Ĥā-Mīm  | 044-001 ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ | حَا-مِيم |
Wa Al-Kitābi Al-Mubīni  | 044-002 አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ | وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ |
'Innā 'Anzalnāhu Fī Laylatin Mubārakatin 'Innā Kunnā Mundhirīna  | 044-003 እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡ | إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُبَارَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ |
Fīhā Yufraqu Kullu 'Amrin Ĥakīmin  | 044-004 በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡ | فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ |
'Amrāan Min `Indinā 'Innā Kunnā Mursilīna  | 044-005 ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡ | أَمْراً مِنْ عِنْدِنَا إِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ |
Raĥmatan Min Rabbika 'Innahu Huwa As-Samī`u Al-`Alīmu  | 044-006 ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ | رَحْمَةً مِنْ رَبِّكَ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ |
Rabbi As-Samāwāti Wa Al-'Arđi Wa Mā Baynahumā 'In Kuntum Mūqinīna  | 044-007 የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡ | رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا إِنْ كُنْتُمْ مُوقِنِينَ |
Lā 'Ilāha 'Illā Huwa Yuĥyī Wa Yumītu Rabbukum Wa Rabbu 'Ābā'ikumu Al-'Awwalīna  | 044-008 ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡ | لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ رَبُّكُمْ وَرَبُّ آبَائِكُمُ الأَوَّلِينَ |
Bal Hum Fī Shakkin Yal`abūna  | 044-009 በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ | بَلْ هُمْ فِي شَكٍّ يَلْعَبُونَ |
Fārtaqib Yawma Ta'tī As-Samā'u Bidukhānin Mubīnin  | 044-010 ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡ | فَارْتَقِبْ يَوْمَ تَأْتِي السَّمَاءُ بِدُخَانٍ مُبِينٍ |
Yaghshá An-Nāsa Hādhā `Adhābun 'Alīmun  | 044-011 ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡ | يَغْشَى النَّاسَ هَذَا عَذَابٌ أَلِيمٌ |
Rabbanā Akshif `Annā Al-`Adhāba 'Innā Mu'uminūna  | 044-012 آ«ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንናآ» (ይላሉም)፡፡ | رَبَّنَا اكْشِفْ عَنَّا الْعَذَابَ إِنَّا مُؤْمِنُونَ |
'Anná Lahumu Adh-Dhikrá Wa Qad Jā'ahum Rasūlun Mubīnun  | 044-013 (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡ | أَنَّى لَهُمُ الذِّكْرَى وَقَدْ جَاءَهُمْ رَسُولٌ مُبِينٌ |
Thumma Tawallaw `Anhu Wa Qālū Mu`allamun Majnūnun  | 044-014 ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) آ«የተሰተማረ ዕብድ ነውآ» ያሉም ሲኾኑ፡፡ | ثُمَّ تَوَلَّوْا عَنْهُ وَقَالُوا مُعَلَّمٌ مَجْنُونٌ |
'Innā Kāshifū Al-`Adhābi Qalīlāan 'Innakum `Ā'idūna  | 044-015 እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡ | إِنَّا كَاشِفُوا الْعَذَابِ قَلِيلاً إِنَّكُمْ عَائِدُونَ |
Yawma Nabţishu Al-Baţshata Al-Kubrá 'Innā Muntaqimūna  | 044-016 ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡ | يَوْمَ نَبْطِشُ الْبَطْشَةَ الْكُبْرَى إِنَّا مُنتَقِمُونَ |
Wa Laqad Fatannā Qablahum Qawma Fir`awna Wa Jā'ahum Rasūlun Karīmun  | 044-017 ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡ | وَلَقَدْ فَتَنَّا قَبْلَهُمْ قَوْمَ فِرْعَوْنَ وَجَاءَهُمْ رَسُولٌ كَرِيمٌ |
'An 'Addū 'Ilayya `Ibāda Al-Lahi 'Innī Lakum Rasūlun 'Amīnun  | 044-018 آ«የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡ | أَنْ أَدُّوا إِلَيَّ عِبَادَ اللَّهِ إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ |
Wa 'An Lā Ta`lū `Alá Al-Lahi 'Innī 'Ātīkum Bisulţānin Mubīnin  | 044-019 آ«በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡ | وَأَنْ لاَ تَعْلُوا عَلَى اللَّهِ إِنِّي آتِيكُمْ بِسُلْطَانٍ مُبِينٍ |
Wa 'Innī `Udhtu Birabbī Wa Rabbikum 'An Tarjumūni  | 044-020 آ«እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡ | وَإِنِّي عُذْتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُمْ أَنْ تَرْجُمُونِ |
Wa 'In Lam Tu'uminū Lī Fā`tazilūni  | 044-021 آ«በእኔም ባታምኑ ራቁኝآ» (ተዉኝ አለ)፡፡ | وَإِنْ لَمْ تُؤْمِنُوا لِي فَاعْتَزِلُونِ |
Fada`ā Rabbahu 'Anna Hā'uulā' Qawmun Mujrimūna  | 044-022 ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) آ«እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸውآ» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡ | فَدَعَا رَبَّهُ أَنَّ هَاؤُلاَء قَوْمٌ مُجْرِمُونَ |
Fa'asri Bi`ibādī Laylāan 'Innakum Muttaba`ūna  | 044-023 (ጌታው) آ«ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡ | فَأَسْرِ بِعِبَادِي لَيْلاً إِنَّكُمْ مُتَّبَعُونَ |
Wa Atruki Al-Baĥra Rahwan 'Innahum Jundun Mughraqūna  | 044-024 آ«ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውናآ» (አለው)፡፡ | وَاتْرُكِ الْبَحْرَ رَهْواً إِنَّهُمْ جُندٌ مُغْرَقُونَ |
Kam Tarakū Min Jannātin Wa `Uyūnin  | 044-025 ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡ | كَمْ تَرَكُوا مِنْ جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
Wa Zurū`in Wa Maqāmin Karīmin  | 044-026 ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡ | وَزُرُوعٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ |
Wa Na`matin Kānū Fīhā Fākihīna  | 044-027 በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡ | وَنَعْمَةٍ كَانُوا فِيهَا فَاكِهِينَ |
Kadhālika Wa 'Awrathnāhā Qawmāan 'Ākharīna  | 044-028 (ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡ | كَذَلِكَ وَأَوْرَثْنَاهَا قَوْماً آخَرِينَ |
Famā Bakat `Alayhimu As-Samā'u Wa Al-'Arđu Wa Mā Kānū Munžarīna  | 044-029 ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡ | فَمَا بَكَتْ عَلَيْهِمُ السَّمَاءُ وَالأَرْضُ وَمَا كَانُوا مُنظَرِينَ |
Wa Laqad Najjaynā Banī 'Isrā'īla Mina Al-`Adhābi Al-Muhīni  | 044-030 የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡ | وَلَقَدْ نَجَّيْنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنَ الْعَذَابِ الْمُهِينِ |
Min Fir`awna 'Innahu Kāna `Ālīāan Mina Al-Musrifīna  | 044-031 ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡ | مِنْ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ كَانَ عَالِياً مِنَ الْمُسْرِفِينَ |
Wa Laqadi Akhtarnāhum `Alá `Ilmin `Alá Al-`Ālamīna  | 044-032 ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡ | وَلَقَدِ اخْتَرْنَاهُمْ عَلَى عِلْمٍ عَلَى الْعَالَمِينَ |
Wa 'Ātaynāhum Mina Al-'Āyāti Mā Fīhi Balā'un Mubīnun  | 044-033 ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡ | وَآتَيْنَاهُمْ مِنَ الآيَاتِ مَا فِيهِ بَلاَءٌ مُبِينٌ |
'Inna Hā'uulā' Layaqūlūna  | 044-034 እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡- | إِنَّ هَاؤُلاَء لَيَقُولُونَ |
'In Hiya 'Illā Mawtatunā Al-'Ūlá Wa Mā Naĥnu Bimunsharīna  | 044-035 እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡ | إِنْ هِيَ إِلاَّ مَوْتَتُنَا الأُولَى وَمَا نَحْنُ بِمُنشَرِينَ |
Fa'tū Bi'ābā'inā 'In Kuntum Şādiqīna  | 044-036 እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡ | فَأْتُوا بِآبَائِنَا إِنْ كُنتُمْ صَادِقِينَ |
'Ahum Khayrun 'Am Qawmu Tubba`in Wa Al-Ladhīna Min Qablihim 'Ahlaknāhum 'Innahum Kānū Mujrimīna  | 044-037 እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡ | أَهُمْ خَيْرٌ أَمْ قَوْمُ تُبَّعٍ وَالَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ أَهْلَكْنَاهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا مُجْرِمِينَ |
Wa Mā Khalaqnā As-Samāwāti Wa Al-'Arđa Wa Mā Baynahumā Lā`ibīna  | 044-038 ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡ | وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لاَعِبِينَ |
Mā Khalaqnāhumā 'Illā Bil-Ĥaqqi Wa Lakinna 'Aktharahum Lā Ya`lamūna  | 044-039 ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ | مَا خَلَقْنَاهُمَا إِلاَّ بِالْحَقِّ وَلَكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لاَ يَعْلَمُونَ |
'Inna Yawma Al-Faşli Mīqātuhum 'Ajma`īna  | 044-040 የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡ | إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ |
Yawma Lā Yughnī Mawláan `An Mawláan Shay'āan Wa Lā Hum Yunşarūna  | 044-041 ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡ | يَوْمَ لاَ يُغْنِي مَوْلىً عَنْ مَوْلىً شَيْئاً وَلاَ هُمْ يُنصَرُونَ |
'Illā Man Raĥima Al-Lahu 'Innahu Huwa Al-`Azīzu Ar-Raĥīmu  | 044-042 አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡ | إِلاَّ مَنْ رَحِمَ اللَّهُ إِنَّهُ هُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ |
'Inna Shajarata Az-Zaqqūmi  | 044-043 የዘቁመ ዛፍ | إِنَّ شَجَرَةَ الزَّقُّومِ |
Ţa`āmu Al-'Athīmi  | 044-044 የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡ | طَعَامُ الأَثِيمِ |
Kālmuhli Yaghlī Fī Al-Buţūni  | 044-045 እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡ | كَالْمُهْلِ يَغْلِي فِي الْبُطُونِ |
Kaghalyi Al-Ĥamīmi  | 044-046 እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡ | كَغَلْيِ الْحَمِيمِ |
Khudhūhu Fā`tilūhu 'Ilá Sawā'i Al-Jaĥīmi  | 044-047 ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡ | خُذُوهُ فَاعْتِلُوهُ إِلَى سَوَاءِ الْجَحِيمِ |
Thumma Şubbū Fawqa Ra'sihi Min `Adhābi Al-Ĥamīmi  | 044-048 ከዚያም آ«ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡آ» | ثُمَّ صُبُّوا فَوْقَ رَأْسِهِ مِنْ عَذَابِ الْحَمِيمِ |
Dhuq 'Innaka 'Anta Al-`Azīzu Al-Karīmu  | 044-049 آ«ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህናآ» (ይባላል)፡፡ | ذُقْ إِنَّكَ أَنْتَ الْعَزِيزُ الْكَرِيمُ |
'Inna Hādhā Mā Kuntum Bihi Tamtarūna  | 044-050 آ«ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነውآ» (ይባላሉ)፡፡ | إِنَّ هَذَا مَا كُنتُمْ بِهِ تَمْتَرُونَ |
'Inna Al-Muttaqīna Fī Maqāmin 'Amīnin  | 044-051 ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ | إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ |
Fī Jannātin Wa `Uyūnin  | 044-052 በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ | فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
Yalbasūna Min Sundusin Wa 'Istabraqin Mutaqābilīna  | 044-053 ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡ | يَلْبَسُونَ مِنْ سُندُسٍ وَإِسْتَبْرَقٍ مُتَقَابِلِينَ |
Kadhālika Wa Zawwajnāhum Biĥūrin `Īnin  | 044-054 (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ | كَذَلِكَ وَزَوَّجْنَاهُمْ بِحُورٍ عِينٍ |
Yad`ūna Fīhā Bikulli Fākihatin 'Āminīna  | 044-055 በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡ | يَدْعُونَ فِيهَا بِكُلِّ فَاكِهَةٍ آمِنِينَ |
Lā Yadhūqūna Fīhā Al-Mawta 'Illā Al-Mawtata Al-'Ūlá Wa Waqāhum `Adhāba Al-Jaĥīmi  | 044-056 የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡ | لاَ يَذُوقُونَ فِيهَا الْمَوْتَ إِلاَّ الْمَوْتَةَ الأُولَى وَوَقَاهُمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ |
Fađlāan Min Rabbika Dhālika Huwa Al-Fawzu Al-`Ažīmu  | 044-057 ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ | فَضْلاً مِنْ رَبِّكَ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ |
Fa'innamā Yassarnāhu Bilisānika La`allahum Yatadhakkarūna  | 044-058 (ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ | فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ |
Fārtaqib 'Innahum Murtaqibūna  | 044-059 ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡ | فَارْتَقِبْ إِنَّهُمْ مُرْتَقِبُونَ |