وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ |